ለጋራ የመኖሪያ ቤታችን እንራራላት ለጋራ የመኖሪያ ቤታችን እንራራላት 

ለጋራ የመኖሪያ ቤታችን እንራራላት

በላቲን ቋንቋ “Laudato si” በአማርኛው ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርዕስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 24/2015 ዓ.ም ለንባብ ያበቁ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ የሆነበት 6ኛው ዓመት ግንቦት 16/2013 ዓ.ም ተዘከሮ ማለፉ ይታወሳል። በዚህ ጳጳሳዊ መልእክታቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ የዛሬ 6 አመት ገደማ ያፋ ያደርጉት ጳጳሳዊ መልእክት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ በዓለማችን ላይ የሚታየው የአየር ንብረት ለውጥ መንስሄ ምድራችንን ያለ አግባቡ በመበዝበዛችን፣ ከባቢ አየርን ሊበክሉ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን፣ ጋዞችን ወደ አከባቢ በመልቀቃችን በመሳሰሉ ጉዳዮች የተከሰተ እና የጋራ የመኖርያ ቤታችንን አደጋ ላይ የጣለ ክስተት በመሆኑ ክስተቱን ለመግታት ባለድርሻ አካላት የራስቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ ሲሆን የጋራ መኖሪያ ቤታችን ምን እየሆነች ነው? የፍጥረት ወንጌል፣ የሥነ ምህዳር ቀውስ ሥረ መሰረቱ የሰው ልጅ መሆኑን፣ የተቀናጀ የሥነ ምህዳር እንክብካቤ፣ የአቀራረብ እና የድርጊት መስመሮች፣ የስነ ምህዳር ትምህርት እና መንፈሳዊነት በተሰኙ አርዕስቶች ላይ ትንታኔ የሚሰጥ 6 ምዕራፎችን አቅፎ የያዘ ጳጳሳዊ መልእክት እንደ ሆነ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ለጋራ የመኖሪያ ቤታችን እንራራላት

ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በጋር በመሆን፣ እንዲሁም ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ማሕበረሰቦች አጋርነት በመፍጠር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለተፈጥሮ እንክብካቤ ይደረግ ዘንድ ዓለማቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደ ምትገኝ ይታወቃል። በመሆኑም “አማኝ ግለሰቦች እና የማኅበረሰብ ክፍሎች እያንዳንዳቸው ተፈጥሮን የመንከባከብ ጥሪያቸውን በድጋሚ የሚያድሱበትን አጋጣሚ በመፍጠር፣ የእዚህን ድንቅ የሆነ ተፈጥሮ ፈጣሪና እንድንከባከበው በአደራ ያስረከበንን እግዚኣብሔርን እንድናመሰግነው እና በቀጣይነትም ይህንን ተፈጥሮ ለመንከባከብ እንድንችል ይረዳን ዘንድ፣ በተጨማሪም በምንኖርባት ዓለም ላይ ላደረስነው ውድመት ይቅርታን ከእግዚአብሔር ዘንድ መለመን እንደ ሚገባን” ግንዛቤው እና ኖሃው እንዲኖረን ለማደረግ በርካታ ሥራዎችን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በማከናውን ላይ እንደ ምትገኝ ይታወቃል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከእዚህ በታች ያለውን የማጫወቻ ቁልፍ ይጫኑ!

