ፈልግ

በካዛክስታን የተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞ በካዛክስታን የተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በካዛክስታን በተካሄደው ተቃውሞ ላይ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 01/2014 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለአለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በቅርብ ቀናት በካዛክስታን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተጎጂዎች እንዳሉ በሃዘን ተረድቻለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው ለእነርሱ እና ለቤተሰቦቻቸው እጸልያለሁ፣ እናም በተቻለ ፍጥነት ማኅበራዊ መግባባት ወደነበረበት እንዲመለስ ተስፋ አደርጋለሁ፣ ውይይት፣ ፍትህ እና የጋራ ጥቅም በሚያስከብር ሁኔታ ላይ አትኩሮ የአገሪቷ ሕዝቦች እና ባለስልጣናት በዚህ አግባብ በስላም ልዩነታቸውን ይፈቱ ዘንድ ይህም ገቢራዊ ይሆን ዘንድ እንዲሰሩ የሰላም ንግሥት የሆነቺው የኦዝዮርኖጄን እመቤታችን ቅድስት ማርያም የካዛክስታን ህዝብ ትጠብቅ ዘንድ በአደራ ሰጣለሁ ማለታቸው ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ሲቀጥሉ ከሮም ከተማ እና እንዲሁም ከተለያዩ አከባቢዎች የመጡ እና በሥፍራው የተገኙትን ምዕመናን በሙሉ ከልብ የመነጨ ሰላምታዬን አቅረባለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይ በኔፕልስ አቅራቢያ ከምትገኘው ከተማ የመጡ ፍራታማጆር በመባል ከሚታወቀው ቡድን የተውጣጡ ምዕመናን እንኳን ደህና በጣችሁ ብለዋል።

ዛሬ ማለዳ እንደ ተለመደው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የጥምቀት በዓል በምናክብርበት ወቅት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ አንዳንድ በቫቲካን የሚሰሩ ሰራተኞች ልጆች አጥምቂያለሁ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ጊዜ ውስጥ ጥምቀትን ለተቀበሉ ወይም ለሚቀበሉ ሕፃናት ሁሉ ጸሎቴን እና ቡራኬየን ማቅረብ እፈልጋለሁ ያሉ ሲሆን ጌታ ይባርካቸው እመቤታችንም ትጠብቃቸው ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው ብለዋል።

እናም ለሁላችሁም አንድ ነገር ለማለት እፈለጋለሁ፣ የተጠመቃችሁበትን ቀን በፍጹም እንዳትረሱ፣ መቼ ነው የተጠመቅኩት? ብለን በመጠየቅ ይህንን መርሳት የለብዎትም፣ እና ያንን ቀን እንደ የበዓል ቀን አድርጋችሁ አክብሩት አስታውሱትም፣ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ፣ እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሳምንታዊውን መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

09 January 2022, 11:46

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >