ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ Catholic Action France አባልት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ Catholic Action France አባልት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ መሰረታችሁን ያደረጋችሁ ውጤታማ ሐዋርያት ሁኑ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሙስ ዕለት ጥር 05/2014 ዓ.ም (Catholic Action France) ከካቶሊክ አክሽን ፈረንሳይ አባላት ጋር ተገናኝተው የእግዚአብሔር ቃል የአገልግሎታቸው ንድፍ ሐሳብ ሥር መሰረት ይሆን ዘንድ መናገራቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከካቶሊክ አክሽን ፈረንሳይ አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት አድርገውት የነበረውን ንግግር የጀመሩት እ.አ.አ አቆጣጠር 1922 ዓ.ም ጀምሮ ለ17 አመታት ያህል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ከነበሩት ፒዮ 11ኛ ዘመን በመሄድ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በዚህ መሰረት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመገናኘት የመምጣት ባህላቸውን አስታውሰዋል።

ማኅበሩ ለዚህ የሮም ጉዞ የመረው መሪ ቃል “የዛሬው ዘመን ሐዋርያት” የሚለው እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህንንም ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “በአሁኑ ጊዜ ውጤታማ ሐዋርያት እንድንሆን የተደረገ ጥሪ” ላይ አትክረው መናገራቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ሲራመዱ “ያጋጠሟቸውን ነገሮች በማስታወስ ይጀምራሉ” ብለዋል። ከዚያም በእነዚያ ክስተቶች ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት ይገነዘባሉ፣ በመጨረሻም የክርስቶስን ትንሣኤ ለማወጅ ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ እርምጃ ወስደዋል በማለት መናገራቸው ተገልጿል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል ትኩረታቸውን በሦስት ደረጃዎች ላይ አድርገው የተናገሩ ሲሆን እነዚህም ማየት፣ መወሰን እና እርምጃ መውሰድ የተሰኙ ሦስት ደረጃዎች ናቸው።

የማስታወስ አስፈላጊነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ማየት የሕይወታችንን፣ የታሪካችን፣ የቤተሰባችን፣ የባህልና የክርስቲያናዊ ወግ እና ሥርዓተ መሠረቱ ምን ማለት እንደሆነ ለማየት መቆምን የሚያካትት የመጀመሪያው መሠረታዊ ደረጃ ነው” ብለዋል።

የማስታወስ አስፈላጊነትን በማጉላት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጣሊያነኛ ቋንቋ “Fratelli tutti” (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) በሚል አርእስት እርሳቸው ያፋ ያደረጉትን ሐዋርያዊ መልእክት በንግግራቸው ወቅት ያስታወሱ ሲሆን እሱም “በአለማችን ያለውን አንዳንድ ጊዜ አሳሳቢ ሁኔታዎችን በመመልከት ይጀምራል። ምናልባት ትንሽ ተስፋ አስቆራጭ ሊመስል ይችላል፣ ግን ወደፊት ለመራመድ አስፈላጊ ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

የእግዚአብሔር ቃል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትኩረታቸውን በሁለተኛው ደረጃ ላይ በማድረግ ለመወሰን ወይም ለማስተዋል ይህ ጊዜ “እራሳችንን እንድንጠይቅ እና ጊዜውን እንድንጠቀምበት የምንፈቅድበት ጊዜ ነው” ብለዋል ።

“የዚህ ደረጃ ቁልፉ የቅዱሳት መጻሕፍት ማጣቀሻ ነው። አንድ ሰው ሕይወቱ በአምላክ ቃል ላይ ተመርኩዞ መደረጉን የመቀበል ጉዳይ ነው” ሲል አስረድቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “በአለም እና በህይወታችን ክስተቶች መካከል ባለው ግንኙነት እና የእግዚአብሔር ቃል በሌላ በኩል፣ ጌታ ለእኛ የሚያቀርበውን ልመና ማስተዋል እንችላለን” ብለዋል።

ሲኖዶሳዊነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በንግግራቸው ወቅት የካቶሊክ አክሽን ንቅናቄዎች “በታሪካቸው እውነተኛ ሲኖዶሳዊ ልምምዶች በተለይም በቡድን ሕይወት ውስጥ ያዳበሩ ናቸው” ብለዋል፣ ይህም የልምዳቸው መሠረት ነው በማለት አክለው ገልጸዋል።

“ቤተ ክርስቲያኒቱ በአጠቃላይ በሲኖዶስ ሂደት ውስጥም ትሰራለች” በማለት የእነርሱ የበኩላቸው አስተዋፅኦ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

"በዚህ ረገድ ሲኖዶሳዊነት ቀላል ውይይት ወይም አብላጫ መግባባትን ፍለጋ በፓርላማ አግባብ የሚደረግ ንግግር አለመሆኑን እናስታውስ።...መከተል ያለብን ዘይቤ ነው፣በዚህም ዋና ተዋናኝ መንፈስ ቅዱስ ነው። በመጀመሪያ እና በዋነኛነት እራሱን በእግዚአብሔር ቃል ይገልፃል ፣ ያነባል፣ ያሰላስላል እና በአንድነት ይካፈላል ” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

የእግዚአብሔር ተግባር

በሦስተኛው ደረጃ ላይ ሲደርሱ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተግባር ምንጊዜም የእግዚአብሔር ተነሳሽነት ሊኖረው እንደሚገባ ወንጌሉ እንዴት እንደሚያስተምር ገልጿል።

"ስለዚህ የኛ ድርሻ የእግዚአብሔርን ተግባር በልቦች መደገፍ እና ማበረታታት ነው፣ በየጊዜው ከሚፈጠረው እውነታ ጋር መላመድ ነው" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ የምንኖርበት ጊዜ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ አይደለም ብለዋል።

 “በአሁኑ ጊዜ፣ በተለይም በአውሮፓ፣ በክርስቲያናዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚካፈሉ ሰዎች ስለ ተቋማት የበለጠ ስለሚጠራጠሩ ብዙ ጊዜ የማይጠይቅ እና ጊዜያዊ ግንኙነት ይፈልጋሉ” ብሏል።

በመቀጠልም “ወጣቶች በተለይ ለፍቅር የበለጠ ስሜታዊ ናቸው፣ እና ስለሆነም የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፣ ካለፉት ትውልዶች የበለጠ ደካማ ናቸው፣ በእምነት ላይ ያልተመሰረቱ፣ ነገር ግን ትርጉም እና እውነትን በመፈለግ ላይ ያሉ በመሆናቸው ብዙም ለጋስ አይደሉም ብለዋል።

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለንቅናቄው አባላት እንደ ካቶሊክ አክሽን አባልት ተልእኳቸው እንደሆነ ገልጸው እነዚህን ሰዎች የተረሱ ሰዎችን እና ድሆችን ተደራሽ ማደረግ፣ በክርስቶስ እና በባልንጀሮቻቸው ፍቅር እንዲያድጉ ማድረግ እና “ወደ ታላቅ መንፈሳዊ ሕይወት መምራት ተጨባጭ ቁርጠኝነት በራሳቸው ሕይወት እና በቤተክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ዋና ተዋናዮች እንዲሆኑ፣ ስለዚህም ዓለም እንዲለወጥ እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

 

14 January 2022, 16:20