አብያት ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ማኅበረሰብ እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ለገጸ-ምድራችን የወደ ፊት እጣ ፋንታ መጠበብ መጀመራቸው አበረታች ነገር ነው። በእርግጥ ባለፉት አስርተ-ዓመታት የሐይማኖት መሪዎች እና ልዩ ልዩ ተቋማት በምድራችን ላይ እየተከሰት የሚገኘውን ኋላፊነት የጎደለው ብዝበዛ ለብዙኋኑ አጋልጠው እንደ ነበረ ይታወሳል። በእዚህም ረገድ የቁስጥንጥንያው ፓትሪያርክ በርተሌሜዎስ ከእርሳቸው ቀደም ብለው የነበሩትን የፓትሪያርክ ዲሚትሪን ፈለግ በመከተል በተፈጥሮ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን አሳሳቢ ውድመት ኋጥያት መሆኑን እና ይህም በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ውድመት ሞራላዊ እና መንፈሳዊ ሥር መሰረቶችን እንደ ምያቃውስ መገለጻቸው ይታወቃል። ከተፈጥሮ ጋር ያለን ውህደት እዲጨምር እንዲሁም የአደጋው አሳሳቢነትን ለማጉላት በማሰብ ሥነ ምህዳርን መንከባከብ አስፈላጊ እንደ ሆነ የሚጠቁሙ ተግባራትን እና አስተምህሮዎችን መስጠት እንደ ሚገባ የሚታመን ሲሆን በተለይም ደግሞ በመስከረም 1 የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናት አምላክ የፈጠራቸውን ፍጥረታትን የሚያስቡበት ቀን በመሆኑ እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቅጣጠር በእየአመቱ ጥቅምት 4 የሚከበረው የቅዱስ ፍራንቸስኮ በዓልን ምክንያት በማደረግ በተቀናጀ መልኩ ለምድራችን እንክብካቤ ማደረግ ተገቢ መሆኑን ማስተማር እና መምከር ያስፈልጋል። በእዚህም ሳቢያ በዓለማችን በእዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ሥራዎች እንዲከናወኑ መንስሄ ከመሆኑም ባሻገር ፍታዊ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እዲኖር፣ ለድሆች ትኩረት እንዲሰጥ፣ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ኋላፊነት ተሰምቶት በተለይም ደግሞ የተለያዩ ሐይማኖት ተከታይ የሆነው የወጣቱ ትወልድ በአንድነት በእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲረባረብ ማነሳሳት ያስፈልጋል። ክርስቲያኖች ይሁኑ ክርስቲያን ያልሆኑ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎችም ጭምር የጋራ መጠልያ ቤታችን ለሆነችው ምድራችን ርኅራኄን እንዲያሳዩ እና የጋራ መኖሪ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን ማሳወቅ ይኖርብናል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ከእዚህ በመቀጠል በላቲን ቋንቋ “Laudato si” በአማርኛው ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርዕስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 24/2015 ዓ.ም ለንባብ ያበቁ ጳጳሳዊ መልእክት የተጠቀሱትን አብይት ጭብቶች በወፍ በረር እንደ ሚከተለው እናስቃኛችኋለን ተከታተሉን።

1.     ምድራችን በልቅሶ ላይ ናት

በእዚህ መልእክቴ ቀደም ሲል ያደረኩትን ንግግር በድጋሜ በማስታወስ “በእዚህ ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በመክራ ውስጥ የሚገኙ ድሆችን እና በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በድጋሜ ማስታወስ እፈልጋለሁኝ”። እግዚኣብሔር የተትረፈረፈ የአትክልት ሥፍራን ሰጠን፣ ነገር ግን እኛ ወደ ባድማነት እና የትርኪሚርኪ መጣያ፣ ወደ ተበከለ የቆሻሻ መጣያ ሥፍራነት ቀየርናት”። በምድራችን ስነ-ምዕዳር እና የተመጋጋቢነት ሂደት ላይ ኋላፊነት በጎደለው መልኩ እና በእራስ ወዳድነት መንፈስ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በግድየለሽነት ስሜት ወይም በዝምታ መመልከት አይኖርብንም። “ምክንያቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎች እየጠፉ በሚመጡበት ወቅት በመኖራቸው ምክንያት እነርሱን በማየት ለፈጣሪ የምንሰጠው ምስጋና እየቀነሰ ስለ ሚመጣ እና ይህንን የማድረግ መብትም ስለሌለን ጭምር ነው።

