ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የዓለም የወጣቶች ቀን አዘጋጆች ቅድመ ዝግጅቱን በብራታ ማከናወን ቀጥሉ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በመጪው አመት 2023 ዓ.ም በፖርቱጋል ዋና ከተማ በሊዝበን ለሚከበረው የአለም ወጣቶች ቀን አዘጋጅ ወጣቶች የቪዲዮ መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ይህም አዲስ፣ ህይወት ያለው እና እምነትን የሚያጠናክር ተሞክሮ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁሉንም የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ ማበረታታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ ከነሐሴ 1 እስከ 6/2023 ዓ.ም በሊዝበን፣ ፖርቱጋል ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም ወጣቶች ቀን ዝግጅት ላይ ለተሳተፉ ወጣቶች በስፓኒሽ ቋንቋ የቪዲዮ መልእክት ልከዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ወጣቶችን ለበዓሉ አከባበር ከዓለም ዙሪያ በመሰብሰብ ለዓለም አቀፍ በዓላት እንደሚያደርጉት ሁሉ በጉጉት እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።

ወጣቶችን ዋና ገጸ ባህሪያት ለማድረግ ለሚሰሩ ሰዎች ዋና ፈተና ነው።

ተስፋን ሰንቁ፣ የፈጠራ ችሎታችሁን አዳብሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዛሬ የምንኖርበትን አስቸጋሪ አውድ አምነዋል፣ ከወረርሽኙ ቀውስ ወጥተን አሁን አዲስ የጦርነት ቀውስ ገጥሞናል በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህ ታላቅ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ በጎ ፈቃደኞች የዓለም የወጣቶች ቀን እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ሲከበር የወጣት፣ አስደሳች፣ ሕያው እና ለሁሉም የማይረሳ ተሞክሮ እንዲሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነት የሚያመጣውን አስደሳች ተስፋ እንዲያረጋግጥ ሁሉም የፈጠራ ኃይላቸውን እንዲጠቀሙ አበረታቷቸዋል።

የዓለም የወጣቶች ቀን እንደ ባለፉት ጊዜያት ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን በማድረግ ብቻ እንዲከናወን ማድረግ ሳይሆን ነገር ግን እንደ ግጥም ገጣሚዎች የሚታወስ አዲስ ልምድ እንዲያልሙም ጥሪ አቅርበዋል። ሁሉም ሰው ለእዚህ ማዋጣት ይችላል፣ አይዞዋችሁ ወደ ፊት ለመሄድ ሞክሩ በማለት ቅዱስነታቸው መናገራቸው ተገልጿል።

ቀውሶች አብረው ይሸጋገራሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዛሬ ዓለም የሚያጋጥሟቸውን ቀውሶች እንዴት መፍታት እንደምንችል እና ከእምነት በሚመነጨው የተስፋ ምስክርነት እንዲመለከቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ቀውሶቹ የተሻለ ስራ እንድንሰራ እና ከነሱ በተሻለ ሁኔታ እንድንወጣ እድል ይሰጡናል ሲሉ ገልፀው በዚህ ረገድ እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም ላይ የሚከበረው የዓለም የወጣቶች ቀን ወደፊት በመመልከት የፈጠራ ቅንዓታቸውን እንዲገልጹ አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጸሎታቸውን አረጋግጠው ስለ እርሳቸው እና ስለ አገልግሎታቸው ጸሎት እንዲደረግላቸው ከጠየቁ በኋላ ጌታ እንዲባርካቸው እና ድንግል ማርያም እንድትጠብቃቸው ከተማጸኑ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

09 March 2022, 11:54