ፈልግ

ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰማይ ንግሥት ጸሎት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰማይ ንግሥት ጸሎት   (Vatican Media) ርዕሰ አንቀጽ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ በውይይት ወደ ሰላም መንገድ መመለስ እንደሚገባ ጠይቀዋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰማይ ንግሥት ባቀረቡት ጸሎት በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ወገኖች በመካከላቸው የሚታየውን ወታደራዊ ጥቃት እና ጦርነትን የሚያባብስ የቃላት ልውውጥ አስወግደው ድርድር እንዲጀምሩ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

እሑድ ሚያዝያ 23/2014 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተገኙት በርካታ ምዕመናን ጋር ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰማይ ንግሥት ጸሎታቸውን ባቀረቡበት ወቅት፣ “በእርግጥ በዩክሬን ውስጥ ሰላምን ለማምጣት ጥረት እየተደረገ ነው?" በማለት መጠየቃቸው ይታወሳል።    

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት፣ የሰላም ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ የከተታቸው በመሆኑ   ይህን ጥርጣሬአቸውን በጥያቄ መልክ ማቅረብን መርጠዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣው እና አሳሳቢው ወታደራዊ ግጭት፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሲቪሎችን ከፍተኛ ዋጋን እያስከፈለ እንደሚገኝ እና በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረግ የቃላት ዛቻዎች ወደ አጠቃላይ የኒውክሌር ጥቃት የሚያመራ ይመስላል።

የሩስያ ጦር ኃይል በዩክሬን ላይ የሚፈጽመው የጥቃት ጦርነት፣ ከባድ የጦር መሣሪያ የማስታጠቅ ውድድር፣ሰላምን ለማስከበር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ ጠንካራ ተነሳሽነት አለመኖሩ፣ በከፍተኛ የጦር መሣሪያ በመታገዝ ወደ ቀድሞ የጦርነት ዘመን መመለስ የማይቀር እንደሆነ የሚናገሩ ሰዎች አስተሳሰብን የሚያጠናክር ይመስላል።

ይህ እየሆነ ባለበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ ሚያዝያ 23/2014 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለእኩለ ቀን ጸሎት ለተሰበሰቡት ምዕመናን ባሰሙት ንግግር፣ ለበርካታ ሳምንታት የዘለቀውን የዩክሬን ጦርነት ለማስቆም እና ሰላምን ለማምጣት እውነተኛ ፍላጎት ስለመኖሩ፣ የጦር መሣሪያዎች ድምጽ እንዳይሰማ ለማድረግ በተቻለ መጠን ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ እና በዘላቂነት እየጨመረ ያለውን ወታደራዊ እና የቃላት ሽኩቻዎችን ለማስወገድ ፍላጎት እንዳለ ለማወቅ ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ሆነው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ለር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ለመስጠት ችግር እናዳለ በጣም ግልጽ ነው። የዓለም መንግሥታት መሪዎች መልስ “ሁላችንም ሰላምን እንፈልጋለን” የሚል ነው። ነገር ግን ይህ በቃላት የተገለጸው ፍላጎት ወደ ተግባር ተለውጦ በቁርጠኝነት ለድርድር ካልተደረሰ በቀር እውነተኛ ፍላጎት ሊሆን አይችልም። ስለ ሰላም በቃላት ብቻ ተናግሮ በተግባር የማይገልጹት ከሆነ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "የጦርነት እቅድ" ብለው የጠሩት ድርጊት ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በቅርቡ በተካሄደው የሄልሲንኪ ኮንፈረንስ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ የተከሰተውን ነገር ስንመለከት፣ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና በመዋቅሮቻቸው ላይ የበለጠ መተማመን እንደሚያስፈልግ፣ ሁሉም ሰው ውክልና እንዳለው እና

የበለጠ 'የጋራ ቤት' እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይሰማናል። እንደዚሁም አዲስ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥርዓትን መገንባት እንደሚያስፈልግ በማመን፣ ከአሁን በኋላ ዓለም አቀፍ ግንኙነቱ በአውዳሚ የጦር መሣሪያ ትጥቅ እና ወታደራዊ ኃይል ላይ እንዳይመሠረት ማድረጉ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ካላሰብን እና ​​ካልሠራን ወደ ጠቅላላ የጦርነት ገደል ለመሮጥ ተዘጋጅተናል።" ማለታቸው ይታወሳል።

በዚህም መሠረት፣ የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ የሆኑት ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ “ለአመጽ እና ለጦር መሣሪያ አመክንዮ ሳንገዛ፣ ወደ ውይይት መድረክ እና ወደ ሰላም መንገድ መጓዝ ያስፈልጋል” በማለት ደጋግመው መጠየቃቸውን የቅድስት መንበር ርዕሠ አንቀጽ ገልጿል።

(ANDREA TORNIELLI - editorial director of the Dicastery for Communication of the Holy See.)

03 May 2022, 16:53