ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የፍልስጤም ግዛት ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የፍልስጤም ግዛት ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከፋልስጤም ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትላንት ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም በቫቲካን ከፍልስጤም ግዛት ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ተገናኝተው በግል የተወያዩ ሲሆን በፍልስጤም እና በእስራኤል መካከል ቀጥተኛ ውይይት እንደሚያስፈልግ የተወያዩ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም የሰላም መፍትሄ ተብሎ የቀረበውን የሁለቱን አገራት ሉአላዊነት የሚያረጋግጥ የሁለት ሀገር መፍትሄን እንዲተገብሩ ቅዱስነታቸው ምክረ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም መሰረት እስራኤል የአይሁዳዊያን፣ ፍልስጤም ደግሞ የፍልስጤማዊያን ሉአላዊ አገር መሆናቸው ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንደ ሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ሁለቱም ባደረጉት ውይይት አረጋግጠዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የፍልስጤም ፕረዚዳንት ማሃውድ አባስ በቫቲካን ውስጥ በግል ተገናኝተው መወያየታቸውን የቅድስት መንበር የዜና አውታር ሐሙስ ዕለት አስታውቋል።

ይህንን በተመለከተ የቅድስት መንበር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ውይይታቸው “አክብሮታዊ” እና በፍልስጤም እና በቅድስት መንበር መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት አጽንኦት የሰጠ እንደ ነበረ ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሰው ልጆችን ወንድማማችነት እና በሰላም አብሮ የመኖር አስፈላጊነትን እንዲሁም በቅድስት ሀገር የሁለት መንግስታት የመፍትሄ ሃሳብ ላይ እንደተናጋገሩ መግለጫው አክሎ ገልጿል።

የሁለት-ግዛት መፍትሄ

በእስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን መካከል ያለውን የሰላም ሂደት በተመለከተ የሁለት ሀገር መፍትሄን ለማምጣት ቀጥተኛ ውይይትን ለማደርግ የሚያስችሉ ውይይቶች ለማድረግ ይቻል ዘንድ የሚያስችሉ ተግባራትን እንደገና ማንቃት አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው የተናጋገሩ ሲሆን በተጨማሪም ይህ ተግባር በአለም አቀፉ ማህበረሰብ በኩል የበለጠ የተጠናከረ ጥረት መታገዝ እንዳለበት መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ፕረዚዳንት አባስ “ኢየሩሳሌም በሁሉም ዘንድ እውቅና ማግኘት አለባት የግጭት ስፍራ ሳትሆን ነገር ግን ደረጃዋን በሚመጥን መልኩ እና ከታሪክ አኳያ ለሦስቱም የአብርሃም ልጆች ሃይማኖቶች ቅድስት ከተማ በመሆን ማንነቷን እና ሁለንተናዊ እሴቷን ማስጠበቅ አለባት፣ ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ መታወቅ አለበት” በማለት መነጋገራቸውን ከቅድስት መንበር የተሰጠው መግለጫ አክሎ ገልጿል።

በመቀጠልም ሁለቱ መሪዎች ስለ ሰላም መስራት፣ የጦር መሳሪያ መጠቀምን ማስወገድ እና ሁሉንም አይነት ጽንፈኝነት እና የአይማኖት አክራሪነትን መዋጋት እንደ ሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ፕረዚደንት አባስ ከቫቲካን ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እና ከአገሮች ጋር የሚደርገውን ግንኙነቶች የሚከታተለው የቅድስት መነበር ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ከሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውም ተገልጿል።

ስጦታ መለዋወጥ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወዳጃዊ ግንኙነትን የሚያመለክት የነሐስ ሐውልት ለአቶ አባስ በስጦታ አበርክተዋል። ከበስተጀርባ የሚታየው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ የሚገኘው ስደተኞች የሚጓዙበት ጀልባ የሚያመልክት ምስል የያዘ ስዕል የታተመበት ሲሆን “እጃችንን በሌላ እጃችን እንሙላ” የሚሉት ቃላቶች በሰሌዳው ግርጌ ላይ ተለጥፈዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ለፕሬዚዳንቱ የጳጳስ ሰነዶች እና ለዘንድሮው የሰላም ቀን ያስተላለፉትን መልእክት ግልባጭ፣ የሰው ልጅ ወንድማማችነት ሰነድ ያበረከቱላቸው ሲሆን ፕረዚደንት አባስ ለሊቀ ጳጳሱ በቤተልሔም የሚገኘውን ክርስቶስ የተወለደበት ቤተክርስቲያንን የሚያመለክት መጽሐፍ እና በአምበር ውስጥ ስለሚገኘው ቤተመቅደስ የሚዘግበውን መጽሐፍ በስጦታ መልክ ለቅዱስነታቸው ሰጥተዋል።

05 November 2021, 12:16