ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስርት ከሆኑት ከክቡር አቶ አንቶኒ ብሊንኬን ጋር ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስርት ከሆኑት ከክቡር አቶ አንቶኒ ብሊንኬን ጋር  

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ለአሜሪካ ሕዝብ ያላቸውን ፍቅር እና ትኩረት ገለጹ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ትናንት ሰኔ 21/2013 ዓ. ም ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑት ከክቡር አቶ አንቶኒ ብሊንኬን ጋር በቫቲካን ተገናኝተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስርት ከሆኑት ከክቡር አቶ አንቶኒ ብሊንኬን ጋር ያደረጉት ቆይታ መልካም እንደነበር የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይሬክተር ክቡር አቶ ማቴዎ ብሩኒ ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ከአቶ አንቶኒ ብሊንኬን ጋር ባደረጉት የአርባ ደቂቃ ቆይታ እ. አ. አ በ2015 ዓ. ም ወደ አሜሪካ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማስታወስ መልካም አጋጣሚ ያገኙ መሆኑን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይረክተር ክቡር አቶ ማቴዎ ብሩኒ ገልጸው፣ በዚህ አጋጣሚ ቅዱስነታቸው ለአሜሪካ ሕዝብ ከፍተኛ ፍቅር እንዳላቸው፣ ጥንቃቄም እንደሚያደርጉለት ገልጸዋል ብለዋል።

አቶ ብሊንኬን በጣሊያን ውስጥ የነበራቸው ቆይታ

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ አንቶኒ ብሊንኬን በአውሮፓ ቆይታቸው ጀርመንን እና ፈረንሳይን የጎበኙ ሲሆን ከሰኔ 20/2013 ዓ. ም. ጀምረው በጣሊያንን ውስጥ ጉብኝት ሲያደርጉ መቆየታቸው ታውቋል። አቶ አንቶኒ ብሊንኬን በጣሊያን ሮም ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ጸረ-ዳኢሽ የሚኒስትሮችን ስብሰባ ለይ ተገኝተዋል። በሮም ከተማ በተካሄደው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኙት አቶ ብሊንኬን የጣሊያንን አቋም በመደገፍ የአፍሪካን ሕዝቦች የሚያበረታታ ማኅበራዊ ድጋፎችን ለማድረግ መንግሥታቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፍሪካ ውስጥ ራሱን “እስላማዊ መንግሥት” ብሎ የሚጠራው ቡድን ለሚያስከትለው ጥፋት የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አቶ ብሊንኬን ተናግረው፣ ምክንያቱን ሲገልጹ በተዋጊዎች መካከል የተመዘገበ የታዳጊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ነው ብለዋል። አክለውም እስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎችን በጋራ ለመዋጋት የተሰረገው ጥረት መልካም ውጤቶችን ማስገኘቱን በድጋሚ ገልጸዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አንቶኒ ብሊንኬን በጣሊያን መሪነት የሚካሄደውን የG20 አገሮች ስብሰባን በማቴራ ከተማ ላይ የሚካፈሉ መሆናቸው ታውቋል። በዚህ ስብሰባ ወቅት የአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚወያዩባቸው የመጀመሪያ ርዕሠ ጉዳዮች ጤናን፣ ዘላቂ እድገትን፣ የአየር ንብረት ለውጥ መዋጋትን እና ዓለም አቀፍ ንግድን የሚመለከቱ መሆኑ ታውቋል። የሁለተኛ ደረጃ የመወያያ ርዕሠ ጉዳይ ከአፍሪካ አህጉር ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚመለከት መሆኑ ታውቋል። 

29 June 2021, 16:39