በአንዶራ እየተካሄደ ያለው ኢቢሮ-አሜሪካዊያን የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች በአንዶራ እየተካሄደ ያለው ኢቢሮ-አሜሪካዊያን የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለኢቢሮ-አሜሪካዊያን የመሪዎች ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት የኮቪድ ቀውስን እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.ኤ.አ. በሚያዝያ 21/2021 ዓ.ም እየተካሄደ ላለው የ 27 ኛው የኢቤሮ-አሜሪካዊያን የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት ኮቪድ -19 ወረርሽኝ በተንሰራፋበት በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ ያመጣቸውን ተግዳሮቶች ለመቋቋም በጋራ አብሮ መቆም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ረቡዕ ዕለት ሚያዝያ 13/2013 ዓ.ም ለአይቤሮ-አሜሪካ (የእስፓኒሽ፣ የፖርቹጋል እና የእግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ አገሮች ሕብረት) ሕብረት ዋና ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ለሆኑት ርብቃ ግሪንስሳን ማዩፊስ እንዲሁም በ 27 ኛው የኢቤሮ-አሜሪካዊያን የመሪዎች ጉባሄ ላይ ለተሳተፉ የመንግሥታት ተወካዮች ሁሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

ረቡዕ ቀን በአንዶራ እየተካሄደ ያለው የመሪዎች ጉባሄ የላቲን አሜሪካ አገራት መሪዎች “ፈጠራ ለዘላቂ ልማት - ዓላማ 2030” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘውን ጉባሄ እየተካፈሉ እንደ ሚገኙ ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመልእክታቸው እንዳሉት ስብሰባው በእነዚህ በተለይም አስቸጋሪ በሆኑት የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ጊዜያት ውስጥ ከአገራትን እና የዜጎቻቸውን መስዋእትነት የሚጠይቁ ቢሆንም መላው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኃላፊነት መንፈስ እራሳቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፣ በወንድማማችነት መንፈስ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት የነበሩትን ችግሮች ሳይቀር ለመፍታት የአገራት መሪዎች የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አክለው ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም በወረርሽኙ የተነሳ ተጎድተዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወረርሽኙ ሳቢያ ለሞቱት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን እና የታመሙትን በመጥቀስ የጤናው ድንገተኛ ሁኔታ ምንም ልዩነት እንደሌለው በመጥቀስ በእያንዳንዱ ባህል ፣ እምነት እና ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ክፍል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚነካ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው አክለው እንደ ገለጹት “በአቅራቢያችን በኮሮና ቫይረስ የሞተ ወይም በተላላፊ በሽታ የተጎዳ አንድ ሰው በሞት ማጣቱን ሁላችንም እንዴት እንደ ሚጎዳ እንዲሁም እንዴት እንደ ሚያሳምም አንውቃለን” ሲሉ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን መቅረብ ያልቻሉትን ቤተሰቦች ሥቃይ ይበልጥ አጉልተዋል። የሚወዷቸው ሰዎች ማጽናኛ እንዲሰጧቸው እና በወረርሽኙ ላይ በልጆችና በወጣቶች ላይ ያደረሰው አሳዛኝ ውጤት ችላ ሊባል የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሀኪሞች ፣ በነርሶች እና በሌሎች የሕክምና ባልደረቦች እንዲሁም ሕይወታቸው አደጋ ላይ ሆነው በሽተኞችን በማከም ላይ የሚገኙትን “ቤተሰቦች እና ወዳጆች” በማለት እርሳቸው የጠሯቸውን ሃኪሞች ፣ ነርሶች እና ሌሎች የሕክምና ባልደረቦች ሥራን አድንቀዋል።

