ፈልግ

ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የፋርማሲ ባለሞያ ፌዴሬሽን አባላትን ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የፋርማሲ ባለሞያ ፌዴሬሽን አባላትን  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ የፋርማሲ ባለሞያዎች በወረርሽኙ ወቅት ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታወሱ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የፋርማሲ ባለሞያ ፌዴሬሽን አባላትን በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው በቅድስት ማርታ የብጹዓን ጳጳሳት መኖሪያ ቤት ውስጥ ተቀብለው አነጋግረዋል። ቅዱስነታቸው ለአባላቱ ባደረጉት ንግግር፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረገው የሕክምና አገልግሎት እና የመድኃኒት አቅርቦት፣ ለሰው ልጅ ያለው ቅርበት በተግባር የተገጠበት ልዩ አጋጣሚ እንደነበር አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የፋርማሲ ባለሞያዎች ኅብረት እና ተነሳሽነት ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት እንደ አስተማማኝ ተገን ሆኖ እንዳገለገለ፣ የተገኘውን ዕድል ተጠቅመው በአንድነት መሰብሰብ የቻሉበት፣ በዜጎች እና በጤና ሥርዓቱ መካከል “ድልድይ” ሆነው ያገለገሉበት እና ለወረርሽኙ የነበረውን ሐሰተኛ ጥንካሬን ያጋለጡበት ጠቃሚ እገዛ” እንደነበር ገልጸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የፋርማሲ ባለሞያ ፌዴሬሽን አባላትን በሐዋርያዊ ሕንጻ ውስጥ ሳይሆን በቅድስት ማርታ የብጹዓን ጳጳሳት መኖሪያ ቤት የተቀበሏቸው፣ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በጉልበቱ ላይ በደረሰው ሕመም ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ቅዱስነታቸው ለፋርማሲ ባለሞያ ማኅበራት አባላት ባሰሙት ንግግር፣ ማኅበሩ እንደ ሌሎች የቤተክርስቲያን ማኅበራት ሁሉ በግል ተነሳሽነት፣ ሁሉን ሰው ተቀብለው አገልግሎትን ለማበርከት ባለው ስሜት መሠረት እና "በሰብዓዊ ክብር ላይ በተመሰረተው ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር መርሆዎችን በመከተል ነው" ብለዋል። 

ወረርሽኙ በሚከሰትበት ጊዜ ዋና ዋና ክስተቶች

ወረርኙ የሚገኝበትን ደርጃ በማስታወስ ንግግራቸውን ያቀረቡት ቅዱስነታቸው፣ ወረርሽኝ ያስከተለውን ቀውስ እንደ መልካም አጋጣሚ መመልከት ያስፈልጋል ብለው፣ በዚህ አጋጣሚ አማካይነት "ከካቶሊካዊ ባሕል ጋር ግንኙነት ያላቸውን የአስተሳሰብ እሴቶችን" ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኙ ወቅት መሄጃ ያጡ በርካታ ዜጎች የሕክምና ዕርዳታን፣ ምክርን፣ መረጃን እና ዋስትናን ከሕክምና ባለሞያዎቹ እናዳገኙ ቅዱስነታቸው ገልጸተው፣ በጊዜው ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስፈላጊ የሆኑ ምርመራዎችን በፍጥነት ለማከናወን አስፈላጊ እንደነበር አስታውሰው፣ ይህ ሁኔታ በሞያዊ የሥራ ዘርፍ አባላቱ ኅብረታቸውን እንዲያጠናክሩት የረዳቸው መሆንኑ ገልጸዋል።

ማኅበራዊ ሚና

የፋርማሲ ባለሞያዎች ዜጎችን ከጤና ሥርዓቱ ጋር በማገናኘት ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር ገልጸው ካለፉት ቅርብ ወራት ወዲህ የወረርሽኙ ስርጭት መቀነሱን እና አንዳንዴም አለመታየቱን ተናግረዋል። ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተደረጉ አንዳንድ ረጅም ሂደቶች በዜጎች ላይ ችግርን እና ስቃይን እንዳስከተሉ ገልጸው፣ በወረርሽኙ የተጠቁትን በጤናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን አስረድተዋል።

የፋርማሲ ባለሞያዎች ለጋራ ጥቅም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እጥፍ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው፣ በጤና ሥርዓቱ ላይ የወደቀውን ሸክም ከማቅለል በተጨማሪ ማኅበራዊ ውጥረትን ያቃልላል ብለዋል። ሚናው በታላቅ ጥንቃቄ እና ሙያዊ ብቃት መከናወን እንዳለበት፣ ነገር ግን ወደ ሕሙማን ዘንድ ለድረስ የሚደረግ የአቀራረብ ገጽታ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስነታቸው አስረድተዋል።

አዲስ የኑሮ ዘይቤ አራማጆች

በሌሎች ባሕሎች፣ እንደ ምሥራቁ የዓለማችን ክፍሎች እና በአሜሪካ ቀደምት ነዋሪዎች ዘንድ በሚገኙ ገዳማት ውስጥ ያደጉ የመድኃኒት ቅመማ ልምዶች ለዘመናዊው የመድኃኒት ቅመማ ዘዴ ያበረከቱትን አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑን በማስታወስ የፋርማሲ ባለሞያዎች ለሥነ ምሕዳር ሽግግር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መኖሩን ጠቅሰዋል።

03 May 2022, 16:38