ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለኢየሱሳዊያን ማሕበር አባላት የቪዲዮ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት የሚያሳይ ምስል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለኢየሱሳዊያን ማሕበር አባላት የቪዲዮ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት የሚያሳይ ምስል። 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሲኖዶሳዊነት ወደ ህያው ኅብረት ሊመራን ይገባል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን ምልአተ ጉባኤ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት የሲኖዶሳዊነት እና የኅብረት ትርጉም ላይ በማንፀባረቅ ቤተክርስቲያን የሲኖዶሳዊ ጉዞ ስትጀምር ሁለቱም ማለትም ሲኖዶሳዊነት እና ሕብረት አስፈላጊ ናቸው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሲኖዶሳዊነት በላቲን አሜሪካ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥር እየሰደደ ሲሆን የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ አስተምህሮት "በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱትን ወቅታዊ ለውጦች በመጋፈጥ አዲስ ትምህርትን መማር" የሚለውን "ትክክለኛውን ትርጓሜ" ተቀብያለሁ ብለዋል።

በዚሁ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን አሜሪካ ለሚገኘው ጳጳሳዊ ኮሚሽን “በዚህ ሲኖዶሳዊ ጎዳና ላይ መብሰል እና የወንጌል ፍሬ ማፍራት እንድንችል ያለንን ውስንነት ማወቅ አለብን” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ሲኖዶሳዊነት እና ሕብረት” በሚል መሪ ቃል ለኮሚሽኑ ሙሉ ጉባኤ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት መንፈስ ቅዱስ፣ የሲኖዶሳዊው ጉዞ ዋና ተዋናይ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በንግግራቸው ራሳችንን “ሁሉን እንደምናውቅ” ወይም ለሁሉም ነገር መልስ እንዳለን በማመን  እንዳንታለል በአእምሯችን ውስጥ ክፍት የመሆንን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ተንግረዋል። ሁሉንም ነገር እንደምናውቅ መገመት ለሲኖዶሳዊነት “በጣም አደገኛ ነው” ያሉ ሲሆን “መንፈስ ቅዱስ እውነተኛው የሲኖዶሳዊ መንገድ ዋና ተዋናይ” ስለሆነ ቦታ ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።

“ስጦታው መንፈስ ቅዱስ ነው” ሲሉ ጳጳሱ በመልእክታቸው የተናገሩ ሲሆን “እራሱን በጉልበት የማይጭን ነገር ግን ፍቅራችንን እና ነፃነታችንን በእርጋታ ጠርቶ በግንኙነታችን ውስጥ የሚፈልገውን የአንድነትና የኅብረት መልክ እንድንይዝ ያደርገናል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህን የመንፈስ ስጦታ ማግኘት ከቻልን ሕይወታችን “ለሌሎች የማያቋርጥ አገልግሎት” ይሆናል ብለዋል።

መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ይንቀሳቀሳል እና ያድሳል እንጂ ከእኛ አይወስድም ብሏል። “መንፈስ ቅዱስ ያለፈው ኃይል አይደለም። ይልቁንም ጴንጤቆስጤ በራሳችን ጊዜ እየተፈጸመ ነው፡- ‘ታላቅ ያልታወቀ’፣ ምንም ምስል የሌለው፣ ሁልጊዜም ወቅታዊ ነው እናም እኛን ማጽናናት እና ማስተማር አያቆምም!”  ብለዋል።

ሕበረት ሲኖዶሳዊውን መንገድ መንካት አለበት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሲኖዶሳዊነት መንፈስ ላይ የተመሠረተ ብቻ ሳይሆን፣ ከክርስቶስ አካል ጋር ኅብረትን የሚያካትት በመሆኑ፣ “ቤተ ክርስቲያንን የሚቀርጽ የግንኙነት ተለዋዋጭነት ምልክት እና መሣሪያ” በመሆኑ የሕብረት ምንጭ መሆኑን አበክረው ገልጸዋል።

ሲኖዶሳዊነት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንዳሉት “ተለዋዋጭ ልኬት፣ በሥላሴ ኅብረት ውስጥ የተመሰረተው የቤተ ክህነት ኅብረት ታሪካዊ ገጽታ፣ እሱም በአንድ ጊዜ የሁሉም ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ስሜት፣ ሐዋርያዊ ምእመናን እና ከጴጥሮስ ተተኪ ጋር ያለው አንድነት ይንከባከባል። በየደረጃው ያለው የቤተ ክርስቲያን ለውጥ እና ተሃድሶ እንዲያደርግ ይረዳል ብለዋል።

ሲኖዶሳዊነትን የማስተዋወቅ ግዴታ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመቀጠል የጳጳሳዊ ኮሚሽንን ሚና ተመልክተዋል፣ ይህም እንደ ዲያቆንያ ማለትም አገልጋይ መሆን ማለት እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን ለላቲን አሜሪካ ያላቸውን ፍቅር እና ትኩረት ለማሳየት ሞክረዋል።

27 May 2022, 13:46