የሰው ልጆች በምያደርጉት እንቅስቃሴ ምክንያት የአለም ሙቀት መጨመሩ ይቀጥላል፣ እ.አ.አ. ባሳለፍነው 2015 ዓ.ም የነበረው የዓለማችን ሙቀት እስካሁን ከተመዘገቡት ሁሉ በጣም የላቀ ሲሆን እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም እና በተከታታይ ከእዚያ ቀጥሎ በሚገኙ አመታት ውስጥ ይህ ነገር በቀጣይነት እንደ ሚከሰት እሙን ነው። ይህም ጉዳይ በዓለማችን ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ሰደድ እሳት እና ያልተለመደ የአየር ንብረት ለውጥ እዲኖር እያደረገ ይገኛል። የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ለስደተኞች ፍሰት ቀውስ ከፍተኛ የሆነ ድርሻ አበርክቷል። በዓለም ውስጥ የሚኖሩ ድሆች ኋላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች አማካይነት ድህነት ከደቀንባቸው መከራ ባሻገር በአለም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከድጥ ወደ ማጡ እየወረዱ ይገኛሉ።

 የተመጣጠነ የስነ-ምዕዳር ሂደት እንደ ምያሳየው የሰው ልጆ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዳለው ነው። ስለዚህ ተፈጥሮን መበደል ማለት የሰው ልጆችን መበደል ማለት ነው። በተመሳሳይ መልኩ እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ የሆነ ተፈጥሯዊ እሴቶች አሉት ይህም ሊከበር ይገባዋል። “ምድራችን እና ድሆች እያሰሙ የሚገኙትን ለቅሶ ችላ አንበል” ተገቢ እና ወቅታዊ ምላሽ እንዲገኝ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።

2.     . . .እኛ አጥያትን ስለ ሠራን

እግዚአብሔር ለእኛ ምድርን የሰጠን ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ “እንድናለማት እና እንድንከባከባት ነው” (ዘፍ 2፡15)። ከመጠን በላይ መጠቀም እና በጣም አንሰተኛ በሚባል መልኩ መንከባከብ አጥያት ነው።

ወንድሜ ፓትሪያርክ በርቴሌመዎስ ብርታት በተሞላው መልኩ በተፈጥሮ ላይ እየፈጸምነው የምንገኘውን አጥያት ተንብየው ነበር።  አሁን በጋራ የመኖሪያ ቤታችን ላይ እየተከሰተ ካለው እውነታ በመነሳት እና በተለይም ደግሞ በምስጢረ ንስኋ አማካይነት “ውስጣዊ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይኖርባናል። በተፈጥሮ ላይ ያደረስነውን ጥፋት ተገንዝበን ይቅርታን መጠየቅ ይኖርብናል። እንዲሁም ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንድያስችልን እስቲ ራሳችንን እንመልከት ምክንያቱም ለስነ-ምዕዳር የምናደርገው አስተዋጾን በግልጽ በማወቅ  ለራሳችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለተፈጥሮ እና ለፈጣሪ ማሳየት የሚገባንን ኃላፊነት ማወቅ ያስፈልጋል።

3.     ሕሊናችንን መመርመር እና መጸጸት

ለእዚህ ችግር ቀዳሚ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት እንዲያስችለን በቅድሚያ “ማመስገን እንድንችል፣ ዓለማችን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኗን መረዳት እንድንችል እንዲሁም በጽሞና የእርሱን መልካምነትን በመላበስ በመልካም ሥራችን እራሳችንን መስዋዕት ማድረግ እንድንችል፣ በቅድሚያ እራስን መመርመር ያስፈልጋል። ጠንከር ያለ የሕሊና ምርመራ ካደረግን ቡኋላ በፈጣሪ፣ በፍጥረት፣ እንዲሁም በወንድም እና ሕህቶቻችን ላይ ባደረስነው ጥፋት ተጸጽተን ንስኋ መግባት ያስፈልጋል። “ንስኋን አስመልክቶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ  እንዳስቀመጠው እውነት ነጻ ያወጣችኋል” “እግዚአብሔር ከአጥያታችን በላይ ነው” ስለሆነም በተፈጥሮ ላይ ላደረስነው በደል ይቅር ይለናል”።

4.     አካሄዳችንን ማስተካከል

ሕሊናን መመርመር፣መጸጸት እንዲሁም አጥያታችን በምሕረት ለተሞላው እግዚአብሔር መናዘዝ ወደ አንድ መሻሻልን ማምጣት ወደ ምያስችለን አንድ ዓላማ ይመራናል። ይህም ዓላማ ተፈጥሮን ማክበር ወደ ምያስችለን ተጨባጭ ሐሳብ እና ተግባር ሊተረጎም ይገባል። ለምሳሌም “ፕላሲቲክ ነክ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም አቁመን በምትኩም ወረቀት ነክ ነገሮችን መጠቀም፣ የውሃ አጠቃቀማችንን በቁጠባ ማድረግ፣ ህይወት ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ እንክብካቤ ማሳየት፣ በካይነት የሌላቸውን የመጓጓዣ አገልግሎቶችን መጠቀም፣ ዛፎችን መትከል. . . ወዘተ የመሳሰሉትን ተግባራት መፈጸም ያስፈጋል።

5.     አዲስ የምሕረት ተግባር

“የምሕረትን ተግባር ከማከናወን በተሻለ ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር የምያዋህደን የተሻለ ነገር የለም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ኋጥያታችንን ይቅር የሚለን እና ፀጋውን የሚሰጠን እኛም ይህንን የምሕረት ተግባር በስሙ ማከናወን እንድንችል ነው”።

የክርስቲያን ሕይወት ባህል ሰባት አካላዊ እና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን መፈጸም እንዳለብን ያስተምረናል። “ብዙን ጊዜ የምሕረት ተግባራት ከግለሰቦች ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚፈጸሙ ለምሳሌ ለታመሙት ሆስፒታል፣ ለተራቡት ምግብ ቤት፣ ቤት ለሌላቸው መኖሪያ ቤት፣ ለተማሪዎች ትምህርት ቤት. . . ወዘተ ብቻ መስሎን ሊታይን ይችላል። ነገር ግን የምሕረት ተግባራትን በጥቅሉ ብንመለከት የምሕረት ተግባራት ዋናው ትኩረት የሰው ነፍስ እና ሰውን ያማከሉ ነገሮች ብቻ እንደ ሆኑ ያመለክታል።

ያለምንም ጥርጥር “የሰው ልጅ ሕይወት እና ይህንንም ያማከሉ ነገሮች ሁሉ” የጋራ መኖሪያችን የሆነውን ቤታችን እንድንከባከብ አደራ ይሉናል ማለት ነው። የጋራ መኖሪያ ቤታችን መንከባከብ የእዚህ የምሕረት ተግባራ አንደኛው አካል ነው።

6.     በመጨረሻም እንጸልይ

ምንም እንኳን ኋጥያተኞች ብንሆንም እና በብዙ መከራዎች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም ቅሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም ምክንያቱም ፈጣሪያችን መቼም ቢሆን ብቻችንን አይተወንም እና ነው። መቼም ቢሆን ፈጣሪያችን መሆኑን አያቆምም ምክንያቱም እርሱ ከምድራችን ጋር የተዋኋደ እና የእርሱ ፍቅር ሁል ጊዜም ቢሆን ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚደግፈን በመሆኑ ጭምር ነው።

እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባናል. . . “የድሆች አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ የተረሳችሁን እና የተጣለችሁን በአንተ ፊት ግን በጣም ውድ የሆነችውን ምድራችንን መታደግ እንድንችል እርዳን። የፍቅር አምላክ ሆይ በእዚህ ምድር ላይ ለሚገኙ ፍጥረቶች ሁሉ ያንተን ፍቅርን ማሳየት የምንችልበትን ቦታ እና ምንገዱን አሳየን። የምሕረት አምላክ ሆይ ያንተን ምሕረት የተጎናጸፍነውን ምሕረርት የጋራ የመኖሪያ ቤታችን በሆነችው ምድራችን ውስጥ መተግበር እንድንችል እርዳን። የእግዚአብሔር ሥም የተመሰገን ይሆን።

26 May 2021, 13:45