ፈልግ

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የዐብይ ጾም በተጀመረበት ወቅት የዐመድ መቀበት ሥነ ስረዓት ሲያከናውኑ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የዐብይ ጾም በተጀመረበት ወቅት የዐመድ መቀበት ሥነ ስረዓት ሲያከናውኑ  (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እግዚአብሔር ብቻ የሚሰጠውን ሰላም እንማጸን ማለታቸው ተገለጸ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መዕመናን ዘንድ በየካቲት 23/2014 ዓ.ም የዐብይ ጻም መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የዐብይ ጾም አስመልክቶ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን የዐብይ ጾም ማስጀመሪያ ስነ ስረዓት በመስዋዕተ ቅዳሴ ለማስጀመር ቀድም ሲል የድርጊት መርዐ ግብር እንደ ወጣላቸው የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን ቅዱስነታቸው በድንገት በጉልበታቸው ላይ በደረሰባቸው የጤና እክል ምክንያት የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባር የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በእርሳቸው ፈንታ ዝግጅቱን መምራታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዚህም መሰረት በሮም ከተማ በሚገኘው በቅድስት ሳቢና ቤተክርስቲያን ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ተክተው ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እግዚአብሔር ብቻ ሊሰጠን በሚችለው የሰላም ዓይነት መማጸን እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን በተመሳሳይም በአሁኑ ወቅት በዩክሬይን እየተደረገ የሚገኘው ጦርነት አብቅቶ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል ብለዋል።

የቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የዓብይ ጾም መጀመሩን የሚያበስረው የአመድ መቀባት መንፈሳዊ ስነ ስረዓት በተካሄደበት ወቅት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ሰለ ሰላም መጸለይ አስፈላጊ እንደሆነ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

እ.አ.አ መጋቢት 2/2022 ዓ.ም የዐብይ ጾም መግቢያ ሲሆን ይህም የ40 ቀናት የጸሎት፣ የጾም፣ የመታቀብ እና የመልካም ሥራ ጊዜ ሲሆን ይህም የኢየሱስን ሕማማት እና ሞትን ተከትሎ ታላቁን እና ክብር የሚሰጠውን ትንሣኤን ለሚያከብረው የክርስትና እምነት ታላቅ የትንሣኤ በዓል ዝግጅት ነው። በመስቀል ምልክት በግንባር ላይ ዐመድ የመቀባት ወይም በጭንቅላቱ ላይ አመድ መነስነስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የንስሐ ምልክት ሲሆን ይህም አማኞች በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኛ መሆናቸውን እና የእነርሱን ሟችነት ያስታውሳል፣ ዐመዱን በግንባር ላይ የሚነሰንሰው ቄስ “ሰው ሆይ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ” በማለት ነው ሥነ ስርዓቱን የሚያከናውነው።

ለዩክሬን የጸሎት እና የጾም ቀን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በኩል እንዲነበብ ባደረጉት ስብከተ ወንጌል ላይ እንደ ገለጹት ጸሎት፣ ምጽዋት እና ጾም ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም “መድኃኒቶች” መሆናቸውን እና “ታሪክን ሊለውጡ ይችላሉ” እናም “ዋና መንገዶች” መሆናቸውን አስምረውበታል። እግዚአብሔር በሕይወታችን እና በአለም ውስጥ ጣልቃ እንዲገባ የምንማጸንበት መንገድ እንደ ሆነ እና እናም በዚህ የጸሎት እና የጾም ቀን ለዩክሬን "ወንዶች እና ሴቶች በራሳቸው መገንባት የማይችሉትን ሰላም ከእግዚአብሔር እንማጸናለን ብለዋል። " ጌታ እነዚህን ጸሎቶች ይስማ፣ በተለይም ከዓመፅ የሚሸሹትን ድሆች እና የሚሰቃዩ ሰዎችን፣ ጳጳሱ "በልባችን ሰላምን ይመልስልን፣ ዳግመኛም ለዘመናችን ሰላምን ይስጠን ብለዋል።

ሁለት ዓይነት ሽልማቶች

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በስብከታቸው መጀመሪያ ላይ እንዳስታወቁት በዛሬው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ በወንጌል እንደተገለጸው በሌሎች ዘንድ ለመታየት እና ለመመስገን ምግባራችንን ከመለማመድ እንጠንቀቅ በምትኩ ከአብ ዘንድ "ዘላለማዊውን" መፈለግ ይገባናል ብለዋል። እውነተኛ እና የመጨረሻው ሽልማት የሕይወታችን ዓላማ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ከሌሎች የሚሰጠው ሽልማት "ጊዜያዊ" እና ወደ ውጫዊ ነገር የሚመለከት ነው ሲሉ የገለጹ ሲሆን ለራሳችን አድናቆት እየፈለግን ይህ ደግሞ እንድንሰናከል የሚያደርገን ቅዠት ነው በማለት አክለው ገልጸዋል።

