ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግሪክ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስገኑ። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግሪክ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስገኑ። 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግሪክ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስገኑ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግሪክ ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል አድናቆታቸውን ገልጸው “ምስጋና” የክርስቲያን እምነታችን እና ሕይወታችን እምብርት መሆኑን አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እሁድ ኅዳር 26/2014 ዓ.ም በአቴንስ ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ ሲያጠናቅቁ የግሪክ ሕዝብ ስላደረገላቸው አንክብካቤ እና ሞቅ ያለ አቀባበል ቅዱስነታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “አመሰግናለሁ” የሚለውን የግሪክ ቃል በመጠቀም የግሪክ ቋንቋ ለቤተክርስቲያን በሙሉ የክርስቶስን ስጦታ ለማጠቃለል ይቻል ዘንድ “ቁርባን” (ምስጋና) የሚለውን ቃል ለቤተክርስቲያን መሰጠቱን አክለው የገለጹ ሲሆን ለእኛ ክርስቲያኖች ምስጋና የእምነታችን እና የህይወታችን እምብርት ነው" ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

መንፈስ ቅዱስም “ከእኛ ከሁላችን እና ከምንሰራው ሁሉ ጋር እንዲሆን  ‘ቅዱስ ቁርባን’፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን የፍቅር ስጦታ እንዲያደርግልን መጸለይ ይኖርብናል ብለዋል።

ግሪክን በልቤ ውስጥ ይዤ ሄዳለሁ

በዚህ የአመስጋኝነት መንፈስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የግሪክ ሲቪል ባለ ሥልጣናትን እና የአገሪቱን የካቶሊክ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞውን በማዘጋጀት ላደረጉላቸው ግብዣ እና እገዛ አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን በቀጣይም ህዝቡ ያሳየውን አሳቢነቱንና ተቆርቋሪነቱን ቅዱስነታቸው አመስግነዋል።

“ነገ ከግሪክ ወደ ጣሊያን እመለሳለሁ፣ ነገር ግን ግሪክን በልቤ ውስጥ ይዤ እመለሳለሁ ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ "በመታሰቢያዬና በጸሎቴ ሁሌም አስባችኋለሁ፣ እናንተም አባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ማለታቸው ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአቴንስ ከወጣቶች ጋር ያደረጉትን ውይይት ከአጠናቀቁ በኋላ ሰኞ ኅዳር 27/2014 ዓ.ም ማለዳ ወደ ሮም መመለሳቸው ተገልጿል።

05 December 2021, 14:37