ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማካሄድ ከቆጵሮስ ወደ ግሪክ መጓዛቸው ተገለጸ

35ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በቆጵሮስ እና በግሪክ ለማካሄድ ሐሙስ ኅዳር 23/2014 ዓ. ም. ከቫቲካን የተነሱት ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በቆጵሮስ ሲያደርጉ የቆዩትን ጉብኝት ፈጽመው ዛሬ ጠዋት ወደ ግሪክ መግባታቸው ታውቋል። በአገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ጠዋት ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ በቆጵሮስ ከሚገኝ ርናካ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሱት ቅዱስነታቸው ወደ አቴንስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ገደረሱት በገሪትይ የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ አምስት ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአቴንስ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር አቀባበል ከደረገላቸው በኋላ በአቴንስ ከተማ በሚገኝ ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥት አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል። ቅዱስነታቸው በዚህ ወቅት ከአገሪቱ ፕሬዚደንት ከክብርት ካቴሪና፣ ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአቶ ሳኬላሩፑሉ፣ ከሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና የልዩ ልዩ አገራት ዲኦሎማቶች ጋር መገናኘታቸው ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቀጥለውም፣ ከአቴንስ ከተማ ሊቀ ጳጳስ እና ከመላው የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳ ከብጹዕ አቡነ ሄርኖሙስ ጋርም መገናኘታቸው ታውቋል። በመቀጠልም ከሁለቱም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት አባቶች እና ተባባሪዎቻቸው መሰብሰባቸው ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ በሚያደርጉት የሐዋርያዊ ጉብኝታት መርሃ ግብር መሠረት ከሰዓት በኋላ በነበራቸው ጊዜ ከአገሪቱ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት፣ ካኅናት፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት፣ ከዘርዓ ክኅነት ተማሪዎች እና የትምህርተ ክርስቶስ መምህራን ጋር በአቴንስ ከተማ በሚገኝ የቅዱስ ዲዮናስዮስ ካቴድራል ውስጥ መገናኘታቸው ታውቋል። ከዚያም በአቴንስ ከተማ በሚገኝ የቅድስት መንበር እንደራሴ ጽሕፈት ቤት ከኢየሱሳዊያን ማኅበር አባላት ጋር የግል ስብሰባ አድረገዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በግሪክ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር መሠረት እሑድ ኅዳር 26/2014 ዓ. ም. በሌስቦስ ደሴት መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።   

04 December 2021, 17:46