ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የራሳችሁን እና የሌሎችን ተጋላጭነት ማወቅ ተገቢ ነው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም ለዓለም አቀፉ የበላይ አለቆች ኅብረት (UISG) (በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች ሕብረት) ባደረጉት ንግግር ደናግላን ገዳማዊያት ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ እና መግደላዊት ማርያም በማሰብ እና በማሰላሰል ራሳቸውን ሌሎችን ለማገልገል እንዲያነሳሱ እና የሲኖዶስ ጉዟቸውን ማድረግ እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዚህ ሳምንት በመቶዎች የሚቆጠሩ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች (UISG “International Union of Superiors Generals”) ጠቅላላ ጉባኤ በሮም ከተማ መካሄዱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጉባሄ "በሲኖዶሳዊ ጉዞ ላይ ያለውን ተጋላጭነት መቀበል" በሚለው መሪ ሃሳብ ሲቃኙ ቆይተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሐሙስ ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም በቫቲካን በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ያደረጉት ንግግር በዚህ ጭብጥ ላይ ያተኮረ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር ላይ አንዳንድ ነጥቦችን በመጥቀስ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ በተጠቀሱ በሁለት ትዕይንቶች ላይ አትኩረው መናገራቸው ተገልጿል።

ተጋላጭነት እና አገልግሎት

ቅዱስነታቸው በቀዳሚነት የገለጹት ትይንት ኢየሱስ በመጨረሻው እራት የጴጥሮስን እግር ማጠቡን በሚያመልክተው ትይንት ላይ ያተኮረ ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ ሁኔታ ላይ ማሰላሰላችን “ሁለቱም ማለትም የጴጥሮስን ተጋላጭነት እና ኢየሱስ እሱን ለማግኘት የሚያደርገውን ጉዞ ተጋላጭነት እንድንገነዘብ ያደርገናል” ሲሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች መናገራቸው ተዘግቧል።

“ጴጥሮስ የወንድሞቹንና የእህቶቹን እግር ማጠብ እንዲችል እግሩን እንዲታጠብ የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የልብ ለውጥ እንደሚያስፈልገው መቀበል ከብዶት ነበር” ብሏል።

ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ ኢየሱስ ጰጥሮስን ለማግኘት በመውጣት “የእግዚአብሔር ልጅ ራሱን ተጋላጭ በሆነ ቦታ፣ በአገልጋይነት ቦታ ያስቀምጣል፣ ይህም የኢየሱስን ሕይወት በአገልግሎት ውስጥ ብቻ እንዴት መረዳት እንደሚቻል ያሳያል” ብለዋል።

ከጴጥሮስ ጋር አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ “ቤተ ክርስቲያን ሌሎችን በማገልገል ህይወቷን ለመስጠት እንድትችል፣ ደካማነቷን እንድትገነዘብ እና እንድትቀበል፣ ከዚያ በመነሳት ሌሎችም ደካሞች መሆናቸውን እንደ መምህሯ ትማራለች” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች የማሕበሮቻቸው አባላትን ህይወት እንዲያነቃቁ እና በገዳሞቻቸው ውስጥ ያለውን አስተዋይነት እንዲያጅቡ ተሳታፊዎችን የጋበዙ ሲሆን ኢየሱስ በመጨረሻው እራት ላይ የሐዋርያቱን እግር እንዳጠበ ሁሉ “ወደዚህ የእግር መታጠቢያ ቦታ ገብተው፣ በዚህ የቤተክርስቲያን መንገድ እንዲሄዱ እና ኃላፊነታቸውን እንደ አገልግሎት በመቁጠር እንዲወጡ” ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች እንደ ተናገሩት ከሆነ ዛሬ መንፈሳዊ እና የገዳም ሕይወት አንዳንድ ጊዜ ችግር ቢገጥሙትም ተጋላጭነታቸውን እንዲገነዘቡ አክለው ተናግሯል።

