ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ድሆች እና ደስተኞች ነበሩ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚገኙ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በየካቲት 06/2014 ዓ.ም ያደርጉት አስተንትኖ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 6፡20-26 ላይ ተወስዶ በተነበበው ከዚህ በታች በተጠቀሰው የእግዚአብሔር ቃል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ተገልጿል፣ ቃሉም እንዲህ ይል ነበር . . .

ኢየሱስም አብሮአቸው ከተራራው ወርዶ ደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፤ ከደቀ መዛሙርቱም እጅግ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፤ ከይሁዳ ሁሉና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ጠረፍ የመጣ ብዙ ሕዝብም በዚያ ነበረ፣ እነዚህም የመጡት ሊሰሙትና ካለባቸው ደዌ ሊፈወሱ ነበር። በርኩሳን መናፍስት ይሠቃዩ የነበሩትም ተፈወሱ፤ ኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበር። ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመመልከት እንዲህ አለ፤ “እናንት ድኾች ብፁዓን ናችሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ናትና፤ እናንት አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፤ ኋላ ጠግባላችሁና፤ እናንት አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፤ ኋላ ትሥቃላችሁና፤ ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሏችሁ፣ከመካከላቸው ሲለዩአችሁና ሲነቅፏችሁ፣ ክፉ ስምም ሲሰጧችሁ ብፁዓን ናችሁ። “እነሆ፤ ወሮታችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፣ በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ፈንድቁም፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነበርና። “ነገር ግን እናንት ሀብታሞች ወዮላችሁ፤ መጽናናታችሁን አሁኑኑ ተቀብላችኋልና። እናንት አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ትራባላችሁና።እናንት አሁን የምትሥቁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ታዝናላችሁ፤ ታለቅሳላችሁም። ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም ሲናገሩላችሁ ወዮላችሁ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት ያደረጉላቸው ይህንኑ ነበርና”

በሚለው የቡራኬና የወዮታ ስብከት ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ድኾች እና ደስተኞች ነበሩ ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዝቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።  

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ማእከል ብፁዓን ናቸው (ሉቃ. 6፡20-23) የሚለው ቃል ይገኝበታል። ኢየሱስ በብዙ ሕዝብ ቢከበብም “ደቀ መዛሙርቱን” (6፡20) እየተመለከተ ስብከቱን ማወጅ መቀጠሉ ትኩረትን የሚስብ ነገር ነው። ለደቀ መዛሙርቱ ነበር የተናገረው። ብፁዓን ናቸው እያለ የሰበከው ስብከት የኢየሱስን ደቀ መዝሙር ማንነት ይገልጻሉ፣ ምናልባት እንግዳ ሊመስሉ ይችላሉ፣ ደቀ መዛሙርት ላልሆኑት ለመረዳት አዳጋች ሊመስሉ ይችላሉ። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ምን ይመስላል ብለን እራሳችንን ብንጠይቅ መልሱ በትክክል ብፁዓን ናቸው የሚለው ይሆናል። የሌሎቹ ሁሉ መሠረት የሆነውን የመጀመሪያውን እናያለን፡- “እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ናትና” (6፡20)። እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ። ኢየሱስ ስለ ተከታዮቹ የተናገራቸው ሁለት ነገሮች፡- የተባረኩና ድሆች መሆናቸውን ነው። በእርግጥ ድሆች ስለሆኑ የተባረኩ ናቸው።

