ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለኢትዮጵያ እና ለሴራሊዮን ጸሎት አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን ጸሎት ከምእመናን ጋር በመቀባበል እንደ ሚደግሙ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በጥቅምት 28/2014 ዓ.ም የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበት ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለአለም በአስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት አሁን በኢትዮጲያ እና በሰራሊዮን ስላለው ሁኔታ ጸሎት ያደረጉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሁን በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በተለይም በኢትዮጵያ “ሰላማዊው የውይይት መንገድ እንዲሰፍን” ጸሎት ማደረጋቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በሴራሊዮን በነዳጅ ፍንዳታ ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን አስታውሰዋል። በስፔን ውስጥ ለሦስት አዳዲስ ብፁዓን ሰዎችም ክብር ሰጥቷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አድርገው ካጠናቀቁ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በተለይም በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በላይ በርካቶች ለሞቱበት እና እጅግ አሳሳቢ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ እያደርሰ ያለው ግጭት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ለነዚህ ለሚሰቃዩ ሕዝቦች እንድትጸልዩ እጋብዛለሁ፣ እናም ወንድማማችነት፣ ስምምነት እና ሰላማዊ የውይይት መንገድ እንዲሰፍን በድጋሚ ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል።

በሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን ዳርቻ ላይ በደረሰው የነዳጅ ፍንዳታ ምክንያት በእሳት አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎታቸውን ያቅረቡት ቅዱስነታቸው አርብ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም መገባደጃ ላይ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 98 ሰዎች ሲሞቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል።

07 Nov 2021, 10:45