ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 21 አዲስ ካርዲናሎችን ይፋ አደረጉ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 21 አዲስ ካርዲናሎችን ይፋ አደረጉ!  (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 21 አዲስ ካርዲናሎችን ይፋ አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 20/2014 ዓ.ም ለ21 አዲስ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግ መስጠታቸው የተገለጸ ሲሆን እነዚህ 21 አዳዲስ ካርዲናሎች ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እንደ መውጣጣታቸው ቤተክርስቲያንን በዓለም ዙሪያ እንደ ሚወክሉ እና የተለያዩ ባህሎችን፣ አውዶችን እና የሐዋርያዊ አገልግሎቶችን እንደ ሚያንጸባርኩ ማዕረገ ስዕመቱን በሰጡበት ወቅት መናገራቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እሁድ እለት ግንቦት 21/2014 ዓ.ም  “ የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እርሱ እንደ ተናገረው ከሞት ተነስቷል” የሚለውን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት 21 አዳዲስ ካርዲናሎች መሰየማቸውን ተናግሯል ።

በተጨማሪም በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት - ሰኞ እና ማክሰኞ  እ.አ.አ በመጪው ነሐሴ 29-30/2022 ዓ.ም - ከሁሉም ካርዲናሎች ጋር አዲሱን የሐዋርያዊ ሕገ በተመለከተ በቅዱስ ወንጌል እይታ ለማሰላሰል እንደሚገናኙ ተናግሯል።

እ.አ.አ ቅዳሜ ነሐሴ 27/2022 ዓ.ም ለአዲስ ካርዲናሎች ይፋዊ በሆነ መልኩ የካርዲናሎችን ምክር ቤት ይቀላቀላሉ። ለእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ጥቅም እና ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ እና ለተልእኮዬ እንዲረዱኝ እንጸልይ ማለታቸውም ተገልጿል።

የካርዲናሎች ከፍተኛ ምክር ቤት በአሁኑ ወቅት 208 ካርዲናሎችን ያቀፈ ሲሆን ከነዚህም 117ቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የመምረጥ እና ራሳቸውም የመመረጥ መብት ያላቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ  91 ካርዲናሎች ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆኖ የመመረጥ ወይም የመምረጥ መብት ያላቸው አይደሉም። እ.አ.አ ከመጪው ነሐሴ 27/2022 ዓ.ም ጀምሮ የጠቅላላ የካርዲናሎች ከፍተኛ ምክር ቤት አባላት ቁጥር ወደ 229 የሚያድግ ሲሆን ከነዚህም መካከል 131 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የመምረጥ እና የመመረጥ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው።

አዲስ ከተመረጡት ካርዲናሎች መካከል ስምንቱ ከአውሮፓ፣ ስድስቱ ከእስያ፣ ሁለቱ ከአፍሪካ፣ አንድ ከሰሜን አሜሪካ፣ አራት ከመካከለኛው እና ከላቲን አሜሪካ ናቸው።

የ21ዱ አዳዲስ ካርዲናሎች ስም እነሆ፡-

1. ሊቀ ጳጳስ አርተር ሮሽ - የመለኮታዊ አምልኮ እና የቅዱሳን ምስጢራት ጉባኤ አስተዳዳሪ

2. ሊቀ ጳጳስ ላዛሮ ዩ ሄንግ ሲክ - የቀሳውስት ማኅበረ አስተዳዳሪ

3. ሊቀ ጳጳስ ፈርናንዶ ቬርጌዝ አልዛጋ፤ የቫቲካን ከተማ ግዛት ጳጳሳዊ ኮሚሽን ፕረዚዳንት እና የቫቲካን ከተማ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ፕሬዝዳንት

4. ሊቀ ጳጳስ ዣን-ማርክ አቬሊን - የሜትሮፖሊታን የማርሴይ ሊቀ ጳጳስ (ፈረንሳይ)

5. ጳጳስ ፒተር ኦክፓሌኬ - የኤክሉሎቢያ (ናይጄሪያ) ጳጳስ

6. ሊቀ ጳጳስ ሊዮናርዶ ኡልሪክ ስቲነር፤ የማናውስ የሜትሮፖሊታን ሊቀ ጳጳስ (ብራዚል)

7. ሊቀ ጳጳስ ፊሊፔ ኔሪ አንቶኒዮ ሴባስቲአዎ ዲ ሮሳሪዮ ፌርራዎ - የጎዋ እና ዳማኦ ሊቀ ጳጳስ (ህንድ)

8. ኤጲስ ቆጶስ ሮበርት ዋልተር ማኬልሮይ - የሳንዲያጎ ጳጳስ (ሰሜን አሜሪካ)

9. ሊቀ ጳጳስ ቨርጂሊዮ ዶ ካርሞ ዳ ሲልቫ፤ የዲሊ ሊቀ ጳጳስ (ምስራቅ ቲሞር)

10. ጳጳስ ኦስካር ካንቶኒ - የኮሞ ጳጳስ (ጣሊያን)

11. ሊቀ ጳጳስ አንቶኒ ፑላ - የሃይደራባድ ሊቀ ጳጳስ  (ህንድ)

12. ሊቀ ጳጳስ ፓውሎ ሴዛር ኮስታ - የብራዚሊያ የሜትሮፖሊታን  ሊቀ ጳጳስ (ብራዚል)

13. ጳጳስ ሪቻርድ ኩዩያ ባዎብር፣  የዋ ጳጳስ (ጋና)

14. ሊቀ ጳጳስ ዊልያም ጎህ ሴንግ ቻዬ - የሲንጋፖር ሊቀ ጳጳስ (ሲንጋፖር)

15. ሊቀ ጳጳስ አድልቤርቶ ማርቲኔዝ ፍሎሬስ - የአሱንቺዮን የሜትሮፖሊታን ሊቀ ጳጳስ (ፓራጓይ)

16. ሊቀ ጳጳስ ጆርጆ ማሬንጎ፤ የኡላንባታር ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ (ሞንጎሊያ)

17. ሊቀ ጳጳስ ጆርጅ ኤንሪኬ ጂሜኔዝ ካርቫጃል - የካርቴጅና ሊቀ ጳጳስ ኤመሪተስ (ኮሎምቢያ)

18. ጳጳስ ሉካስ ቫን ሎይ፤ - የጄንት ኤጲስ ቆጶስ (ቤልጂየም)

19. ሊቀ ጳጳስ አሪጎ ሚግሊዮ - የካሊያሪ ሊቀ ጳጳስ (ጣሊያን)

20. አባ ጃንፍራንኮ ጊሪላንዳ፣ የነገረ መለኮት ፕሮፌሰር

21. አቡነ ፎርቱናቶ ፍሬዛ - የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ዋና አስተዳዳሪ መሆናቸው ተገልጿል።

30 May 2022, 14:13