ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ‘መረን የለቀቀው ዓለማችን የበለጠ ክርስቲያናዊ እና ሰብአዊ መሆን አለበት’አሉ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተሻለ ዓለም ለመገንባት የሚደረግ ንቅናቄ ማሕበር 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት እንኳን ለ70ኛው አመት የምሥረታ በዓል አደረሳችሁ የሚል መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ክርስትያኖች አለም የበለጠ ሰብአዊ እና ሰላማዊ እንዲሆን መሥራት የጠበቅብናል ብለዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
የተሻለ ዓለምን ለመገንባት የሚደረግ ንቅናቄ (በጣሊያንኛ፡ ፐር ኡን ሞንዶ ሚልዮሬ) በጣሊያን ከተመሰረተ 70ኛ አመት ሲያከብር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓሉን ምክንያት በማድረግ አጭር የቪዲዮ መልእክት ልከዋል።
ከንቅናቄው አባላት ጋር ያለውን ቅርርብ በመግለጽ ባለፉት 7 አስርት ዓመታት ላስመዘገቡት ሰፊ ስራ ቅዱስነታቸው የንቅናቄውን አባላት ያመሰገኑ ሲሆን "የሕይወት ራዕይ፣ የፍጥረት ራእይ ነበር" ብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒየስ 12ኛ እ.አ.አ የካቲት 10 ቀን 1952 ዓ.ም “የተሻለ ዓለም አዋጅ” በሚል ርዕስ በሬዲዮ ባስተላለፉት መልእክት “ለውጥ” እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ “መረን የለቀቀ” የሚል ቃል ተጠቅመው የነበረ ሲሆን ጌታ ሁል ጊዜ ለሰው ልጅ ቅርብ ስለሆነ መረን የለቀቀው ዓለም የበለጠ ሰብአዊ፣ ክርስቲያናዊ፣ ነገር ግን የበለጠ ሰላማዊ ዓለም መሆን ይኖርበታል ማለታቸው ይታወሳል።
ለሰላምና ለፍትህ የሚደረጉ ጥረቶች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የመውደቅ ፈተናዎችን በመቃወም የተሻሉ የዓለም ንቅናቄ አባላትን ወደፊት ለመሄድ እንዲጥሩ አበረታተዋል። ዓለምን ለመለወጥ መስራታቸውን እንዲቀጥሉ ጋብዘዋል ብለዋል ።
"ከሁሉም በላይ ለፍትህ፣ ለህጻናት እና ለአረጋውያን እና ለሰላም እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ። ይህ የተሻለ ዓለም ነው፣ እሱም የሰላም ዓለም እንዲሆን ነው የምንፈልገው ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የንቅናቄው አባላት ላከናወኑት ሥራ አመስግነው የዓመታዊ በዓላቸውን ቡራኬ በማድረግ የቪዲዮ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።
የተሻለ ዓለም ለመገንባት የተቋቋመው እንቅስቃሴ ታሪክ
የተሻለ ዓለም ለመገንባት የተቋቋመው ንቅናቄ የተቋቋመው የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል በሆኑት በአባ ፈረድሪኮ ሎምባርዲ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን እ.አ.አ በ1952 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ያወጡትን አዋጅ ተከትሎ የተቋቋመ ንቅናቄ ነው።
አብ ሎምባርዲ - የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዳይሬክተር እና የቫቲካን ረዲዮ የቀድሞ ዳይሬክተር እንደ ነበሩ የሚታወቅ ሲሆን የተሻለ ዓለም ለመገንባት ይቻል ዘንድ በእየወቅቱ የተለያዩ አስተማሪ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት የሎዮላውን የቅዱስ ኢግናሽዬስ የሚያንጸባርቅ እና ማሕበሩን እንደ አንድ ድርጅት ሳይሆን ከቤተክርስቲያን እና ከአለም ጋር የተሳሰረ መንፈሳዊ ማሕበር እንደ ሆነ አድርገው ነበር አስተምህሮዋቸውን የሚያከናውኑት።
ንቅናቄው በጣሊያን ስር ሰድዶ እ.አ.አ በ1970ዎቹ ችግሮችን በውይይት መፍታት የሚችላበትን ጉዳዮች፣ ሳይንሳዊ፣ ሳይንስና ተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረቱ ተግባሮችን ተከትሎ የሚከሰቱ ነገሮችን እንዴት መፍታት እንደ ሚቻል እና ቁምስናዎችን በአዲስ አስተሳሰብ ማነጽ በተመለከተ ከእነዚህ ጋር የተያያዙ ጭብጦችን ለማጥናት ይቻል ዘንድ ወደ ሥራ የገባ ንቅናቄ እንደ ነበረ ምእመናን፣ ቤተሰብ እና ህይወትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የገለጸ ሲሆን እ.አ.አ በ1988 ዓ.ም ንቅናቄው የምዕመናንን ጉዳይ የሚመለከተው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ የምእመናን ማኅበር እንዲሆን እውቅና እንደ ሰጠው ይታወቃል።