ፈልግ

በአውርፓ በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን የሚያሳይ ምስል በአውርፓ በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን የሚያሳይ ምስል 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሜዲትራኒያን እስከ ቤላሩስ ድረስ ለሚገኙ ለሁሉም ስደተኞች ጸሎት አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 19/2014 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደ ሚያደርጉት ለአለም ባስተላለፉት መልእክት በቅርቡ የተለያዩ ማሕበራት አባላትን፣  የስደተኞች ተንከባካቢ ድርጅቶችን እና ጉዟቸውን በወንድማማችነት መንፈስ የሚጋሩ ሰዎች ጋር መገናኘታቸውን ቅዱስነታቸው አውስተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“ነገር ግን ስንት ስደተኞች በእነዚህ ቀናት ውስጥ እንኳን ለትልቅ አደጋ ተጋልጠዋል፣ ስንቶች በድንበራችን ህይወታቸውን እያጡ ናቸው” በማለት ጥያቄ በማንሳት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ብዙዎቹ የደርሰባቸውን መከራ እና የስቃይ ሁኔታ ዜና በመስማቴ አዝኛለሁ፣ በእንግሊዝ የውሃ መተላለፊያ መንገድ (ካናል) አቋርጠው ሊሄዱ ሲሉ የሞቱትን፣ በቤላሩስ ድንበር ላይ የሚገኙትን፣ ብዙዎቹ ህጻናት እና በሜዲትራኒያን ባህር ሰጥመው የሞቱትን ሰዎች ሁሉ አስባለሁ ብለዋል። ስለ እነርሱ በማስብበት ጊዜ  በጣም ብዙ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ ብለዋል።

ወደ ሰሜን አፍሪካ እንዲመለሱ የተደረጉ ስደተኞች መካከል፣ በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች የተያዙ ብዙ ስደተኞች እንዳሉ ስምቻለሁ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ወደ ባርነት ሕይወት ውስጥ እንደ ሚያስገቧቸው የተናገሩ ሲሆን በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች በጸሎቴ ከእነርሱ ጋር እንደ ሆንኩኝ ላረጋግጥ እወዳለሁ፣ በጸሎት እና በተግባር ከልቤ ሁል ጊዜ ወደ አንተ እንደምቀርብ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል። ሁሉንም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች ተቋማትን በተለይም አለማቀፉ የካሪታስ ኤጀንሲዎችን እና ስቃያቸውን ለማቃለል ቁርጠኛ የሆኑትን ሁሉ አመሰግናለሁ ብለዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት አስተዋፅዖ ለሚያደርጉት ሰዎች በተለይም የሲቪል እና ወታደራዊ ባለስልጣናት መግባባት እና ውይይቶች በማደረግ በመጨረሻ በማንኛውም ዘርፍ ስደተኞችን ለመርዳት የሚደርገውን ጥረት እንዲያሸንፉ እና የእነዚህን ሰብአዊነት የሚያከብሩ መፍትሄዎችን እና ጥረቶችን እንዲያደርጉ ልባዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል። እባካችሁን ለአንድ አፍታ ስደተኞችን እና ስቃያቸውን እናስብ እና በጸጥታ አብረን ከእነርሱ ጋር እንሁን ካሉ በኋላ ለአፍታ ያህል የሕሊና ጸሎት ከምዕመናን ጋር አድርገዋል።

በመቀተል ከጣሊያን እና ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ምዕመናን በሙሉ ሰላምታ ያቀረቡ ሲሆን የተለያዩ አገራት ባንዲራዎችን እየተመለከትኩኝ እገኛለሁ፣ ለቤተሰቦች፣ የሰበካ ቡድኖች እና ማህበራት ሁሉ ሰላምታዬን ለማቅረብ እወዳለሁ በተለይ ከምስራቃዊ ቲሞር ለመጡ ምእመናን ሰላምታዬን አቀርባለሁ ያሉ ሲሆን ለሁሉም መልካም እለተ ሰንበት እንዲሆን ከተመኙ በኋላ እና በተጨማሪም መልካም የስብከተ ገና ወቅት ጉዞ እንዲሆን ተመኝተው እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይን አትዘንጉ” ካሉ በኋላ ሐዋርያው ቡራኬያቸውን ሰጥተው መልክታቸውን አጠናቀዋል።

28 November 2021, 12:41