በመቀጠልም የእግዚአብሔር ልጅ ራሱን በሰው ልጆች እግር ስር በማስቀመጥ ሊይዘው የሚፈልገው ቦታ “ሥነ-መለኮታዊ ቦታ” እንደሆነ ተናግሯል።

"እንደ ጴጥሮስ እና ከጴጥሮስ ጋር፣ አሁን ተጠርተናል፣ ተጋላጭነታችንን ከተገነዘብን በኋላ፣ እኛ ገዳማዊያን ወንድሞች እና ገዳማዊያት እህቶች ዛሬ እራሳችንን ዝቅ ማድረግ ያለብን አዳዲስ ተጋላጭነቶች ምንድ ናቸው ብለን እራሳችንን እንድንጠይቅ ተጠርተናል”።

በገዳሞቻቸው እና በመንፈሳዊ ማሕበሮቻቸው ውስጥ ካሉ እህቶች ጀምሮ ወደ “የቆሰሉት የሰው ልጆች እግር” እንዲቀርቡም ጠይቀዋል።

በሁለተኛው የወንጌል ትዕይንት ላይ ባተኮረው ንግግራቸው ቅዱስነታቸው እንደገለጹት በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው መግደላዊት ማርያም ዋና ተዋናይ ነበረች። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ከተዝረከረከ እና ከተበላሸ ሕይወት ወደ ኢየሱስ እና የአዋጅ አገልግሎትን ማዕከል ያደረገ ሕይወት መሸጋገር ምን ማለት እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች" ብለዋል።

ሲኖዶሳዊው መንገድ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትኩረታቸውን ወደ ሲኖዶሳዊው መንገድ በማዞር በቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶሳዊ ጉዞ ውስጥ ቤተክርስቲያን ከገዳማዊያን እና ከዳማዊያት ሕይወት የምትጠብቀው አስተዋጽኦ ምን እንደሆነ አመልክተዋል።

“ሲኖዶሱ ከምንም በላይ አስፈላጊ የመደማመጥ እና የማስተዋል ጊዜ ከሆነ እናንተ ማድረግ የሚትችሉት ዋናው አስተዋፅዎ በአስተያየት እና በማስተዋል መሳተፍ ነው” ሲሉ ለተሰበሰቡት ተናግሯል።

"በዚህ ሲኖዶሳዊ ሂደት የኢየሱስን ሕይወት እና ተልዕኮ እያሰባችሁ ህብረት ገንቢዎች ሁኑ" ብለዋል። ምእመናንም የሲኖዶሳዊ ጉዟቸውን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን የደናግላን ገዳማት እና መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች እህቶች ያደርጉትን ንግግር ሲያጠቃልሉ  “በዚህ ሲኖዶስ ሂደት ውስጥ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎች አብረዋቸው ኅብረትን ለመገንባት ጠበብት በመሆን መደማመጥን እና ማስተዋልን እንዲያሳድጉ” እንደሚተማመኑ ተናግሯል።

በተጨማሪም “በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እየኖርን ያለውን የሲኖዶስ ሂደት በእናንተ ተቋሞች ውስጥም ሊፈጸም ይችላል፣ ወጣቶችም ሆኑ አዛውንቶች ጥበባቸውን እና የተቀደሰ ህይወት ራዕያቸውን ይለዋወጣሉ” የሚል ተስፋም እንዳላቸው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መንፈሳዊ ጥሪ ተቀብለው ወደ ገዳማት የሚገቡ ወንድሞች እና እሕቶች እጥረት እና የእርጅና ስጋት እንዳለ አረጋግጠዋል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ “ዋናው ነገር ሁል ጊዜ ታማኝ እና በፈጠራ የተቃኜ ምላሽ ለጌታ መስጠት መቻል ነው። ከእግዚአብሔር የተሰጠን ጸጋ በትክክለኛው ጊዜ እና የምንኖርበትን ዘመን እንኳን ደህና መጣህ በማለት ልንቀበል ይገባል፣ ከእጁ የሚያመልጥ የለምና” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።  

05 May 2022, 11:58