አመድ እንደ አስጨናቂ ምልክት

በጭንቅላታችን ላይ አመድ የምንቀበልበት ሥርዓት “ከአብ ከምንቀበለው ሽልማት ይልቅ ከሌሎች የተቀበልነውን ሽልማት ከማስቀደም ስህተት” እንደሚጠብቀን እና የሚረዳን “አስጨናቂ ምልክት” መሆኑን ገልጸዋል። የሰውን ልጅ ሁኔታ አላፊነት እናደንቃለን። ልክ እንደ መራራ መድሀኒት ነው፣ “የመልክን በሽታ ለመፈወስ ውጤታማ፣ እኛን ባሪያ የሚያደርግ እና በሌሎች አድናቆት ላይ ጥገኛ እንድንሆን የሚያደርግ መንፈሳዊ ህመም” ነው ሲል ተናግሯል። ኢየሱስ “ጸሎት፣ ምጽዋት እና ጾም እንኳን እራስን መግለጽ ይችላሉ” በማለት መናገሩን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብጽዕ ካርዲናል ፓሮሊን በኩል ባስተላለፉት ስብከት ገልጸዋል። በመቀጠልም  ብዙ ጊዜ የተደበቀውን እራስን መቻልን ለማሸነፍ እና የራሳችንን ግብዝነት ለመገንዘብ መጣር አለብን ሲሉ አክለው ገለጸዋል።

በዐቢይ ጾም አመድ የጸዳ

አመድ ለዓለማዊ ሽልማት ከምናደርገው ፍለጋ በስተጀርባ ያለውን “ባዶነት” ሊወክል ይችላል ሲሉ ጳጳሱ የገለጹ ሲሆን “ዓለማዊነት በትንሽ ንፋስ እንደሚወሰድ አቧራ እንደሆነ ያስታውሰናል” ብለዋል። የዐብይ ጾምን ጊዜ “ለመታደስ፣ የውስጥ ሕይወታችንን የምንከባከብበት፣ እና ወደ ፋሲካ፣ ወደማያልፈው ነገር የምንጓዝበት፣ ከአብ ልንቀበለው የሚገባንን ዋጋ የምናገኝበት ጊዜ ብናደርገው መልካም ነው” ብሏል። " ዓብይ ጾም ዕለት ዕለት "በታደሰ መንፈስ" የሚሄድ የፈውስ ጉዞ መሆኑን ጨምረው የገለጹ ሲሆን ጸሎት፣ ምጽዋትና ጾም የሂደቱ አንድ አካል ናቸው ብለዋል።

ጸሎት፤ ምጽዋት እና ጾም

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጸሎት - ድብቅ በሆነው የውስጣችን ክፍል ውስጥ "ልባችንን የሚያጽናና እና የሚያሰፋ" ሞቅ ያለ እና እምነት የሚጣልበት ውይይት በመሆኑ "ሕይወታችንን በሌሎች ቦታዎች እንዲያብብ ለማድረግ ምስጢር" እንደሚሆን አሳስበዋል። "ለእግዚአብሔር ርኅራኄ ልባችን ክፍት እንዲሆንልን የእኛንና የዓለማችንን ቁስሎች በእርሱ ቁስል ውስጥ ማኖር ተገቢ ነው" በማለት ዓይናችን የተሰቀለውን ጌታ ይመልከት ዘንድ ጋብዘዋል።

በተግባር የሚውል ጸሎት በበጎ አድራጎት ፍሬ ማፍራት አለበት ሲሉም “በዚህ አመድ የጸዳች የዓብይ ጾም ምጽዋት ወደ አስፈላጊው ነገር ይመልሰናል፣ ​​በመስጠት ወደሚገኝ ጥልቅ ደስታ ይመራናል” በማለት ተናግሯል። ምጽዋት "ከድምቀት ርቆ የሚሠራ" ልባችንን በሰላምና በተስፋ የሚሞላ ነገር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ጾም ነገሮችን ለእውነተኛ ዋጋቸው እንድናደንቅ ይረዳናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ከምግብ በተጨማሪ ሌሎች ነገሮችንም ሊያካትት እንደሚችል ጠቁመው "በውስጣችን ማንኛውንም ዓይነት ሱስ ሊፈጥር ከሚችል ከማንኛውም ነገር" እንድንጾም አደራ እላለሁ ብለዋል። ጸሎታችን፣ ምጽዋታችንና ጾማችን ያድግ ዘንድ  ለሁሉም መድኃኒት የሚሆን እና ታሪክን የሚቀይር ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው ካሉ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በኩል ያስተላለፉት ስብከት አጠናቀዋል።

02 March 2022, 13:38