በምን መልኩ? የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ደስታውን የሚያገኘው በገንዘብ፣ በሥልጣን ወይም በሌላ ቁሳዊ ነገር ሳይሆን በየቀኑ ከእግዚአብሔር በሚቀበለው ስጦታዎች ማለትም ሕይወት፣ ፍጥረት፣ ወንድሞችና እህቶች ወዘተ ነው። የህይወት ስጦታዎች ናቸው። የያዛቸውን እቃዎች እንኳን ቢያካፍላቸው ደስ ይለዋል ምክንያቱም በእግዚአብሔር አመክንዮ ውስጥ ስለሚኖር፣ ታዲያ የእግዚአብሔር አመክንዮ ምንድን ነው? ችሮታ። ደቀ መዝሙሩ በነጻነት መኖርን ተምሯል። ይህ ድህነት ለሕይወት ትርጉም ያለው አመለካከትም ነው፣ ምክንያቱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር እኔ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ ሳይል በየቀኑ መማር እንዳለበት ስለሚያውቅ፤ እሱ እንዳለው አያስብም። እናም ይሄ ድህነት ነው፡ በየቀኑ መማር ስላለበት ግንዛቤው እየሰፋ ይሄዳል። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር፣ እንዲህ ዓይነት አመለካከት ስላለው፣ ትሑት፣ ግልጽ ሰው፣ ከጭፍን ጥላቻና ግትርነት የጸዳ ነው።

ባለፈው እሑድ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ አንድ የሚያምር ምሳሌ ነበር፡- ስምዖን ጴጥሮስ የተባለው ባለሙያ ዓሣ አጥማጅ ባልተለመደ ሰዓት መረቡን እንዲጥል የሚጠይቀውን የኢየሱስን ግብዣ ተቀበለ። ከዚያም እጅግ በጣም ብዙ ዓሳ በመያዙ ተደንቆ ጌታን ለመከተል ጀልባውን እና ንብረቱን ሁሉ ትቶ ሄደ። ጴጥሮስ ሁሉንም ነገር በመተው አስተዋይ መሆኑን አሳይቷል፣ በዚህም ደቀ መዝሙር ሆነ። በአንጻሩ ግን፣ ከራሳቸው ሐሳብ ጋር በጣም የተጣበቁ፣ ለራሳቸው እርግጠኞች የሆኑ ሰዎች ግን፣ ኢየሱስን በትክክል አይከተሉትም፣ በትንሹ ነው የሚከተሉት፣ “በእርሱ እስማማለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይስማማል” በተባለው ነገር ብቻ ነው የሚተማመኑት ከዚያ በኋላ ግን ለቀሪው አይሰራም ነው የሚሉት ።  ይህ ደግሞ ደቀመዝሙር አይደለም። እና ስለዚህ በሀዘን ውስጥ ይወድቃል። ያዘነበት ምክንያት ሂሳቦቹ በእሱ ላይ ስለማይጨመሩ፣ እውነታው ከአእምሮው ስላመለጠ እና እርካታ ስላጣ ነው። ደቀ መዝሙሩ በበኩሉ እራሱን እንዴት እንደሚጠይቅ ያውቃል፣ በየቀኑ እግዚአብሔርን በትህትና እንዴት መፈለግ እንዳለበት ያውቃል፣ እና ይህ ወደ እውነታው እንዲገባ፣ ብፅዕናውን እና ውስብስብነቱን እንዲረዳ ያስችለዋል።

