ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የልባችንን ሥነ-ምህዳር” ማዳበር አለብን አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ በሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ምያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሐምሌ 11/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ከማርቆስ ወንጌንል 6፡30-34 ላይ ተወስዶ በተነበበውና “ሐዋርያትም በኢየሱስ ዙሪያ ተሰብስበው የሠሩትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት”  በሚለው ቃል ላይ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን “የልባችንን ሥነ-ምህዳር” ማዳበር አለብን ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው የስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 6: 30-34) ውስጥ የምንመለከተው የኢየሱስ አመለካከት ሁለት አስፈላጊ የሕይወት ገጽታዎችን እንድንገነዘብ ይረዳናል። የመጀመሪያው እረፍት ነው። የሚሶዮናዊ ተልእኮ ሥራ አጠናቀው የተመለሱ ሐዋርያት በደስታ ያደረጉትን ሁሉ መዘርዘር የጀመሩ ሲሆን ኢየሱስ “እስቲ ብቻችሁን ከእኔ ጋር ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ እንሂድና ጥቂት ዕረፉ” በማለት ሐዋርያቱን ይጋብዛቸዋል። የእረፍት ግብዣ ያቀርብላቸዋል።

በዚህም ኢየሱስ ጠቃሚ ትምህርት ይሰጠናል። ምንም እንኳን በስብከታቸው አስደናቂ ነገሮች የተነሳ የደቀ መዛሙርቱን ደስታ በማየቱ ደስ ቢለውም ፣ ለእነሱ ምስጋና ወይም ጥያቄ ለማቅረብ ጊዜ አላጠፋም።ይልቁንም እሱ ስለ አካላዊ እና ውስጣዊ ድካማቸው ያሳስባል። እናም ለምን ይህን ያደርጋል? ምክንያቱም እሱ ለእኛም ቢሆን ሁል ጊዜ እዚያ በድብቅ የሚጠብቀንን አደጋ እንድናውቅ ለማደረግ ስለሚፈልግ ነው ፣ ነገሮችን በማከናወን እብደት ውስጥ ገብተን የመያዝ አደጋ ፣ በጣም አስፈላጊ እና የምናገኛቸው ውጤቶች ባሉበት የእንቅስቃሴ ወጥመድ ውስጥ የመውደቅ አደጋ እና ፍጹም ተዋንያን የመሆን ስሜት ለማስወገድ ፈልጎ ነበር ይህንን ግብዣ ያቀረበላቸው። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስንት ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ይከሰታሉ - እኛ ስራ ላይ ነን ፣ እንሮጣለን ፣ ሁሉም ነገር በእኛ ላይ የተመረኮዘ ነው ብለን እናስብና በመጨረሻም ኢየሱስን ችላ የማለት ስጋት ውስጥ እንገባለን፣ ሁሌም እራሳችንን ማዕከል እናደርጋለን። ለዚህም ነው ደቀ መዛሙርቱን እነርሱ ብቻ ትንሽ ከእሱ ጋር እንዲያርፉ የሚጋብዘው። እሱ አካላዊ እረፍት ብቻ ሳይሆን ለልብም እረፍት ነው። እራሳችንን “መንቀል” በቂ አይደለም ፣ በእውነት ማረፍ ያስፈልገናል። እና ይህን እንዴት እናደርጋለን? ይህንን ለማድረግ ወደ ነገሮች ልብ መመለስ አለብን -መቆም፣ ዝም ማለት ፣ ከሥራ ብስጭት ይልቅ ዘና ወደ ሚያደርገን እና ወደ እብደት ላለመሄድ መጸለይ አለብን። ኢየሱስ የሕዝቡን ፍላጎት ችላ አላለም፣ ነገር ግን በየቀኑ ከማንኛውም ነገር በፊት ፣ በጸሎት ፣ በዝምታ ፣ ከአብ ጋር ያለውን ቅርበት ለማጠናከር ገለል ወዳለ ቦታ መሄድ ነበረበት። የእሱ - ትንሽ ጊዜ ማረፍ - የሚለው የእርሱ ግብዣ አብሮን ሊሄድ ይገባል። ወንድሞችና እህቶች ውጤታማ መሆን አለብን ብለን ከምናደርገው ሩጫ እንጠንቀቅ ፣ በአጀንዳዎቻችን የታያዘውን ሽኩቻ እናቁም። እንዴት ማረፍ እንዳለብን ፣ ሞባይላችንን በማጥፋት ፣ ተፈጥሮን ለማሰላሰል ፣ ከእግዚአብሄር ጋር በመነጋገር እራሳችንን ለማደስ እንድንችል እንዴት መማር እንችላለን?

ሆኖም ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ እነርሱ እንደወደዱት ማረፍ እንደማይችሉ ይነግረናል። ህዝቡ እነሱን ለማግኘት ከሁሉም አቅጣጫ ወደ እነሱ ይጎርፋል። በየትኛውም ጊዜ ቢሆን እርሱ በርህራሄ ይነዳል። ርህራሄ የሚለው ቃል ሁለተኛው ገጽታ ነው፣ እሱም የእግዚአብሔር ዘይቤ ነው። የእግዚአብሔር ዘይቤ መቅረብ ፣ ርህራሄ እና ምሕረት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “እርሱ ራራላቸው” የሚለውን ይህንን ሐረግ በወንጌሉ ውስጥ ስንት ጊዜ እናገኛለን? ኢየሱስ ራሱን ለሰዎች ወስኖ እንደገና ማስተማር ይጀምራል (ማርቆስ 6፡ 33-34)። ይህ እርስ በእርሱ የሚቃረን ይመስላል ፣ ነገር ግን በእውነቱ የሚቃረን ነገር አይደለም። በእውነቱ በችኮላ እንዲወሰድ የማይፈቅድ ልብ ብቻ ነው የመንቀሳቀስ ችሎታ ያለው፣ ማለትም በራሱ እና በሚከናወኑ ነገሮች እንዲጠመድ ባለመፍቀድ እና ስለ ሌሎች ሰዎች ቁስሎች እና ፍላጎቶቻቸው ያውቃል። ርህራሄ ከማሰላሰል የተወለደ ነው። በእውነት ማረፍ የምንማር ከሆነ የእውነተኛ ርህራሄ ችሎታ እናዳብራለን። የማሰላሰል አስተሳሰብን ካዳበርን ሁሉንም ነገር ለመያዝ እና ለመበላት የሚፈልጉ እነዚያ ርኩስ አመለካከት የሌላቸውን ተግባራትን እናከናውናለን፣ ከጌታ ጋር ከተገናኘን እና የራሳችንን ጥልቅ የሆነ ክፍል ካላደነቅን ማድረግ ያለብን ነገሮች እንዳናከናውን የሚያደርጉን ነገሮች ኃይል አይኖራቸውም። እኛ እረፍ ማደረግ ያስፈልገናል፣ በማረፍ፣ በማሰላሰል እና በርህራሄ የተዋቀረ “የልብ ሥነ-ምህዳር” ያስፈልገናል። ለዚህም የበጋውን ጊዜ እንጠቀምበት! ትንሽ ሊረዳን ይችል ይሆናል።

እናም አሁን ዝምታን ፣ ጸሎትን እና ማሰላሰልን ለእኛ ያስተማረች፣ እኛ ልጆቿ ለሆንን ሰዎች ሁልጊዜ በርኅራኄ ቅርብ ወደ ሆነችው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንጸልይ።

18 July 2021, 10:36

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >