ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትምህርት ቤቶች ለጋስ እና በእኩልነት የምያምን ህሊናን መገንባት አለባቸው አሉ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትምህርት ቤቶች ለጋስ እና በእኩልነት የምያምን ህሊናን መገንባት አለባቸው አሉ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትምህርት ቤቶች ለጋስ እና በእኩልነት የምያምን ህሊናን መገንባት አለባቸው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለላቲን አሜሪካ የኢየሱሳውያን ትምህርት ቤቶች ፌዴሬሽን (FLACSI) በ 20 ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ላይ የእንኳን አደረሳችሁ የቪዲዮ መልእክት መላካቸው የተገለጸ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ለጋስ እና በእኩልነት የምያምን ህሊናን መገንባት አለባቸው ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች አንድ ሰው የራሱን ቁስሎች ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ሰዎች ቁስሎች የሚፈውስባቸው “እንኳን ደህና መጣችሁ” በማለት ሁሉንም የሰው ልጆች ያለ ልዩነት የምንቀበልባቸው ስፍራዎች ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።  በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች አንድ ሰው “የዘመኑን ምልክቶች” ለማንበብ እና ለመለየት የሚማርባቸው ቦታዎች እንዲሆኑ ይፈለጋል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ነገር ግን ከሁሉም በላይ በሰዎች መካከል ያለው አሳፋሪ የሆነ ያለተመጣጠነ እድገትን የሚፈጥሩ አንዳንድ የእድገት እና የፍጆታ ሞዴሎች ላይ ወሳኝ አመለካከት እንዲያዳብሩ ማደረግ የሚችሉ የትምህርት ዓይነቶችን የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው መስጠት እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አክለው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የ 20 ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ለላቲን አሜሪካ የኢየሱሳውያን ትምህርት ቤቶች ፌዴሬሽን (FLACSI) ሐሙስ ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ባስተላለፉት መልእክት ተስማሚ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ራዕይቸውን ገልጸዋል። እ.አ.አ በ 2001 ዓ.ም የተጀመረው በ 19 የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን ሀገሮች ውስጥ በኢየሱሳዊያን ማሕበር የሚተዳደሩ ወደ 92 የሚሆኑ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ያቀፈ ፌደሬሽን ሲሆን ፌዴሬሽኑ የተመሰረተው በኮሎንቢያ ዋና ከተማ በቦጎታ እንደ ነበረም ይታወሳል። የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ያቀፈ ፌደሬሽን (FLACSI) የተጀመረው በላቲን አሜሪካ ውስጥ በሚገኙ የማሕበራት አለቆች አማካይነት ሲሆን ይህም በአጠቃላይ ፖሊሲዎች ፣ ስትራቴጂዎች እና ትግበራዎች በመላው አውታረ መረቡ ውስጥ በትምህርት አገልግሎት እና በክልሉ ማህበራዊ ለውጥ እንዲመጣ በማበረታታት እየሰራ የሚገኝ ፌደሬሽን ነው።

ለሌሎች ሕይወት መስጠት

የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእስፓኒሽ ቋንቋ ባስተላለፉት መልእክት “ከሌሎች እና ከፍጥረት ጋር እንድንገናኝ የሚያስተምረንን የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ያቀፈ ፌደሬሽን (FLACSI) ስር የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ይህንን እውን ለማደረግ ከራሳቸው አልፈው መውጣት ይኖርባቸዋል” በማለት ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም “ከአቅመ ደካሞች ጋር፣ ከድሆች እና ከተገለሉ ሰዎች ጋር ለመገናኘት” መውጣት ይኖርብናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  ት / ​​ቤቶቻችን የተመሰረቱባቸውን አላማ እና ተልእኮ ለመወጣት ከልብ ሊሰሩ ይገባል፣  እናም ህይወት እያደገ እና እየበሰለ ሊሄድ የሚችለው እኛ ለሌሎች ህይወት በሰጠን መጠን ነው ብለዋል።

“ራስ ወዳድነትን” ማስወገድ

ስለሆነም ሌሎችን በደስታ የሚቀበሉ ትምህርት ቤቶች በቃላት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በተግባር በሮቻቸውን ለሁሉም የሰው ልጆች ክፍት ማደረ ይኖርባቸዋል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተለይም ደግሞ ለድሆች ክፍት የሆነ እና ሁሉም የሰው ልጆች የሚገናኙበት ሥፍራ ሊሆኑ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል። ትምህርት ቤቶች አንድ ሰው ብዙ ሊማርበት የሚችልበት ልዩ መብት የሆነውን የወንጌልን ጥበብ ማሳየት አለባቸው በማለት አክለው የገለጹት ቅዱስነታቸው ትምህርት ቤቶች “ራስ ወዳድ የሆኑ ሊዕቃን” የሚፈጠሩበት ቦታ ሳይሆን ነገር ግን ትምህርት ቤቶች “ሁሉም ሰው አብሮ የሚኖርባቸው ፣ ሁሉም ነገር የተገናኘ መሆኑን በማወቅ በወንድማማችነት የሚኖርባቸው” ስፍራዎች መሆን አለባቸው ብለዋል። በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት አንድ ሰው “ወንድማማችነት በመጀመሪያ ፣ የሞራል ግዴታ አለመሆኑን” ማስታወስ ይኖርበታል” ያሉ ሲሆን ይልቁንም ወንድማማችነት “በቤተሰብ ውስጥ እንደ ወንድም እና እህት ሆነን የተፈጠረ የሰው ዘር እና የፍጥረት ሁሉ ተጨባጭ ማንነት ” ምልክት ነው ብለዋል።

ሕሊናን ማነጽ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አክለው እንደ ገለጹት የካቶሊክ ትምህርት ቤቶችን ያቀፈ ፌደሬሽን (FLACSI)  “የዘመኑን ምልክቶች እንዲያስተውሉ ፣ የዘመኑ ምልክቶችን እንዲያነቡ ፣ የአንድን ሰው ሕይወት ስጦታ መሆኑን በመረዳት ለሌሎች ማካፈል እንዳለብን መማር የምንችልበት ስፍራዎች እንዲሆኑ መሥራት ይኖርብናል” ብለዋል። አክለውም “በልማት ፣ በምርት እና በፍጆታ ሞዴሎች ላይ እጅግ በጣም ብዙ የአለም ህዝብ እንዲሰቃይ በሚያደርግ አሳፋሪ ልዩነቶችን የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ይፈታሉ” የሚል ወሳኝ አመለካከት እንዳላቸው እና ተስፋ እንደ ሚያደርጉ ገልጸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አንዳሉት “እንደምትመለከቱት ምኞቴ ት / ቤቶቻችሁ ሕሊና እንዲኖራቸውና ሕሊና እንዲፈጥሩ ነው” በማለት የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ያቀፈ ፌደሬሽን አባልት የተናገሩ ሲሆን “ደቀመዛሙር እና ሚስዮናዊ ትምህርት ቤቶች” እንዲሆኑ “እምነት እና ፍትህን የምታስፋፉ” ትምህርት ቤቶች እንድትሆኑ እፈልጋለሁኝ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

11 June 2021, 15:05