ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ‘በወንድም ላይ የተነሳውን የወንድም እጅ እባካችሁን አንሱ’ ማለታቸው ተገለጸ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በሚያዝያ 07/2014 ዓ.ም የስቅለተ አረብ በዓል በጸሎት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። በዚህ በሮም ከተማ ኮሌሴዮም በሚባልበት ሥፍራ ምሽት ላይ በተደረገው የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተሳትፈው የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያ በመገኘት የመስቀል መንገድ ጸሎት እንደ መሩም ተገልጿል።

የዘንድሮ የመስቀል መንገድ ጸሎት የተዘጋጀው ከተለያዩ ሕብረተሰቦች በተውጣጡ ምዕመናን ሲሆን በዚህ መሰረት ቤተሰቦች በራሳቸው የስቃይ እና የተስፋ ልምዳቸው ላይ በመመሥረት ለእያንዳንዱ 14 የመስቀል መንገድ ጽሎት ላይ አስተንትኖ አድርገዋል።

ባህላዊው እና ከፍተኛ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው ይህ የመስቀል መንገድ ጽሎት በስቅለተ ዓርብ ምሽት በሮም ከተማ በሚገኘው ኮሌሴዮም በመባል በሚታወቅ ሥፍራ ተባልበት ሥፍራ እንደ ተከናወነ የተገለጸ ሲሆን ይህ የመስቀል መንገድ ጽሎት በዚህ በስቅለተ አረብ ቀን በኮሌሴዮም መከበር የጀመረው እ.አ.አ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ከእዚያም በኋላ ለጥቂት አመታት ያህል በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ከተቋረጠ በኋላ በአዲስ መልክ በስፍራ መከበር ጀምሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኢየሱስን ህማማት እና ሞት ክስተቶችን ላማክበር እና የመስቀል መንገድ ጽሎት ከ 10,000 በላይ ምዕመናን በተገኙበት ዝግጅቱን መርተዋል ።

በኮሎሲየም የሚከበረው የመስቀል መንገድ ጽሎት ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የተጀመረ ቢሆንም፣ በዘመናችን ወግ በአዲስ መልክ የተጀመረው እ.አ.አ በ1964 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ዝግጅቱን ሲመሩ ነበር።  

የመስቀሉ መንገድ ጽሎት የተጀመረው “እናመልክሃለን” በሚል መዝሙር ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል በክርስቶስ ስቃይ እና መስቀል ውስጥ የተደበቀውን ኃይል፣ እንዲሁም በፈተናዎች መካከል የሚገኙትን በርካታ የቤተሰብ ህይወት እና የተስፋ ገጽታዎችን ወደ አእምሯቸው የሚያመጣ የመክፈቻ ጸሎት አነበቡ።

ከሙታን የተነሣው ኢየሱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጸሎታቸው እንደገለጹት ከሆነ  ለሰው ልጅ የመዳንን ስጦታ አቅርቧል እናም እንባዎችን ሁሉ ለማድረቅ እና ሁሉንም ህዝቦች ወደ “በፍቅር እና በሰላም ወደ ተገነባው ቤትህ ታላቅ ቤተሰብ” ውስጥ ለመኖር እንኳን መጣችሁ በማለት ስላሙን እንደሚሰጠን ኢየሱስ ቃል ገብቶልናል ብለዋል።

የወንጌል ክፍል ሲታወጅ እና በእያንዳንዱ የመስቀል መንገድ ጽሎት ዙሪያ ላይ አስተንትኖ ሲደረግ እያንዳንዳቸው አስራ አራቱ ማረፊያዎች ሲከበሩ የተለያዩ ቤተሰብ መስቀሉን ሲሸከሙ ታይተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እያንዳንዱን ማረፍያ በጸሎት አጠናቅቀዋል።

በጦርነት ተቃራኒ ወገን የሚገኙ ሁለት ቤተሰቦች

የመስቀል መንገድ ጽሎት ላይ በዚህ አመት የተቀመጠው አስተንትኖ የተፃፈው በአሥራ አምስት ቤተሰቦች ሲሆን ከካቶሊክ በጎ ፈቃደኞች ቡድኖች ጋር በተቆራኙ እና በአለም ዙሪያ ያሉ ቤተሰቦች የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች እና መከራዎች የተለያዩ ገፅታዎችን ዳስሷል።

የአስተንትኖ መደምደሚያው በ13 ኛው ማረፊያ ላይ ሁለት ሴቶች መስቀሉን አንድ ላይ ተሸክመው ሲመለከቱ አልቢና ከተባላችው ከሩሲያ እና ኢሪና ከተባለችው ከዩክሬን የመጡ ናቸው ።

ከተዘጋጀው አስተንትኖ ይልቅ ዝምታ ከማንኛውም ቃል በላይ ጮኸ።

ሁለቱ ሴቶች - ጓደኛሞች እና ሁለቱም በሮማ ከተማ የሚሰሩ ነርሶች ናቸው - መስቀሉን ይዘው እርስ በእርሳቸው ዓይን ውስጥ በጨረፍታ ሲመለከቱ በጦርነት ውስጥ ያሉ ወንድሞችን ስቃይ እና የማይጠፋውን የሰላምና የዕርቅ ተስፋ የሚገልጽ ይመስላል።

የአፍታ ጸጥታ ታየ እና ሁሉም የእግዚአብሔርን የሰላም ስጦታ ለማግኘት ጸለዩ።

በመከራ ጨለማ ውስጥ የወንጌል ብርሃን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እያንዳንዱ ምዕመናን የቤተሰባቸውን ግላዊ ልምድ ለራሳቸው እንዲናገሩ በመፍቀድ በመስቀል መንገድ ጽሎት ላይ  ምንም አይነት ስብከት ወይም አስተያየት አልሰጡም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዝግጅቱ የመጨረሻ ጸሎታቸው ላይ የወንጌል ብርሃን በሁሉም ቤተሰቦች ልብ ውስጥ በደስታ እና በሀዘን ፣ በፈተና እና በተስፋዎች ውስጥ እንዲበራ ጸልየዋል።

እናም እኛን ከእግዚአብሔር የሚያርቁንን "ዓመፀኛ ልባችንን" ይቅርታ እና ሰላም እንዲያሸንፈው እግዚአብሔርን በጸሎታቸው ጠይቀዋል።

“ጌታ ሆይ፣ የሰላምን ዕቅድ እንድንከተል እንድንማር፣ ዓመፀኛውን ልባችንን ወደ ልብህ መልሰው። ጠላቶች እጅ እንዲጨባበጡ እና የጋራ ይቅር ባይነትን እንዲቀምሱ አነሳሳ። ጥላቻ ባለበት መግባባት እንዲያብብ በወንድም ላይ የተነሳውን የወንድም እጅ ትጥቅ በመፍታት እንዲቆም አድርግ። ከትንሣኤው ክብር እንድንካፈል ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶች እንዳንሆን ፀጋህን ስጠን። አሜን”

15 April 2022, 14:45