በሌላ አገላለጽ፣ ደቀ መዝሙሩ የብፁዕናን እርስ በእርስ የሚጋጭ የሚመስል (አያአዎ) ይቀበላል፤ እርሱ የተባረከ፣ ማለትም፣ ደስተኛ፣ ድኽ፣ ብዙ ነገር የጎደለው እና ይህንንም የሚገነዘብ መሆኑን ያውጃሉ። ሰብአዊነት በሌላ መንገድ እንድናስብ ይመራናል፣ ሀብታም የሆኑት ደስተኛ ናቸው፣ በቁሳቁሶች የተሞሉ ሰዎች ደስተኞች ናቸው፣ ጭብጨባ የሚቀበሉ እና ብዙዎች የሚቀኑባቸው ሁሉም ነገር በእርግጠኝነት ያላቸው ናቸው ብለን እናስብ ይሆናል። ነገር ግን ይህ አለማዊ ሃሳብ ነው እንጂ የብፁዕና ሐሳብ አይደለም! በተቃራኒው ኢየሱስ ዓለማዊ ስኬት ውድቀት መሆኑን ያውጃል፣ ምክንያቱም በራስ ወዳድነት ላይ የተመሰረተ እና ከዚያም በልብ ውስጥ ያለውን ባዶነት ያመለክታል። ብፁዕና እርስ በእርሱ የሚጣረዝ (አያአዎ) የሚመስል ነገር ሲገጥመው፣ ደቀ መዝሙሩ ወደ አእምሮው ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ይህ ነገር የተፈጠረው ከእግዚአብሔር በመጣ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝቦ እግዚአብሔር ሳይሆን በእኛ አምክዮ ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ግን በተቃራኒው እኛ በእግዚአብሔር አመክንዮ ውስጥ መግባት እንዳለብን ተረድተን ወደ እርሱ መቅረብ ይኖብናል። ይሄ በቀስታ መጓዝን ይጠይቃል፣ አንዳንዴ አድካሚ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሁሌም በደስታ ይታጀበ ነው። ምክንያቱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ከኢየሱስ ወደ እርሱ በሚመጣው ደስታ ደስ ይለዋልና፣ ኢየሱስ የተናገረው የመጀመሪያው ቃል፡- የተባረክ ነው የሚለው እንደ ነበረ እናስታውስ፣ ስለዚህም ብፁዕን ናቸው የሚለው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ስም ነው። ይህ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የመሆን ተመሳሳይ ቃል ነው። ጌታ ከራስ ወዳድነት ባርነት ነፃ አውጥቶናል፣ መዘጋታችንን ፈታልን፣ ግትርነታችንን አቀለጠልን እናም እውነተኛ ደስታን ይገልጥልናል ይህም ብዙ ጊዜ በማናስበው ቦታ ይገኛል። ህይወታችንን የሚመራው እሱ እንጂ እኛ አይደለም፣በቅድመ-አሳባችን ወይም በፍላጎታችን ብቻ መኖር አንችልም። በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ በራሱ በኢየሱስ እንዲመራ የፈቀደ፣ ልቡን ለኢየሱስ የሚከፍት፣ የሚያዳምጠው እና መንገዱን የሚከተል ነው።

ከዚያም እራሳችንን መጠየቅ እንችላለን፡- እኔ - እያንዳንዳችን - እንደ ደቀ መዝሙር ሆነን መኖር እንችላለን ወይ? ወይስ እኔ ደህና ሆኖ የሚሰማውን፣ ጥሩ ስሜት የሚሰማውን፣ አስቀድሞ እንደደረሰ የሚሰማውን ሰው ግትርነት ነው የምከተለው? ብፅዕና እርስ በእርሱ የሚጣረዝ (አያአዎ) በሚመስል ነገር ውስጥ እራሴን ለማስገባት እፈቅዳለሁ ወይስ በሃሳቦቼ ክልል ውስጥ እቆያለሁ? እናም ከዚያ የብፅዕና አመክንዮ ከችግሮች እና ከመከራዎች ባሻገር ኢየሱስን በመከተሌ ደስታ ይሰማኛል ወይ? ይህ የደቀ መዝሙሩ ዋና ባህሪ ነው፡ የልብ ደስታ አስፈላጊ ነው። አንርሳ፡ የልብ ደስታ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ሰው ደቀ መዝሙር መሆኑን ለማወቅ ከፈለገ ይህ የመሰረት ድንጋይ ነው: በልቡ ደስታ አለው ወይ? በልቤ ውስጥ ደስታ አለኝ? ዋናው ነገር ይህ ነው።

ሁሉን ለመቀበል ዝግጁ እና ደስተኛ ደቀ መዛሙርት ሆነን እንድንኖር የመጀመሪያዋ የጌታ ደቀ መዝሙር የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

13 February 2022, 11:51

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >