ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሮታ ሮማና በመባል ከሚታወቀው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሮታ ሮማና በመባል ከሚታወቀው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቤተክርስቲያን የሕግ የማስከበር ሂደቶችን በሐዋርያዊ ልቦና ማዳመጥ ያስፈልጋል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሮታ ሮማና በመባል የሚታወቀው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ፍርድ ቤት የዚህን የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማሕበርሰብ ክፍሎች ዘንድ በቅርቡ የተጀመረው 2022 ዓ.ም ላይ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ሥራቸውን በይፋ በጀመሩበት ወቅት ከቅዱስነታቸው ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ሐዋርያዊ የሕግ ማስፈጸም ሂደቶችን በሐዋርያዊ ልቦና ውስጥ ሆነው እንዲያከናውኑ ጥሪ ማቀረባቸው ተገልጿል። በጥር 19/2014 ዓ.ም ላይ በቫቲካን በተደርገው ስብሰባ ላይ ለተገኙ የሐዋርያዊ ፍርድቤቱ ዳኞች ቅዱስነታቸው ባደርጉት ንግግር በዚህ የፍርድ ቤት ስራ ውስጥ በትዳራቸው መፍረስ ምክንያት ለሚሰቃዩ ሰዎችን ሁል ጊዜ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከተሰብሳቢዎቹ ጋር ባደረጉት ንግግር፣ የተሻሩ ጉዳዮችን በሚመለከት የሲኖዶሳዊውን ጭብጥ በማሰላሰል ተልእኳቸው ቤተሰብን በማገልገል እንዲወጡ ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

ሲኖዶሳዊ ሂደት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባደርጉት ንግግር የሲኖዶስ ሥራ ከፍትህ ሥራዎች ጎን ለጎን የሚደረጉ ውይይቶችን ማካተት እንደሚገባቸው አስምረውበታል፣ ይህም የቀኖናዊውን ሂደት አስፈላጊነት እንደገና እንዲያጠናቅቅ ለማበረታታት “የትዳር መፍረስ ላጋጠማቸው እና በተመሳሳይ ጊዜ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በሚስማማ መልኩ አስተሳስረው እንዲቀጥሉ ሐዋርያዊ የሆነ እንክብካቤ ማድረግ እንደ ሚጠበቅባቸው” ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ሲኖዶሳዊነት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ገለጹት ከሆነ “በአንድ ላይ መመላለስን ያመለክታል” ያሉ ሲሆን በመቀጠልም “ሁሉም የሂደቱ ተሳታፊዎች ለተመሳሳይ ዓላማ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቦላቸው፣ በወንድና በአንዲት ሴት መካከል ስላለው ተጨባጭ ጥምረት እውነትን ማብራት እና ድምዳሜ ላይ መድረሱን በድጋሚ ማወቅ አለብን። በመካከላቸው እውነተኛ ትዳር መኖር ወይም አለመኖሩን በተመለከተ ማረጋገጥ ይኖርብናል” ብለዋል።

እውነትን መፈለግ

በቅድመ ደረጃም ቢሆን ምእመናን የሐዋርያዊ አግልግሎት ዕርዳታን በሚፈልጉበት ወቅት “ስለ ሕብረታቸው እውነትን ለማወቅ ጥረት መደረግ አለበት፣ ቁስሎችን ለመፈወስ መሥራት የግድ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ” መሆኑን አበክሮ ተናግሯል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም “ከንቱ የመሆን ዕድልን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ምእመናን የጋብቻ ስምምነትን ውድቅ እንዲሆን የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች ላይ እንዲያስቡ ማድረግ ያስፈልጋል” ያሉ ሲሆን እውነትን ለማግኘት የሚደረገው የጋራ ፍለጋ ተመሳሳይ ዓላማ “የፍትህ ሂደቱን በእያንዳንዱ ደረጃ መለየት አለበት” ብሏል።

ማንኛውም ሆን ተብሎ የተደረገ የእውነታ ለውጥ ወይም እውነታን መጠቀሚያ ማደረግ “በተግባራዊ ሁኔታ የሚፈለገውን ውጤት ለማግኘት ተቀባይነት የለውም” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አክለውም “ጠበቆችም ቢሆኑ አስከፊ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በፍርድ ሂደት ውስጥ አብሮ የመጓዝ እውነታ "ለተዋዋይ ወገኖች እና ለደጋፊዎቻቸው፣ ለተጠሩት ምስክሮች እንደ እውነቱ ከሆነ እውቀታቸውን ለሂደቱ አገልግሎት መስጠት ለሚገባቸው ባለሙያዎች ማዳመጥ እንደሚገባ እንዲሁም በተለየ መንገድ ዳኞች በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔዎችን ማድረግ እንደ ሚጠበቅባቸው” ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ማዳመጥ እና ማስተዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ ከህግ ጋር በተያያዘ ሲኖዶሳዊነት “የማያቋርጥ የማዳመጥ ልምምድን ያመለክታል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፤ ይህም ዝም ብሎ መስማት ማለት ግን አይደለም ብለዋል።

ሌላው የሲኖዶሳዊው ገጽታ የማስተዋል አስፈላጊነት ነው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ ማስተዋል አብሮ በመመላለስ እና በማዳመጥ ላይ የተመሰረተ ነው፣ እናም ተጨባጭ የጋብቻ ሁኔታ በእግዚአብሔር ቃል እና በቤተክርስቲያኗ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ብርሃን እንዲነበብ ያስችላል" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አክለውም እንደገለጹት “የዚህ መንገድ ውጤቱ ፍርድ ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል “በግል ልምድ ላይ ወደሚገኝ የእውነት ቃል የሚመራ በጥንቃቄ የማስተዋል ፍሬ ላይ ተንተርሰን ፍርድ መስጠት እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን ስለዚህም ከዚያ በኋላ የሚከፈቱትን መንገዶች አጉልቶ ያሳያል” ሲሉ አክለው ገለጸዋል።

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሐዋርያዊ ፍርድ ቤት አባላትን በታማኝነት እና በታዳሽ ትጋት ፣ በፍትህ ፣ በእውነት እና በመጨረሻም በላቲን ቋንቋ “በሰላስ አኒማረም” (የነፍስ መዳን) አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

27 January 2022, 11:50