የክትባቶች እኩል ተደራሽነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኮቪድ -19 ቫይረስ ለመከላከል ይችላ ዘንድ ውጤታማ የሆነ ክትባት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፈለግ የተደረጉ ጥረቶችን አድንቀዋል። በተመሳሳይ ጊዜ ክትባቱ ለሁሉም የሰው ልጆች ተደራሽ ይሆን ዘንድ እና የእዚህ ክትባት ፍታዊ ስርጭት እንደ "ሁሉን አቀፍ የጋራ ጥቅም" ተደርጎ መታየት አለበት የሚል ጥሪ አቅርበዋል - ምርምርን ፣ ምርታማነትን እና ክትባቶችን የሚያሰራጩ ተጨባጭ እርምጃዎችን የሚጠይቅ አስተሳሰብ ማዳበር እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ አዳዲስ የአብሮነት ዓይነቶችን የሚፈጥሩ ተነሳሽነቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ብቻ የተመሠረተ ሳይሆን የክትባት ፍትሃዊ ስርጭትን የሚያረጋግጡ ስልቶችን በማበረታታት ከእዚያ ባሻገር ደግሞ ተጋላጭና የተቸገሩትን ጨምሮ የሁሉንም ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገባ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን እክለው ገለጸዋል።

ዓለም አቀፍ የዕዳ ማሻሻያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጋጣሚውን በመጠቀም ዓለም አቀፍ የዕዳ ማሻሻያ ሥነ-ስረዓትን በመዘርጋት በእዚህ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት ይህንን የባሰ ላለማወሳሰብ ለእዳ ቅነሳ መርሃ ግብር ትኩረት መስጠት እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገለጸዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ድሃ አገራት እንዲያድጉ ለመርዳት እና የክትባት ፣ የጤና ፣ የትምህርት እና የስራ እድል ተደራሽ ማደረግ ይችሉ ዘንድ የእዳ ጫና መቀነስ የሚቻልበት ሁኔታ እንደገና ለድርድር እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው አክለው እንደ ገለጹት “ጤናማ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በመተግበር እና ወደ ድሆች የሚደርስ መልካም አስተዳደርን መዘርጋት አለበት” ሲሉ አጥብቀው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲስፋፋ እና “ሁሉም ሰው አሁን ካለበት ሁኔታ እንዲወጣ ለማድረግ የአገራት መሪዎች የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ” ጥሪ አቅርበዋል።

የተሻለ ድህረ ወረርሽኝ ማሕበረሰብ ስለመገንባት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እኛ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከዚህ ወረርሽኝ‘ በተሻለ ’መልኩ ልንወጣ እንደሚገባ መጠቆም እፈልጋለሁ” ያሉት ሲሆን “አሁን ያለው ቀውስ የአጭር ሽክርክሪቱን ሽግግር ለማገዝ በሰብዓዊ እና በኢኮኖሚ መካከል ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማጤን እድል የሚሰጥ ነው” ብለዋል።

ይህንን ለማሳካት ዓለም አቀፍ የጋራ ጥቅም ላይ ያነጣጠሩ አዳዲስ ፣ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማመንጨት የሚያስችል አቅም እና እንዲሁም በተቃራኒው የሰው ልጅ ሕይወት ጥበቃ በሚያገኝበት ቦታ የሚጠበቁ አድማሶችን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይም ድሆች በሰው ልጆች ላይ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ከፍተኛውን ዋጋ እንዳይከፍሉ ለማድረግ “ነገሮችን በተለይም ለመለወጥ ቅድሚያ ለመስጠት ድፍረት ያለው ጠንካራ የፖለቲካ ፍላጎት ከሌለ ይህ ተጋባራዊ ሊሆን እንደ ማይችል ልብ ሊባል ይገባል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልእክታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአይቤሮ-አሜሪካዊያን ስብሰባ ስኬት ያላቸውን ምኞት በመግለጽ ለተሳታፊዎች እንዲሁም በሚወክሏቸው የማሕበረሰብ ክፍል ላይ የእግዚአብሔርን በረከት ይወርድባቸው ዘንድ በጸሎት ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ ቅዱስነታቸው ከገለጹ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

21 April 2021, 09:34