ፈልግ

በስዋዚላንድ የተቀሰቀሰው አመጽ በስዋዚላንድ የተቀሰቀሰው አመጽ  

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በስዋዚላንድ የጋራ ውይይት እንዲደረግ፣ ሰላም እና እርቅም እንዲወርድ ጠየቁ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ እሑድ ሰኔ 27/2013 ዓ. ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እና መንፈሳዊ ነጋዲያን ደቡብ አፍሪካዊት አገር ከሆነች ስዋዚላንድ አሳዛኝ ዜና የሚደርሳቸው መሆኑን ገልጸው፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ወገኖች የጋራ ውይይቶችን በማካሄድ የተቀሰቀሰው አመጽ ቆሞ መረጋጋትን፣ ሰላምን እና እርቅን ለማምጣት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀው፣ የአገሪቱ መሪዎች ከሕዝብ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጡ አደራ ብለዋል።  

05 July 2021, 19:55