ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን ያለው አሁናዊ ውጥረት በሰላም ይፈታ ዘንድ ጸሎት ማድረግ ይገባል አሉ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን ያለው አሁናዊ ውጥረት በሰላም ይፈታ ዘንድ ጸሎት ማድረግ ይገባል አሉ!  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን ያለው አሁናዊ ውጥረት በሰላም ይፈታ ዘንድ ጸሎት ማድረግ ይገባል አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 6/2014 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት ሩሲያ በማንኛውም ጊዜ ጎረቤቶቿን ልትወር እንደምትችል ምዕራባውያን ሃገራት እያስጠነቀቁ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት በዩክሬን እና በዙሪያዋ ላለው ሁኔታ የዓለም መሪዎች ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በርካታ የምዕራባውያን ሃገራት ዜጎቻቸው ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ ሲያሳስቡ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለምስራቅ አውሮፓ ሀገር ጸሎታቸውን አድርገዋል፣ ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ የተነሳ በቀጠናው ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ሁኔታውን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አደራ ሰጥተው፣ የፖለቲካ መሪዎችም ሰላምን ፍለጋ ሁሉንም ዓይነት ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽነዋል።

ስለዚህም ሰላም ይሰፍን ዘንድ ሁሉም ሰው በጸጥታ እንዲጸልይ ቅዱስነታቸው በወቅቱ መጋበዛቸው ይታወቃል።

“ከዩክሬን የሚሰማው ዜና በጣም አሳሳቢ ነው። የድንግል ማርያምን አማላጅነት እና የፖለቲካ መሪዎችን ሕሊና ሰላምን ይመርጥ ዘንድ ጥረት እንዲያደርጉ ትረዳቸው ዘንድ ወደ እመቤታችን ማርያም ጸሎቴን እያቀረብኩኝ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላት የሰላም መንገድን ይመርጡ ዘንድ አደራ እላለሁ ማለታቸው ተገልጿል።

ከፍተኛ ለሆነ ስቃይ ሊጋለጥ የሚችል ወጥረት ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለሰላም እንዲጸልዩ ያቀረቡት ጥሪ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሩስያ አቻቸው ዩክሬንን መውረር “ሰፊ የሰው ልጅ ስቃይ” እንደሚያስከትል አስጠንቅቀው ከነበረበት ቀን ቀጥሎ የተከሰተ ነው።

ዋይት ሀውስ በበኩሉ ባይደን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን እንደተናገሩት ምዕራቡ ዓለም አሁንም ቀውሱን ለማስቆም በዲፕሎማሲያዊ ስራ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ነገር ግን ፕሬዝዳንት ባይደን የምዕራባውያን አጋሮች በእርሳቸው አገላለጽ “ለሌሎች ሁኔታዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ዝግጁ መሆናቸውን” አፅንዖት ሰጥተው ተንግረዋል፣ ይህም የሚያመልክተው የኃይል አማራጭን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት አማራጮችን እንደ ሚጠቀሙ ጠቁመው እንደ ነበረ ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እነዚያ ሁኔታዎች በምስራቅ አውሮፓ ውስጥ ማዕቀቦችን እና ወታደራዊ እርምጃዎችን ሊያካትቱ እንደሚችሉ አብራርተዋል።

"እኛ እና አጋሮቻችን ይህንን ከባድ የሆነ ሁኔታ ለሞስኮ ግልፅ አድርገነዋል፡- ፕሬዝዳንት ፑቲን ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ከወሰነ በአለም ዙሪያ ካሉ አገሮች እና አጋሮችን ጋር በመተባበር ከባድ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንጥላለን። ብሊንከን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በኔቶ ምስራቃዊ ክፍል ያሉትን አጋሮቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ባደርጉት ንግግር "ይህንን አንድነት እና ቁርጠኝነት እንዳረጋገጡላቸው” አክለው ገልጸዋል።

ወታደራዊ ግንባታ

የሩሲያ ወታደራዊ ግንባታ በቀጠለበት ወቅት ብሊንከን የሩስያ ወረራ "የቀረበ" ስጋት በኪየቭ፣ ዩክሬን የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ለቆ መውጣቱ ትክክል መሆኑን ተናግሯል።

የኖርዌይ የስለላ አገልግሎት ሃላፊ ምክትል አድሚራል ኒልስ አንድሪያስ ስቴንስሶንስ እንዳሉት አሁን የሩሲያ 150,000 ወታደሮች በዩክሬን ዙሪያ ተከማችተው ይገኛሉ፣ ይህ ካለፈው የዩክሬን እና የአሜሪካ ግምት እጅጉን ይበልጣል ብለዋል።

የእሁዱ የሰዓታት ቆይታ በፕሬዝዳንት ባይደን እና ፑቲን መካከል የተደረገው ጥሪ በአውሮፓ የማይቀረውን ጦርነት ስጋት ቀንሶታል ሲል ዋይት ሀውስ አላቀረበም።

ሆኖም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሁሉም አገራት እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል። እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም ሩሲያ የዩክሬን ክሬሚያ ልሳነ ምድርን ወደ ራሷ ግዛት ከቀላቀለች በኋላ እና በምስራቅ ሩሲያን የሚደገፉ ተገንጣዮችን ከደገፈች በኋላ ሀገራቸው አሁን የተሻለ ዝግጅት እንዳላት ተናግረዋል ። "በየቀኑ ዝግጁ መሆን አለብን እና (ከሩሲያ ጋር ያለው ውጥረት) የተጀመረው ትናንት አይደለም እ.አ.አ በ 2014 ዓ.ም ነበር የተጀመረው፣ ስለዚህ ዝግጁ ነን "ብለዋል።

በክሬምሊን የሚደገፈው የሩሲያ የሚሳኤል እና የመድፍ ሳይንስ አካዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ኮንስታንቲን ሲቭኮቭ በዩክሬን ጉዳይ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግጭት ወደ ኒውክሌር ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

ይህም በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የፍጻሜ ዘመን ጦርነት ላይ በመጥቀስ “የአርማጌዶን መንገድ” እንደሚሆን ተናግሯል። እንዲህ ያለው የኒውክሌር ጦርነት ዛሬ የሚታወቁትን ዩኤስ እና ሩሲያ ያጠፋል እና አለምን ለዘላለም ይለውጣል ብሏል።

13 February 2022, 12:23