ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሄሮድስ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ስላሉ ንጹሃን ሕጽናት ግፍ ተናገሩ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሄሮድስ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ስላሉ ንጹሃን ሕጽናት ግፍ ተናገሩ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሄሮድስ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ስላሉ ንጹሃን ሕጽናት ግፍ ተናገሩ!

የጎሮጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማህበረሰቦች ዘንድ ታኅሣሥ 16/2014 ዓ.ም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል መከበሩ የሚታወስ ሲሆን ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከተከበረ ከ 3 ቀን በኋላ “ሄሮድስ ጠቢባኑን በምስጢር አስጠርቶ በማነጋገር ኮከቡ የታየበትን ትክክለኛ ጊዜ ተረዳ። ጠቢባኑንም ወደ ቤተ ልሔም ልኮ፣ “ሂዱና ሕፃኑን ፈልጉ፤ እኔም ደግሞ ሄጄ እንድሰግድለት፣ እንዳገኛችሁት ወደ እኔ ተመልሳችሁ የት እንዳለ ንገሩኝ” አላቸው። ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ” እነዚህ ንጹሃን ሕጻንት የሚታሰቡበት አመታዊ በዓል በታኅሳስ 19/2014 ዓ.ም በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቲውተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት ከሄሮድስ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ቀን ድረስ ስላሉ ንጹሃን ሕጽናት ላይ ሰለሚከሰተው ግፍ ያወሱ ሲሆን ዛሬም ቢሆን ሕጻናትን ከአዳዲሶቹ ሄሮድሳዊያን መከላከል ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን   

"በዘመናችን ያሉት አዲሶቹ ሄሮድሳዊያን ሕጻናትን በባርነት በመያዝ ጉልበታቸውን በመበዝበዝ፣ በሴተኛ አዳሪነት እና ለጥቃት በመዳረግ፣ በጦርነት እና በግዳጅ የተሰደዱ ሕፃናትን ንፁህነታቸውን መመስከር ይኖርብናል፣ ለእነዚህ ሕጻናት ዛሬ አብራችሁን ልትጸልዩ እና ስለነሩስ መብት ልትሟገቱ ይገባል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ሕፃኑን ኢየሱስን ለማጥፋት በማሰብ በንጉሥ ሄሮድስ የተገደሉትን የቤተልሔም ልጆችን ለማስታወስ ለዛሬው የቅዱሳን ንጹሐን የሥርዓተ አምልኮ መታሰቢያ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  @Pontifex በተሰኘው የቲውተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት ተናግረዋል። ኢየሱስ፣ መሲሕ እና የእስራኤል አዲስ ንጉሥ እንደሆነ በነቢያት እንደ ተነገረም ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

152 ሚሊዮን ታዳጊዎች ለጉልበት ሥራ ተዳርገዋል።

ዛሬ ግን ልክ እንደ ትናንቱ ልክ እንደ ሄሮድስ ገና ብዙ እና ብዙ ንጹሃን ሕጻናትን ለማጥፋት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች አሉ። የሚያስከትለውንም አሉታዊ የሆነ ዋጋ ማየቱ በራሱ በቂ ነው። እ.አ.አ በመጋቢት 2021 ዓ.ም የታተመው ILO (አለም አቀፍ የሰራተኛ ድርጅት) ባወጣው የቅርብ ጊዜ ዘገባ መሰረት አሁንም 152 ሚሊዮን ህጻናት እና ጎረምሶች በአስገዳጅ የሥራ ሁኔታው ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ጉልበታቸውን ያለአግባቡ እየተበዘበዙ ይገኛሉ። ከእነዚህም ውስጥ 64 ሚሊዮን የሚሆኑት ሴቶች እና 88 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ወንድ ህጻናት ይገኙበታል፣ እነዚ ሕጻናት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ሰለባዎች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ግማሾቹ 73 ሚሊዮን የሚሆኑት ጤናቸውን፣ ደህንነታቸውን እና የሞራል እድገታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ አደገኛ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዳሉ። ብዙዎቹ የሚኖሩት በሕይወት ለመኖር በሚታገሉባቸው ጦርነቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች በተጎዱት አውድ ውስጥ ነው። ሌሎቹ ደግሞ ሕጻናት ወታደሮች ሆነው በጦርነቱ ውስጥ ይሳተፋሉ።

"የሞት ነጋዴዎች" የሕጻናትን ንጽህና ይውጣሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም ድምጻቸውን ያሰሙበት አስደናቂ እና ተቀባይነት የሌለው ክስተት በዚያው ዓመት ታኅሣሥ 28/2016 ዓ.ም ይፋ በሆነው እና ለጳጳሳት በላኩት ደብዳቤ ሊቀ ጳጳሳት ሹማምንትን በመጋበዝ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን "ከሚውጧቸው" አደገኛ ከሆኑ ድርጊቶች በሙሉ ለመከላከል ድፍረት እንዲኖራቸው መጋበዛቸው ይታወሳል። በሺህ የሚቆጠሩ ልጆቻችን በሽፍቶች፣ በማፍያዎች እና በሞት ነጋዴዎች እጅ መውደቃቸውን ጳጳሱ አስታውሰዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትምህርት ሳይማሩ የሚኖሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናትን፣ ‹‹በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች››፣ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናት ጉልበት መበዝበዝ ‹‹በግዳጅ በማፈናቀል ከአገራቸው ውጪ እንዲኖሩ የተገደዱ››፣ በምግብ እጦት የሚሞቱ ሕጻናትን እና ለባርነት እና ልጉልበት ብዝበዛ የተዳረጉትን፣ ያለ አቅማቸው መሳሪያ እንዲታጠቁ የተገደዱ ሕጻናትን ጠቅሰዋል።

ዳግመኛ እነዚህ ግፎች መደገም አይኖርባቸውም!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ መልእክታቸው የዩኒሴፍን ግምት ጠቅሰው እንደ ጻፉት ከሆነ "የዓለም ሁኔታ ካልተቀየረ በስተቀር እ.አ.አ በ 2030 ዓ.ም 167 ሚሊዮን ሕጻናት በአስከፊ ድህነት ውስጥ እንደ ሚኖሩ የገለጹ ሲሆን ከአምስት አመት በታች የሆኑ 69 ሚሊዮን ህጻናት በ 2030 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት እንደ ሚለዩ እና 60 ሚሊዮን ህጻናት ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እድል እንደ ማያገኙ ገልጸዋል። ስለዚህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተማጽኖ "እነዚህ አሰቃቂ ድርጊቶች በመካከላችን እንዳይከሰቱ ሁላችንም ቁርጠኝነታችንን ማደስ ይኖርብናል” በማለት ገልጸዋል።

29 December 2021, 12:21