ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሁላችንም የእግዚአብሔር ቃል እንዲለውጠን ልንፈቅድለት ይገባል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰብሰቡ ምዕመናን በእለት ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በጥር 15/2014 ዓ.ም በቫቲካን ያደርጉት አስተንትኖ በእለቱ ለየት ባለ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቃል የሚከበርበት እለተ ሰንበት ቀን ከግምት ያስገባ አስተንትኖ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ሁላችንም ብንሆን የእግዚአብሔር ቃል ሊለውጠን ይገባል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ሥርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ስብከቱን በይፋ ሲጀምር አይተናል (ሉቃስ 4፡14-21)፤ ይህ የኢየሱስ የመጀመሪያ ስብከት ነበር። ወደ አደገበት ወደ ናዝሬት ሄዶ በምኩራብ ውስጥ በጸሎት ይሳተፋል። ለማንበብ ተነሳ እና የነቢዩ ኢሳያስ ቃል የተጻፈበትን የብራና ጥቅልል ​​ውስጥ፣ ለድሆችና ለተጨቆኑት የማጽናኛና የነጻነት መልእክት የሚያውጅ መሲሑን የሚመለከት ክፍል አገኘ (ኢሳ 61፡1-2)። በንባቡ መጨረሻ ላይ “የሁሉም ዓይኖች…ትኩር ብለው የመለከቱት ነበር” (ሉቃስ 4፡ቁ. 20) በማለት ይገልጻል። ኢየሱስም እንዲህ ሲል ይጀምራል፡- “ይህ በጆሮአችሁ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” ይላቸው ጀመር። (ሉቃስ 4፡21)። ዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ እናተኩር። በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የተመዘገበው የኢየሱስ ስብከት የመጀመሪያው ቃል ነው። በጌታ የተነገረው፣ በሁሉም ዘመናት ውስጥ የሚያልፍ እና ሁል ጊዜም የሚሰራ “ዛሬ”ን ያመለክታል። የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም "ዛሬ" ነው። በ "ዛሬ" ይጀምራል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስታነብ "ዛሬ" በነፍስህ ውስጥ መሥራት ይጀምራል፣ በደንብ ከተረዳህ ዛሬ በአንተ ውስጥ መሥራት ይጀምራል። ዛሬ። የኢሳይያስ ትንቢት ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የጀመረ ቢሆንም ኢየሱስ ግን “በመንፈስ ኃይል” (ሉቃስ 4፡14) አግባብነት ያለው እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ፍጻሜውን እንዲያገኝ አድርጎታል፣ እናም የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት መቀበል እንደሚቻል ያሳያል፣ ሁሉም ነገር ከዛሬ ይጀምራል። እንደ ጥንታዊ ታሪክ አይደለም፣ በፍጹም እንዲህ አይደለም፣ ዛሬ ይጀምራል። ዛሬ ለልብህ ይናገራል።

የኢየሱስ አገር ሰዎች በቃሉ ተደንቀዋል። ምንም እንኳን በጭፍን ጥላቻ ተውጠው፣ ባያምኑትም፣ ትምህርቱ ከሌሎቹ አስተማሪዎች የተለየ መሆኑን ይገነዘባሉ (ሉቃስ 4፡ 22)፣ ኢየሱስ የበለጠ ነገር እንዳለው ይገነዘባሉ። ምን አለ? የመንፈስ ቅዱስ ቅባት አለ። አንዳንድ ጊዜ ስብከቶቻችን እና ትምህርቶቻችን አጠቃላይ ውስብስብ ሆነው ሲቀርቡ ይታያል። የሰዎችን ነፍስ እና ህይወት አይነኩም። እና ለምን? ምክንያቱም ዛሬ የዚህ ኃይል ስለጎደላቸው፣ ኢየሱስ በመንፈስ ኃይል “ትርጉም የተሞላው” ዛሬ ነው። ዛሬ እያናገረህ ነው። አዎን አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው እንከን የለሽ ኮንፈረንሶችን፣ በሚገባ የተገነቡ ንግግሮችን ይሰማል፣ ነገር ግን ልብን አያንቀሳቅሱ ይሆናል፣ በዚህም የተነሳ ሁሉም ነገር እንደበፊቱ ሆኖ ይቀራል። ብዙ ስብከቶች እንኳን በአክብሮት እላለሁ ነገር ግን በሐዘን ተሞልቼ ለማለት እፈልጋለሁ ረቂቅ ናቸው፣ እናም ነፍስን ከማንቃት ይልቅ፣ እንቅልፍ ውስጥ ያስገባሉ። ምዕመናን ሰዓታቸውን መመልከት ሲጀምሩ - "ይህ መቼ ነው የሚያበቃው?" ብለው እስኪጠይቁ ድረስ ነፍስን እንቅልፍ ውስጥ ያስገባሉ። ስብከት ለዚህ ዓይነቱ አደጋ ያጋልጣል፡ ያለ መንፈስ ቅባት የእግዚአብሔርን ቃል ያደኸያል ወደ ሥነ ምግባራዊ እና ረቂቅ ፅንሰ-ሀሳቦች ይወርዳል። ወንጌሉን ከጊዜው ውጭ እንደሆነ፣ ከእውነታው የራቀ ይመስል ለየብቻ ያቀርባል። እናም መንገዱ ይህ አይደለም። ነገር ግን በዛሬ ኃይል ያልተዋጀ ቃል ለኢየሱስ የተገባ አይደለም እና የሰዎችን ሕይወት አይለውጥም። ለዛም ነው የምትሰብኩ ሰዎች እባካችሁ የኢየሱስን የዛሬን ቀን ቀድመው ያዩትና በሌሎች ዛሬ ማሳወቅ ይችሉ ዘንድ መስበክ አለባችሁ ይምለው ለዚህ ነው። ትምህርቶችን፣ ኮንፈረንሶችን መስጠት ከፈለጉ፣ ነገር ግን በሌላ ቦታ፣ በስብከተ ወንጌል ጊዜ ሳይሆን፣ ልብን በሚያነቃቃ መልኩ ቃሉን መስጠት አለባቸው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ለየት ባለ ሁኔታ በሚታሰብበት ሰንበት ልብን ለሚነቃቃው ቃል በታማኝነት ጸንተው እስከ “ዛሬ” ድረስ በታማኝነት ጸንተው የቆዩትን የወንጌል ሰባኪዎችን አመሰግናለሁ። ቅዱሳት መጻሕፍትን ሕያው የሚያደርግ የመንፈሱ ጣፋጭ ኃይል የሆነውን ኢየሱስን ዛሬ እንዲኖሩ እንጸልይላቸው። የእግዚአብሔር ቃል፣ በእርግጥ ሕያው እና ውጤታማ ነው (ዕብ. 4፡12)፤ ይለውጠናል፣ ወደ ጉዳያችን ያስገባል፣ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ያበራል፣ ያጽናናል፣ ሥርዓትንም ያመጣል። አስታውሱ የእግዚአብሔር ቃል ተራውን ቀን እግዚአብሔር ወደ ሚናገርበት ዛሬ ይለውጠዋል። እንግዲያው፣ ቅዱስ ወንጌልን አንስተን በየዕለቱ ለማንበብ እና ለማሰላሰል ትንሽ ምንባብ እንምረጥ። በጉዞህ ላይ በማንኛውም ጊዜ ለማንበብ ወንጌልን በኪስህ ወይም በቦርሳህ አስቀምጥ እና በተረጋጋ መንፈስ አንብብ። ከጊዜ በኋላ እነዚህ ቃላት በተለይ ለእኛ ለሕይወታችን እንደተፈጠሩ እንገነዘባለን። እያንዳንዱን ቀን በተሻለ እና በተረጋጋ እይታ እንድንቀበል ይረዱናል፣ ምክንያቱም ወንጌል ወደ ዛሬው ዓለም ሲገባ በእግዚአብሔር ይሞላል። ሀሳብ መስጠት እፈልጋለሁ። በዚህ በዛሬው ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የምሕረት ወንጌል የሆነው የሉቃስ ወንጌል ይሰበካል። ለምን በግል፣ ወይም አንድ ላይ ሆነን አንድ ትንሽ ምንባብ በየቀኑ አታነብም? አጭር የሆነ ቃል በእየለቱ ማንበብ ያስፈልጋል። እራሳችንን ከወንጌል ጋር እናስተዋውቀው፣ የእግዚአብሔርን አዲስነት እና ደስታን ያመጣልናል!

በመላ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረውን የሲኖዶስ ጉዞ የሚመራ የእግዚአብሔር ቃልም ምልክት ነው። እርስ በርሳችን በትኩረት እና በማስተዋል ለመደማመጥ ስንጥር - ምክንያቱም የአመለካከት ጥያቄ አይደለም ፣ በፍጹም እንዲህ አይደለም ፣ ግን ቃሉን የመለየት ፣ እዚያ - የእግዚአብሔርን ቃል እና የመንፈስ ቅዱስን ቃል አብረን እንስማ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየዕለቱ ራሳችንን በወንጌል የምንመገብበትን ጽናት ታሰጠን።

23 January 2022, 11:31

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >