የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የግንቦት ጸሎት ዓላማ ‘ለፋይናንሱ ዓለም’ ጸሎት እንዲደረግ ማቅረባቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ እንደ ሚያቀርቡ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለእዚህ ለያዝነው የግንቦት ወር ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ በዓለም ደረጃ የገንዘብን ፍሰት የሚቆጣጠሩ እና በገንዘብ ልውውጥ የሚደረጉ ገበያዎች ውስጥ ወሳኝ የሆነ ገደብ የሚያደርጉ እና ተራ ሰዎችን ከፍይናንስ አግልግሎት ውጭ የሚያደርጉ ተቋማት ከእዚህ ተግባራቸው እንዲላቀቁ ጸሎት ይደረግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“የሥራ እድልን የሚፈጥረው እውነተኛው ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት ቀውስ ውስጥ ይገኛል” በማለት ወራዊውን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ ባደረጉበት ወቅት የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለግንቦት ወር 2013 ዓ.ም ያቀረቡትን የፀሎት ሀሳባቸውን በዚህ ማስጠንቀቂያ መጀመራቸው ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በቅርቡ የግንቦት ወር የጸሎት ሐሳብን በተመለከተ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት  “የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቪዲዮ” ውስጥ በተራ ሰዎች ሕይወት መካከል ያለው ግንኙነት አስቸጋሪ ወደ ሆነ ቀውስ ውስጥ እየገባ እንደ ሆነ እና በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የፋይናንስ ገበያዎች ውስጥ የሚታየው ቀውስ አሳዛኝ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የፋይናንስ ስርጭት በመልኩ ሆነ በዓይነቱ እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት የሥራ እድል እየጨመረ ከመምጣት ይልቅ “አሁን ስንት ሰው ሥራ አጥ ነው!”  የፋይናንስ ገበያዎች ግን ከእዚህ ቀደም እንደነበሩት በጭራሽ አይደሉም፣ በቀድሞ ጊዜ ከነበረው ደረጃ እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱን፣ በተቃራኒው ደግሞ የሥራ ዕድል እየተቀዛቀዘ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

ደንብ ያስፈልጋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ከፍተኛ ፋይናንስ ቁጥጥር ካልተደረገበት እና ለብቻው የሚተው ከሆነ “በተለያዩ የገንዘብ ፖሊሲዎች የሚመራ ንፁህ መላምት” እንደሚሆን ያሳሰቡ ሲሆን “ይህ ሁኔታ ዘላቂነት የለውም። እናም አደገኛ ነው”ብለዋል። ድሆች በዚህ ሥርዓት አሳዛኝ ውጤት እንዳይጎዱ ፣ የገንዘብ ግምቶች በጥንቃቄ መስተካከል አለባቸው” በማለት አክለው ገለጸዋል።

ከዚያ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “መላምት” በሚለው ቃል ላይ አፅንዖኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ፍትህ እና ኢኮኖሚ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ፋይናንስ የሰዎችን ፍላጎት ለማርካት መሣርያ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ተስፋቸውን ገልጸዋል። ፋይናንስ ህዝቡን ለማገልገል እና የጋራ ቤታችንን ለመንከባከብ የአገልግሎት ዓይነት እና መሳሪያ ሊሆን ይገባል” ያሉ ሲሆን በተጨማሪም የበለጠ ፍትሃዊ እና ዘላቂነት ያለው እና ማንንም ወደ ኋላ የማይተው አንድ ዓይነት ኢኮኖሚን ​​እንዲያስተዋውቁ ሁሉንም አሳስበዋል።

“እኛ ይህንን ማድረግ እንችላለን!” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አረጋግጠዋል። በገንዘብ አያያዝ ላይ ያሉት የፋይናንስ ገበያን በማስተካከል ዜጎችን ከአደጋው ለመጠበቅ ከመንግሥታት ጋር እንዲሠሩ እንጸልይ ብለዋል።

በእኩልነት ሁላችንም እንደግ

በየወሩ “የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቪዲዮ” የሚዘጋጀው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም አቀፍ የጸሎት ኔትዎርክ የጸሎቱን ዓላማ በማጀብ ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ቅዱስ አባታችን ለተንሳፈፉ ገበያዎች ያላቸውን ስጋት በ ‹Covid-19› ወረርሽኝ ከተባባሰው የእኩልነት መዛባት ጋር አገናኝቷል በማለት ገልጿል።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ አንስቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሥራ ውጭ ሆነዋል ወይም  ግሎባል ጠቅላላ ምርት (ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት) መግለጫ እንደ ሚያመለክተው እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል ተነፍገዋል።

ፋይናንስ ለጋራ ጥቅም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለዓለም ባንክ እና ለዓለም የገንዘብ ድርጅት በቅርቡ በጻፉት ደብዳቤ የኅብረተብ ክፍሎች ውስጥ እጅግ ደሃ የሚባሉ ሰዎች ከፋይናንስ ገበያዎች ውጪ እንዲደረጉ ወይም እንዳይካተቱ መደረጋቸውን በምሬት ገልጸዋል። የፋይናንስ ገበያን ሕግ በድጋሚ መከለስ የሚገባበት ምክንያት “ለማህበረሰብ ግቦች” እና ለጋራ ጥቅም የሚሰሩ እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው መግለጻቸው ይታወሳል።

የፕሬስ መግለጫው እንዳመለከተው  “የገቢያ ነፃነት እና ንፁህ ግምቶች የማኅበራዊ ይዘትን አለመጣጣም ከግምት ስለማያስገቡ ይህን ዓይነቱን ችግር ሊፈቱት አይችሉም” በማለት በመልእክታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹ አስታውቋል። ይልቁንም መንግስታት በገንዘብ ገበያዎች እና ሞዴሎች “ሰብአዊ ክብርን ወደ መሃል” ለማስመለስ መሥራት አለባቸው የሚል እንድምታን የያዘ መልእክት ነው።

09 May 2021, 10:21