ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አረጋውያን በእምነት ጎዳና ላይ በጽናት እንድንጓዝ ያስተምሩናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በግንቦት 10/2014 ዓ.ም በቫቲካን ከሚገኘው ከቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሆነው ባደረጉት የክፍል 10 አስተምህሮ አረጋዊያን በእመንት ጎዳና ላይ በጽናት እንድንጓዝ ያስተምሩናል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን  

በእለቱ የተነበበው የእግዚአብሔር ቃል

ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤ “አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ። .[…] በእርግጥ ያልገባኝን ነገር፣ የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጒዳይ ተናገርሁ። “ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤ አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ። ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ። ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።” እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት ባረከ። ከዚህ በኋላ ኢዮብ አንድ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። በዚህ ሁኔታ አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ (ኢዮብ 42,1-6.12.16)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው እናቀርበዋለን፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

አሁን ከመጽሐፈ ኢዮብ ተወስዶ በተነበበው አሁን የሰማነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እጅግ የላቀ ዓለም አቀፋዊ በሆነ የጽሑፋዊ ጥበብ ውጤት ይጠናቀቃል። በትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮዋችን የጉዞ ሂደት ላይ፣ ኢዮብን ያገኘነው በሽምግልና ጊዜው ነው። የእግዚአብሔርን “ባሕርይ” የማይቀበል ነገር ግን እግዚአብሔር ምላሽ እስኪሰጥና ፊቱን እስኪገልጥ ድረስ ጮክ ብሎ የሚቃወም የእምነት ምስክር ሆኖ እናገኘዋለን። እናም በመጨረሻ፣ እግዚአብሔር እንደ ሁልጊዜው፣ በሚያስደንቅ ሁኔታ ምላሽ ይሰጣል - እርሱን በዙም እንዲጎዳ ሳያደርገው ክብሩን ያሳየዋል ወይም በተሻለ ሁኔታ፣ በሉዑላዊ ርህራሄ ይመለከተዋል። የኢዮብ ጩኸት ምን ያህል እንደሆነ ለመረዳት የዚህን መጽሐፍ ገጾች ያለ ጭፍን ጥላቻ በደንብ ማንበብ አለብን። ሁሉን ነገር በማጣታችን ከስቃዩ ብስጭት እና ምሬት የተነሳ የሞራል ፈተናን ለማሸነፍ እራሳችንን በእርሱ  የሕይወት ትምህርት ቤት ብናስቀምጥ ጥሩ ነበር።

በዚህ የመጽሃፉ ማጠቃለያ ክፍል - እግዚአብሔር በመጨረሻ መድረኩን ሲይዝ - ኢዮብ ይመሰገናል፣ ምክንያቱም ከዝምታው በስተጀርባ የተደበቀውን የእግዚአብሔርን የርህራሄ ምስጢር ስለተረዳ ነው። ስለ እግዚአብሔር እና ስለ መከራ ሁሉን ነገር ያውቃሉ ብለው የገመቱትን የኢዮብን ወዳጆች እና ኢዮብን ሊያጽናኑ ከመጡ በኋላ፣ በመጨረሻ ባሰቡት ምሳሌያዊ አነጋገራቸው ፈርደውበት የነበረውን የኢዮብን ወዳጆች ገስጿል። እግዚአብሔር ከዚህ አስመሳይ እና ትምክህተኛ ሃይማኖት ይጠብቀን!

ሕያው እግዚአብሔር በእነርሱ ረገድ ራሱን የገለጸው በዚህ መንገድ ነው “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነዶአል። […] ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እንደ አሳፋሪ ተግባራችሁ እንዳላደ ርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር አልተናገራችሁምና” (ኢዮብ 42:7-8)። የእግዚአብሔር መግለጫ ያስገርመናል ምክንያቱም በኢዮብ ተቃውሞ የተቃጠሉ ገጾችን አንብበናል ይህም እንድንጨነቅ አድርጎናል። ነገር ግን ኢዮብ መልካም ነገር ተናግሯል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር “አሳዳጅ” መሆኑን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ እግዚአብሔር ይናገራል። ለእነዚያ መጥፎ ወዳጆቹ እንዲጸልይላቸው  ከጠየቀው በኋላ እግዚአብሔር እንደ ሽልማት ከንብረቱ ሁሉ እጥፍ እጥፍ ሰጠው።

በእምነት ንግግር ውስጥ የተለወጠው ነጥብ ኢዮብ ከችግሩ ወጥቶ ለመተንፈስ በበቃበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነው፣ እርሱም “የሚቤዠኝ ሕያው እንደሆነ፣ በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ። ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤ ሌላ ሳይሆን እኔው በገዛ ዐይኔ፣ እኔ ራሴ አየዋለሁ፤ ልቤ በውስጤ ምንኛ በጉጉት ዛለ (ኢዮብ 19፡25-27) በማለት ይናገራል። እንደሚከተለው ልንተረጉመው እንችላለን፡- “አምላኬ፣ አንተ አሳዳጅ እንዳልሆንክ አውቃለሁ። አምላኬ መጥቶ ፍርድ ይሰጠኝ" እንደ ማለት ይቆጠራል።

