ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማልታ ወደ ሮም በረራ ባደረጉበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላችው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማልታ ወደ ሮም በረራ ባደረጉበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላችው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከስህተቶቻችን በፍፁም አንማርም፤ ጦርነትና የቃየን መንፈስ እንወዳለን ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 24 እና 25/2014 ዓ.ም 36ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት በማልታ ካከናወኑ በኋላ ከማልታ ወደ ሮም ባደረጉት አጭር በረራ በዩክሬን ስላለው ጦርነት እና ወደ ኪየቭ የመጓዝ እድልን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እኛ "በፍፁም አንማርም። ጌታ ለሁላችን ምሕረቱን ይስጠን፣ እያንዳንዳችን በደለኛ ነን!" በማለት አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማልታ ተነስተው ወደ ሮም የመልስ ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በአይሮፕላን ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በደሴቲቱ የተደረገላቸው አቀባበል ያስደነቃቸውን በማስታወስ በዩክሬን ስላለው ጦርነት መናገራቸው ተገልጿል።

ጥያቄ፡ በማልታ ስለተገኙ እናመሰግናለን። የእኔ ጥያቄ ዛሬ ጠዋት በፀሎት ስፍራ ስላስገረመኝ ነገር ነው። ቅዱስ ጆርጅ ፕሪካ ተቀብሯል... ይህን ማልታውያንን ለማስደነቅ ያነሳሳዎ ነገር ምንድን ነው፣ እናም ስለዚህ የማልታ ጉብኝት ምን ያስታውሳሉ? እናም ጤናዎ እንዴት ነው? በዚህ ከባድ ጉዞ ውስጥ አይተናል። ጤንነቶ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ማለት እንችላለን። በጣም አመሰግናለሁ።

መልስ፡ ጤንነቴ ትንሽ ተለዋዋጭ ነው፣ ይህ በጉልበቴ ላይ ችግር አጋጥሞኛል፣ መሄድ፣ በእግር መሄድ ላይ ችግር ይፈጥራል። ትንሽ የሚያናድድ ነው፣ ግን እየተሻሻለ ነው፣ እናም ቢያንስ መውጣት እችላለሁ። ከሁለት ሳምንት በፊት ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር። ዘገምተኛ ነገር ነው፣ ተመልሶ እንደመጣ እናያለን። ሆኖም ጨዋታው እንዴት እንደሚጠናቀቅ ባለማወቅ በዚህ እድሜ ላይ ጥርጣሬ ይፈጠራል። መልካም እንደሚሆን ተስፋ እናድርግ።

ስለ ማልታ፡ በጉብኝቱ ደስ ብሎኛል፡ የማልታውያንን እውነታዎች አየሁ፣ በጎዞ እና በማልታ፣ በቫሌታ እና በሌሎችም ቦታዎች የህዝቡን አስደናቂ ስሜት አየሁ። በጎዳናዎች ላይ ታላቅ ጉጉት ነበር፣ በጣም ተገረምኩ። ጊዜው ግን ትንሽ አጭር ነበር።

አንድ ያየሁት ችግር የስደተኞች ችግር ነው። የስደተኞች ችግር ከባድ ነው ምክንያቱም ግሪክ፣ ቆጵሮስ፣ ማልታ፣ ጣሊያን እና ስፔን፡ ለአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ በጣም ቅርብ የሆኑ ሀገራት በመሆናቸው እዚህ ያርፋሉ፣ እዚህ ይደርሳሉ... ስደተኞች ሁል ጊዜ አቀባበል ሊደረግላቸው ይገባል! ችግሩ እያንዳንዱ መንግሥት እዚያ ለመኖር ምን ያህል በመደበኛነት መቀበል እንደሚችሉ መናገር አለበት። ይህ በአውሮፓ ሀገራት መካከል ስምምነትን የሚፈልግ ሲሆን ሁሉም ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም። አውሮፓ በስደተኞች መሰራቷን ዘንግተናል አይደል? ግን ነገሩ እንደዛ ነው ግን ቢያንስ ሸክሙን ሁሉ ለእነዚህ ለጋስ ለሆኑ ጎረቤት ሀገራት እንተወውና ማልታ የዚህ አንዷ ሰለባ ናት።

ዛሬ በስደተኞች መቀበያ ማእከል ውስጥ ነበርኩ እና እዚያ የሰማኋቸው ነገሮች አስከፊ ናቸው፣ እነዚህ ሰዎች ወደዚህ ለመድረስ ያሳለፉትን ስቃይ ... እና በካምፖች፣ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ላይ፣ ወደ ኋላ ሲመለሱ የሚያጋጥማቸውን ብዙ ነገሮች ሰምቻለሁ። ይህ አደገኛ ነገር ይመስላል አይደል? ለዚህም ይመስለኛል የሁሉንም ሰው ልብ የሚነካ ችግር ነው የምንለው። አውሮፓ በሩን ለሚያንኳኩ ዩክሬናውያን በልግስና ቦታ እየሰጠች እንዳለች ሁሉ ከሜዲትራኒያን ባህር ለሚወጡት ሌሎችም እንዲሁ ማድርግ ይኖርባታል።

ይህ ጉብኝቱን የጨረስኩበት ነጥብ ነው፣ እናም በጣም ነክቶኛል ምክንያቱም ምስክርነቱን፣ ስቃዮቹን እና ከዛ ትንሽ መጽሃፍ በወጣችው "ሄርማኒቶ" ውስጥ እንዳሉ የነገርኳችሁ ብዙ ወይም ትንሽ ናቸው ብዬ ስለሰማሁ ነው በስፓኒሽ "ታናሽ ወንድም" ማለት ነው፣ እናም የእነዚህ ሰዎች የመስቀል መንገድ የሁሉንም ልብ ይነካል።  ከተናገሩት ሰዎች መካከል አንዱ ሲናገር ወደ እዚያ ሥፍራ ለመድረስ አራት ጊዜ መክፈል ነበረበት! ስለዚህ ጉዳይ እንድታስቡ እጠይቃችኋለሁ። አመሰግናለሁ።

ጥያቄ፣ ወደ ማልታ በምንጓዝበት ወቅት በነበረን በረራ ላይ፣ ወደ ኪየቭ የሚደረግ ጉዞ "በጠረጴዛው ላይ እንዳለ" ለአንድ የስራ ባልደረባዬ ነግረውት ነበር። በማልታ ሳሉ ከዩክሬን ህዝብ ጋር ያለዎትን ቅርበት ጠቅሰዋል፣ እናም አርብ በሮም የተገኙት የፖላንድ ፕሬዝዳንት ወደ ፖላንድ ድንበር ጉብኝት ለማድረግ በሩን ከፍተዋል። ዛሬ ዩክሬናውያን በደርዘን የሚቆጠሩ አስከሬኖችን በጎዳናዎች ላይ ሲያዩ በኪየቭ አቅራቢያ ከምትገኝ ከቡቻ መንደር የሚመጡ ምስሎች አሳይተውናል። ዛሬ በዚያ መገኘትዎ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊ የሆነ ይመስላል። እንደዚህ ዓይነት ጉዞ ማድረግ የሚቻል ይመስልዎታል? እናም ወደዚያ መሄድ እንድችሉ ምን ሁኔታዎች ሊኖሩዎት ይገባል?

መልስ፡ እስካሁን የማላውቀውን የዛሬውን ዜና ስላስተላለፍክልኝ አመሰግናለሁ። ጦርነት ምንጊዜም የጭካኔ ድርጊት ነው፣ ኢሰብአዊ ነገር ነው፣ ይህም ከሰው መንፈስ በተቃራኒ የሚገኝ ጉዳይ ነው፣ ክርስቲያን ሳይሆን ያልኩት ሰው ነው ብዬ የተናገርኩት። የቃየን መንፈስ ነው፣ “የቃይኒስት” መንፈስ... መደረግ ያለበትን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ፣ እናም ቅድስት መንበር፣ በተለይም የዲፕሎማሲው ወገን፣ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፣ እና ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ሁሉንም ነገር እያደረጉ ነው። ለጥንቃቄ እና ምስጢራዊነት የሚያደርጉትን ሁሉ ለህዝብ ይፋ ማድረግ አንችልም ነገር ግን የስራችንን ወሰን እየገፋን ነው።

ሊሆኑ ከሚችሉት መካከል ጉዞው አንዱ ነው፣ ሁለት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዞዎች አሉ፣ የፖላንድ ፕሬዝዳንት በፖላንድ የተቀበሉትን ዩክሬናውያንን ለመጎብኘት ካርዲናል ክራጄቭስኪን እንድልክ ሲጠይቁኝ አንድ ጉዞ አሰብኩኝ። እሱ ቀድሞውኑ ሁለት ጊዜ ሄደው ነበር - ሁለት አምቡላንስ ይዞ ሄዷል፣ እናም ለተወሰነ ጊዜ ከእነሱ ጋር ነበር ፣ እናም እንደገና ተመልሶ ይሄዳል ። ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ነው።

ሌላው አማራጭ አንዳንዶቻችሁ የጠየቃችሁት ጉዞ ነው፣ ልሄድ እንዳቀድኩኝ፣ መገኘቴ የማያቋርጥ መሆኑን በቅንነት መለስኩለት። እንደዚህ አይነት ጉዞን በተመለከተ ሃሳቤ ምንድን ነው? ይህ ጥያቄ ነበር፣ "ወደ ዩክሬን ጉዞ እያሰቡ እንደሆነ ሰምተናል"፣ ይህ የእኔ ሐሳብ ጠረጴዛው ላይ አለ፣ እዚያ አለ፣ ከተቀበልኩት ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ነው፣ ግን ተስማሚ ከሆነ ማድረግ ይቻል እንደሆነ አላውቅም፣ እናም ለበጎ እንደሆነ ወይም እሱን ለመስራት ተገቢ ከሆነ፣ መሄድ እንዳለብኝ አላውቅም… ይህ ሁሉ በአየር ላይ ነው።

ለተወሰነ ጊዜ ከፓትርያርክ ኪሪል ጋር የተደረገውን ስብሰባ በተመለከተ ግምት ውስጥ ገብተዋል፣ ለዚህም ነው እየተሰራ ያለው፣ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለእንደዚህ ዓይነቱ ስብሰባ ቦታ ሊሆን ይችላል። በአሁን ሰአት ነገሮች እየታሰቡ ያሉት በዚህ መልኩ ነው።

ጥያቄ፡ በዚህ ጉዞ ውስጥ ብዙ ጊዜ ስለ ጦርነቱ ተናግረዋል። ሁሉም ሰው የሚጠይቀው ጥያቄ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ተነጋግረዋል ወይ ካልሆነ ዛሬ ምን ይሉታል?

መልስ፡ በሁሉም በኩል ላሉ ባለስልጣናት የነገርኳቸው ነገሮች ይፋዊ ናቸው። ከተናገርኳቸው ነገሮች ውስጥ አንዳቸውም ሚስጥራዊ አይደሉም። ፓትርያርኩን ባነጋገርኳቸው ጊዜ እርስ በርሳችን የተነጋገርነውን ጥሩ መግለጫ አውጥተዋል።

መልካም ልደት እዲሆንልኝ ለመመኘት በደወሉልኝ ወቅት ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ የሩሲያ ፕሬዝዳንትን አነጋገሪያቸው ነበር። ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ጋር ሁለት ጊዜ ተነጋግሬአለሁ። ከዚያም በጦርነቱ የመጀመሪያ ቀን ወደ ሩሲያ ኤምባሲ ሄጄ የሕዝቡ ተወካይ የሆኑትን አምባሳደር ለማነጋገር እና ስለ ሁኔታው ​​ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ግንዛዬን ለማቅረብ እንዳለብኝ ተሰማኝ። እነዚህ ያደረግኳቸው ኦፊሴላዊ ግንኙነቶች ናቸው። ከሩሲያ ጋር በኤምባሲው በኩል እየተናገርን ነው።

እንዲሁም፣ የኪየቭ ሼቭቹክን ዋና ሊቀ ጳጳስ አነጋግሬአለሁ። እንዲሁም በየሁለት ወይም ሶስት ቀኑ—ከናንተ አንዱ ኤሊዛቤትታ ፒኩዬ በሊቪቭ ከነበረች እና አሁን በኦዴሳ ከምትገኝ ጋር በመደበኛነት ተናግሬአለሁ። ነገሮች እንዴት እንደሆኑ ትነግረኛለች። ከዘረዓ ክህነት ዋና ዳይሬክተር ጋርም ተነጋግሬአለሁ። ነገር ግን እንዳልኩት፣ እኔም ከእናንተ ከአንዱ ጋር ግንኙነት አለኝ።

ስለዚያ ስናገር ለወደቁት ባልደረቦቻችሁ መፅናናትን እመኛለሁ። ከየትኛውም ወገን ቢሆኑ ምንም ለውጥ አያመጣም። ነገር ግን የእናንተ ስራ የጋራ ጥቅምን ወክሎ ነው፣ እናም እነሱ በመረጃ ስም፣ ለጋራ ጥቅም አገልግሎት ወድቀዋል። አንርሳቸው። ደፋር ነበሩ፣ እናም ጌታ ለስራቸው ዋጋ እንዲሰጣቸው እጸልያለሁ። እስካሁን ያደረግኳቸው እነዚህ ግንኙነቶች ናቸው።

ጥያቄ፡ ከእርሳቸው ማለትም ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመነጋገር እድሉን ቢያጉኙ ለፑቲን መልእክቶ ምን ሆን?

መልስ፡ ለሁሉም ባለስልጣናት ያስተላለፍኳቸው መልእክቶች በአደባባይ ያደረኳቸው ናቸው። ድርብ ንግግር አላደርግም። እኔ ሁልጊዜ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ እናገራለሁ።

በጥያቄዎ ውስጥ ስለ ፍትሃዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ጦርነቶች ጥርጣሬም ያለ ይመስለኛል። እያንዳንዱ ጦርነት ከፍትሕ መጓደል የሚመነጭ ነው፣ ምክንያቱም ይህ የጦርነት ምሳሌ ነው። ይህ የሰላም ምሳሌ አይደለም። ለምሳሌ የጦር መሳሪያ ለመግዛት መዋለ ነዋይ ማፍሰስ መጀመርን ያጠቃልላል። አንዳንድ ሰዎች ‘እኛ ግን ራሳችንን እንድንከላከል እንፈልጋለን’ ይላሉ። ይህ የጦርነት ምሳሌ ነው። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ ሁሉም ሰው "በፍፁም ጦርነት" አያስፈልግም ብሎ ሰላም ተነፈሰ። የጦር መሳሪያ፣ አቶሚክ የጦር መሳሪያ አለማምረት በጎ ፈቃድ ታየ፣ ሰላምን ወክሎ ከሄሮሺማ እና ናጋሳኪ በኋላ የሰላም ስራ ማዕበል ተጀመረ። ታላቅ በጎ ፈቃድ ነበር።

ከሰባ አመት በኋላ ያን ሁሉ ረሳነው። የጦርነት ዘይቤ እራሱን የሚጭነው በዚህ መንገድ ነው። ያኔ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስራ ላይ ብዙ ተስፋ ነበረ። ነገር ግን የጦርነት ዘይቤ እራሱን እንደገና አስገብቷል። ሌላ ንድፍ መገመት አንችልም። ከአሁን በኋላ የሰላምን ምሳሌ ማሰብ አልለመድንም። እንደ ጋንዲ እና ሌሎችም የምጠቅሳቸው በፍሬተሊ ቱቲ በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት መጨረሻ ላይ የሰላምን ዘይቤ የተከራከሩ ታላላቅ ሰዎች ነበሩ።

እንደ ሰው ግን ግትር ነን። ከጦርነት፣ ከቃየል መንፈስ ጋር እንዋደዳለን። በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ ክፍል ላይ ይህ ችግር የቀረበው በአጋጣሚ አይደለም፡ ከሰላም መንፈስ ይልቅ "የቃይኒዝም" የመግደል መንፈስ ነው።

አንድ የግል ነገር እነግራችኋለሁ፡ እ.አ.አ በ2014 ዓ.ም ሬዲፑሊያ (በጣሊያን አገር የሚገኝ ሥፍራ ነው) እያለሁ የሟቾችን ስም ሳይ፣ አለቀስኩ። በእውነት ከመራራነቱ የተነሣ አለቀስኩ። ከዚያም ከአንድ ወይም ከሁለት ዓመት በኋላ የሙታን ቀን በአንዚዮ ለማክበር ሄጄ በዚያ የወደቁትን ሰዎች ስም አየሁ። ሁሉም ወጣቶች ነበሩ፣ እኔም እዚያ አለቀስኩ። በመቃብር ላይ ማልቀስ አለብን።

የፖለቲካ ችግር ስላለ አንድ የማከብረው ነገር አለ። የኖርማንዲ ማረፊያዎች መታሰቢያ ሲከበር፤ በርካታ የመንግስት መሪዎች በጋራ ለማክበር ተሰበሰቡ። ይሁን እንጂ በባህር ዳርቻዎች ላይ ስለተረፉት 30,000 ወጣት ልጆች ማንም ሲናገር አላስታውስም። ወጣትነት ምንም አይደለም። ያ እንድገረም አድርጎኛል። አዝኛለሁ። መቼም አንማርም። ጌታ ምህረቱን ያውርድልን ለሁላችንም። እያንዳንዳችን ጥፋተኛ ነን!

03 April 2022, 11:44