ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ክርስቶስ በዓለም ላይ ሰላምን የሚያመጣው በየዋህነትና በገርነት ነው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሚያዝያ 05/2014 ዓ.ም ባደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ክርስቶስ በዓለም ላይ ሰላምን የሚያመጣው በየዋህነትና በገርነት ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።የተወደዳቸውሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ።

የኦሳዕናን በዓል ባለፈው ሳምንት እሁድ ቀን ካከበርን በኋላ (የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበርሰቦች ዘንደ የተከበረውን ማለት ነው) እስከ የትንሳኤ እሑድ በሚዘልቀው የሕማማት ሳምንት እኩሌታ ላይ ዛሬ እንገኛለን። እነዚህ ሁለቱም እሑዶች ተለይተው የሚታወቁት በኢየሱስ ዙሪያ በሚከበረው በዓል በመሆናቸው የተነሳ ነው። ግን ሁለት የተለያዩ በዓላት ናቸው።

ባለፈው እሑድ ክርስቶስ በታላቅ ክብር ወደ እየሩሳሌም ሲገባ አይተናል፣ ለበዓል በሚሆን መልኩ እና እንደ መሲህ አቀባበል ሲደረግለት ተመልክተናል ሰዎች እርሱ በሚሄድበት መንገድ ላይ ካባ ያነጥፉ ነበር (ሉቃ. 19፡36) እናም የወይራ ዝንጣፊዎችን በመያዝ ያሸበሽቡ ነበር (ማቴ 21፡8) በፊቱ በመሬት ላይ ያስቀምጡም ነበር።በደስታ የተሞላው ሕዝብ “የሚመጣውን ንጉሥ” እየባረኩ “በሰማያት ሰላም በአርያምም ክብር” በማለት አወድሰዋል (ሉቃስ 19:38)። በዚያ ያሉት ሰዎች የኢየሱስ ወደ እዚያው መግባት ሰላምና ክብር የሚያመጣ አዲስ ንጉሥ መምጣት እንደሆነ አድርገው ስለሚመለከቱት ያከብሩታል። ያ እነዚያ ሰዎች የሚጠብቁት ሰላም ነበር፣ የከበረ ሰላም፣ የንጉሣዊው ጣልቃገብነት ፍሬ፣ ኢየሩሳሌምን ከሮማውያን ወረራ ነጻ የሚያወጣ የኃያሉ መሲህ ፍሬ። ሌሎች ምናልባት የማህበራዊ ሰላም ዳግም መመስረትን አልመው ኢየሱስን እንደ አንድ ጥሩ ንጉስ ያዩት ነበር፣ እሱ አስቀድሞ እንዳደረገው ህዝቡን በእንጀራ ይመግባል፣ እናም ታላላቅ ተአምራትን ያደርጋል፣ በዚህም የበለጠ ፍትህን ወደ አለም ያመጣል።

ኢየሱስ ግን ስለዚህ ጉዳይ ፈጽሞ አልተናገረም። ከፊት ለፊቱ ያለው የተለየ ፋሲካ እንጂ የድል ፋሲካ አይደለም። ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት በሚደረገው ዝግጅት ላይ ያሳሰበው ብቸኛው ነገር “የታሰረ ውርንጭላ ማንም ገና ያልተቀመጠበት” (ቁ. 30) ላይ መቀመጥ ነው። ክርስቶስ በዓለም ላይ ሰላምን የሚያመጣው በየዋህነትና በገርነት ነው፤ በዚያ በተጠረጠረው ውርንጭላ ተመስሎአል፤ ማንም ባልተቀመጠበት ውርንጭላ ላይ ይቀመጣል። ማንም የለም፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር አሰራር ከዓለም የተለየ ነው። በእርግጥም፣ ከፋሲካ በፊት ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “ሰላምን እተውላችኋለሁ። ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፣ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ ዓይነት ሰላም አይደለም” (ዮሐ 14፡27) ብሎ ነበር። እነሱ ሁለት የተለያዩ አካሄዶች ናቸው፡ አለም ሰላምን የሚሰጥበት እና እግዚአብሔር ሰላምን የሚሰጥበት መንገድ የተለያዩ ናቸው።

ኢየሱስ በፋሲካ የሰጠን ሰላም በጉልበት፣ በድል አድራጊነት እና በልዩ ልዩ ጫናዎች እንደሚያገኘው የሚያምን የአለምን ስትራቴጂዎች የሚከተል ሰላም አይደለም። ይህ ሰላም እንደ እውነቱ ከሆነ፣ በጦርነቶች መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ብቻ ነው፡ ይህንን በሚገባ እናውቃለን። የጌታ ሰላም በየዋህነት እና የመስቀል መንገድ የሚከተል የሰላም ዓይነት ነው። ለሌሎች ሀላፊነት መውሰድን ያካትታል። በእርግጥም ክርስቶስ ክፋታችንን፣ኃጢአታችንን እና ሞታችንን በራሱ ላይ ተሸከመ። ይህንን ሁሉ ለራሱ ወሰደ። በዚህ መንገድ ነፃ አወጣን። ከፈለልን። ሰላሙ የአንዳንድ ስምምነት ፍሬ ሳይሆን ራስን ከመስጠት የተወለደ ነው። ይህን የዋህ እና ደፋር ሰላም ለመቀበል ግን ከባድ ነው። ኢየሱስን ከፍ ያደረጉ ሰዎች ከጥቂት ቀናት በኋላ “ስቀለው!” እያሉ የሚጮሁበት ተመሳሳይ መንገድ ይፈጠራል። እናም በፍርሃት እና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ለእርሱ ጠበቃ ሊሆኑ አይችሉም።

በዚህ ረገድ፣ የግራንድ ኢንኩዊዚተር አፈ ታሪክ ተብሎ የሚጠራው በዶስቶየቭስኪ ታላቅ ታሪክ ሁል ጊዜ ጠቃሚ ነው። ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ወደ ምድር ስለተመለሰው ኢየሱስ ይናገራል። ወድያውኑ የሚያውቀው እና የሚያመሰግነው በደስታ የተሞላው ህዝብ አቀባበል ተደረገለት። “አህ ተመለስክ! ና፣ ከእኛ ጋር ና!" ነገር ግን ከዚያ በኋላ ዓለማዊ አመክንዮ በሚወክለው ሐይማኖተኛ ፈራጅ ይያዛል። የኋለኛው ሰው ይጠይቀዋል እናም አጥብቆ ይወቅሰዋል። የተግሣጽ የመጨረሻው ምክንያት ክርስቶስ ምንም እንኳን ቢችልም የዚህ ዓለም ታላቅ ንጉሥ ቄሳር ለመሆን ፈጽሞ አልፈለገም፣ የሰውን ልጅ ከመግዛት እና በኃይል ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ነፃነቱን መተው መርጧል። በዓለም ላይ ሰላምን ማስፈን ይችል ነበር፣ የሰውን ነፃ ነገር ግን ስጋት ያለበትን ልብ በላዕላይ ሃይል ማስጎንበስ የሚችል ሲሆን ነገር ግን ይህንን አላደረገም፡ ነፃነታችንን አከበረ። "ዓለምን እና የቄሳርን ሐምራዊ ቀለም ወስደህ ቢሆን ኖሮ፣ ዓለም አቀፋዊውን መንግሥት በመመሥረት እና ሁለንተናዊ ሰላምን በሰጠህ ነበር" (The Brothers Karamazov, Milan 2012, 345)፣ እናም በሚገረፍበት ወቅት "የእኛን እሳቶች ሁሉ መሸከም አልነበረበትም” በማለት ይደመድማል። በታሪክ ውስጥ የተደጋገመው ማታለል፣ በስልጣን ላይ የተመሰረተ የውሸት ሰላም ፈተና፣ ከዚያም ወደ ጥላቻ እና እግዚአብሔርን መክዳት እና በነፍስ ውስጥ ብዙ ምሬትን ያስከትላል።

በመጨረሻ፣ በታሪኩ መሠረት የሐይማኖት መሪ ፈራጁ “ምንም መራራና አስፈሪ ቢሆንም [ኢየሱስን] ሊናገር ጓጉቷል። ነገር ግን ኢየሱስ በየዋህነት እና በተጨባጭ ምልክቶች ምላሽ ሰጠ፡- “ድንገት በዝምታ ወደ ሽማግሌው ሰው ቀረበ እና ያለ ደም ያረጁ ከንፈሮቹን በቀስታ ሳመው።”

የኢየሱስ ሰላም ሌሎችን በጭራሽ አይጫንም፣ እሱ ትጥቅ የታጠቀ ሰላም አይደለም ፣ በጭራሽ! የወንጌል መሳሪያዎች ጸሎት፣ ርኅራኄ፣ ይቅርታ እና በነጻነት ለባልንጀራ የተሰጠ ፍቅር፣ ለእያንዳንዱ ጎረቤት ፍቅር ናቸው። የእግዚአብሔር ሰላም ወደ ዓለም የመጣው በዚህ መንገድ ነው። ለዚህም ነው በእነዚህ ቀናት የታጠቁት ወረራዎች፣ ልክ እንደ ማንኛውም ጦርነት፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ቁጣ፣ የፋሲካን ጌታ ስድብ፣ የዚህ ዓለም የሐሰት አምላክ ፊት ከየዋህነቱ መመረጥን የሚወክለው። ጦርነት ሁል ጊዜ የሰው ልጅ ድርጊት ነው፣ የኃይል ጣዖት አምልኮን ያመጣል።

ኢየሱስ ከመጨረሻው ፋሲካ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሏቸዋል፡- “ልባችሁ አይታወክ አይፍራም” (ዮሐ 14፡27)። አዎን ምክንያቱም ዓለማዊ ኃያል መንግሥት ጥፋትንና ሞትን ብቻ የሚተወው ቢሆንም – ይህን በቅርብ ቀናት አይተናል – ሰላሙ ከሚቀበለን ሰው ሁሉ ልብ ጀምሮ ታሪክን ይገነባል። ስለዚህም ፋሲካ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ራሱን አሳልፎ በመስጠት ያገኘው ሰላም ለእኛ ተከፍሏልና እውነተኛ የእግዚአብሔርና የሰው ልጆች በዓል ነው። ስለዚህ ከሙታን የተነሣው ክርስቶስ፣ በትንሣኤ ቀን፣ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦላቸዋል፣ እናም እንዴት ነበር ሰላምታ ያቀረበላቸው? "ሰላም ለእናንተ ይሁን!" ( ዮሐንስ 20፡19-21 ) በማለት ነበር። ይህ የክርስቶስ የድል አድራጊነት፣ የተነሣው ክርስቶስ ሰላምታ ነው።

ወንድሞች፣ እህቶች፣ ፋሲካ ማለት “መተላለፊያ” ማለት ነው። ዘንድሮም ከዓለማዊው አምላክ ወደ ክርስቲያን አምላክ፣ በውስጣችን ከምንሸከመው ስግብግብነት ወደ ነፃነት የሚያወጣን በጎ ተግባር፣ በኃይል የሚመጣን ሰላም በመጠበቅ ወደ ቁርጠኝነት እንድንሸጋገር የሚያስችል የተባረከ አጋጣሚ ነው። ስለ ኢየሱስ ሰላም እውነተኛነት መመስከር ተገቢ ነው። ወንድሞች እና እህቶች፣ የሰላማችን ምንጭ በሆነው በተሰቀለው ፊት ራሳችንን እናቅርብ፣ እናም የልብ ሰላም እና የአለም ሰላም እንዲሰጠን እንጠይቀው።

13 April 2022, 13:13