ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ወደ ማልታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ወደ ማልታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ለ36ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማልታ ገብተዋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዳሜ መጋቢት 24/2014 ዓ. ም. ጠዋት ረፋዱ ላይ በማልታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከአገሪቱ ፕሬዚደንት ከሆኑት ክቡር አቶ ጆርግ ዊሊያም ቬላ እና ከባለቤታቸው፣ ከብጹዓን ጳጳሳት እና እንዲሁም ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ቅዱስነታቸው ቀጥለውም በቫሌታ በሚገኝ ግራንድ ማስተር ቤተ መንግሥት ያመሩ ሲሆን በሥፍራው ሲደርሱ ለአገሪቱ ፕሬዚደንት፣ ለከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች፣ ለዲፕሎማቶች፣ ለልዩ ልዩ የሐይማኖት ተወካዮች፣ ለሲቪል ባለሥልጣናት፣ ለማኅበራዊ እና ባሕላዊ ሕይወት ተወካዮች በሙሉ ንግግር አድርገውላቸዋል።

በቫሌታ በሚገኝ ግራንድ ማስተር ቤተ መንግሥት የተገነባው እ. አ. አ በ1571 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ በመካከለኛው ዘመን ከፍ ያለ ጀብዱ ለፈጸመ የሚሰጥ የወታደር ክብር ማዕረግ የነበራቸው የመስቀል ተዋጊዎች በታላቁ ሊቅ እና መምህር በቅዱስ ዮሐንስ መቀመጫ በሆነው ቦታ ላይ የተገነባ ሕንጻ ሲሆን፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የማልታ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊልያም ቬላን እና ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላን ጋር ተገናኝተዋል።

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ወደ ማልታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ
02 April 2022, 18:16