የኢዮብ መጽሐፍ ምሳሌ በአስደናቂ ሁኔታ በህይወት ውስጥ የሚሆነውን በአርአያነት የሚያመለክት ነው - በአንድ ሰው፣ በቤተሰብ እና በሰዎች ላይ ከባድ ፈተናዎች እንደሚወድቁ ከሰዎች ዝቅተኝነት እና ደካማነት አንፃር ተመጣጣኝ ያልሆነ፣ ብዙውን ጊዜ በህይወት ውስጥ "ዝናብ ሲዘንብ" እንደሚባለው ይከሰታል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ኢፍትሃዊ በሚመስለው የክፋት ክምችት ይሸነፋሉ።

ሁላችንም እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እናውቃለን። በእነሱ ጩኸት ተደንቀናል፣ ነገር ግን በእምነታቸው እና በፍቅራቸው ጽኑነት በአድናቆት ቆመናል። ከባድ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ልጆች፣ ቋሚ ሕመም ያለባቸውን ወይም የቤተሰባቸውን አባል የሚረዱትን ወላጆች እያሰብኩ ነው። እነዚህ ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ በኢኮኖሚያዊ ሀብቶች እጥረት ተባብሰዋል። በታሪክ ውስጥ በተወሰኑ ወቅቶች፣ ሸክሞች መከማቸታቸው የቡድን ቀጠሮ እንደተሰጣቸው እንዲሰማቸው ያደርጋል። በነዚህ አመታት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተከሰተው እና አሁን በዩክሬን ጦርነት እየሆነ ያለው ይህ ነው።

እነዚህን “ከመጠን በላይ ያሉ ነገሮችን” ወደ ከፍተኛ የተፈጥሮ እና የታሪክ ብልህነት እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? ለተጎጂዎች ኃጢአት ተገቢ ምላሽ እንደ ሚገባቸው በሃይማኖት ልንባርካቸው እንችላለን? አይ አንችልም። ተጎጂዎች የክፋትን ምስጢር በመመልከት መቃወም ያለባቸው አንድ ዓይነት መብት አለ፣ ይህም እግዚአብሔር ለሁሉም የሰጠው መብት፣ በእርግጥም፣ እሱ፣ ያነሳሳል። በድራማው የመጀመሪያ ቅፅበት የእግዚአብሔር "ዝምታ" ይህንን ያመለክታል። እግዚአብሔር ከሰው ዘንድ የሚቀርበውን ወቀሳ ከመጋፈጥ ወደ ኋላ አይልም፣ ነገር ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ፣ ኢዮብ ተቃውሞውን እንዲገልጽ ፈቀደለት። አንዳንድ ጊዜ ይህን አክብሮትና ርኅራኄን ከአምላክ መማር ያስፈልገናል።

የኢዮብ የእምነት ጥሪ – በትክክል ወደ እግዚአብሔር ከማያቋርጥ ልመና፣ ከፍትኛ ፍርድ የወጣው – በመጨረሻው ላይ ከሞላ ጎደል ምሥጢራዊ ገጠመኝ ጋር ይደመደማል፣ እርሱም እንዲህ እንዲል አድርጎታል፡- “ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ” (ኢዮብ 42፡5)። ይህ ምስክርነት በእርጅና ጊዜ፣ በሂደት ደካማነቱ እና ኪሳራው ውስጥ የተወሰደ በመሆኑ የሚታመን ነው። ያረጁ ሰዎች እነዚህን ብዙ ተሞክሮዎች አይተዋል! እንዲሁም የሰው ተስፋዎች ወጥነት የሌላቸው መሆናቸውንም አይተዋል። ጠበቆች፣ ሳይንቲስቶች አልፎ ተርፎም የሀይማኖት ሰዎች እንኳ ለደረሰባቸው መከራ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ናቸው በማለት አሳዳጁን ከተጠቂው ጋር ግራ ያጋባሉ።

የዚህን ምስክርነት መንገድ ያገኙ አረጋውያን፣ በችግራቸው ምክንያት የገጠማቸውን ቂም ወደ ጽናት የሚቀይሩት የእግዚአብሄርን ተስፋዎች በመጠባበቅ ላይ ያሉ አረጋውያን ከክፋት መብዛት ጋር በተያያዘ ለማህበረሰቡ የማይተኩ የመከላከያ ሥፍራዎች ናቸው። አይኑን ወደ መስቀሉ ያዞረ አማኝ ይማራል። ይህንንም እንደ ማርያም አንዳንድ ጊዜ ልብን የሚሰብር ጸሎታቸውን አንድ አድርገው ራሳቸውን ለአብ በመስቀል ላይ ወደሚተወው የእግዚአብሔር ልጅ ከብዙ አያቶች እና ቅድመ አያቶቻችን እንማር።

18 May 2022, 11:52

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >