ፈልግ

ሁላችንምም ወንድማማቾች ነን የተሰኘው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ በሆነበት ወቅት ሁላችንምም ወንድማማቾች ነን የተሰኘው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ በሆነበት ወቅት  

ሊቀ ጳጳስ ዩርኮቪች “ፍራቴሊ ቱቲ” የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት የሰውን ልጅ አንድነት ያጠናክራል አሉ!

ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ዩርኮቪች በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚል አርእስ ይፋ ባደርጉት ጳጳሳዊ መልእክ ላይ ተንተርሰው በሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም በጄኔቫ በበይነ መረብ አማካይነት ስለሚደርገው ስብሰባ በሰጡት አስተያየት በወንድማማችነት ፣በብዝሃነት እና በሰላም ዓለማችንን መገንባት እንደ ሚቻል የገለጹ ሲሆን በተለይም ደግሞ በእዚህ በአሁኑ ወቅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተንሰራፋበት ወቅት አብሮ የመጓዝ አስፈላጊነትን የገለጹ ሲሆን እንዲሁም በተባበሩት መንግስታትም ሆነ በቅድስት መንበር ታሪክ ውስጥ “ወንድማማችነት” የሚለው ቃል ጥንካሬ መሆኑን ገልፀዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቅድስት መንበርን በመወከል በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅ ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ-ጳጳስ ኢቫን ዩርኮቪች አክለው እንደ ገለጹት “በዚህ ቀውስ መጀመሪያ ላይ በአገራት መካከል የሚከበሩ መልካም አጋርነት ምሳሌዎችን የተመለከትነው ቢሆንም ፣ በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ጉዳቶች እርግጠኛ አለመሆን ፣ ልዩነቶች እና ክፍፍሎች እንዴት እየታዩ እንደሆነ አሁን ማየት እንችላለን” ብለዋል።

አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ

ሊቀ ጳጳስ ዮርኮቪች የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ ከሆነው ከሚካኤል ራቪየት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በዓለማችን ላይ እጅግ በጣም አቅመ ደካማ የሆኑ ድሆች እንደ ሚገኙ የገለጹ ሲሆን በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት በዚህ ወቅት ይህንን በዓለም ሕዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ አንዳንድ የዓለማችን አገራት ክትባቶችን ለራሳቸው ብቻ አከማችተው እንደ ሚገኙ፣ በአንጻሩ ደግሞ ድሃ የሆኑ አገሮች በክትባት እጥረት እየተሰቃዩ እንደ ሚገኙ መመልከቱ በራሱ ያንን ክፍተት ያሳያል ብለዋል።

“የሚያሳዝነው ግን ይህ ባህሪ ሀብታም ሀገሮች ብቻ የሚይዙበት እና ያደጉ ሀገሮች ባወጡት ጠንካራ ህግ የሚመራ መምሰሉ ነው” በማለት የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ ዮርኮቪች በተጨማሪም አንዳንድ ድሃ የሚባሉ አገራት ክትባቱን የበለጠ ያገኙ ዘንድ ይህ የክትባት ስርጭት አለመመጣጠን በመኖሩ ይህንን ጉዳይ ለመፍታት ተግተን መሥራት ይኖርብናል፣ ውይይቶችንም ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። እንዲሁም በአንዳንድ ሁኔታዎች የአንዱ አገር ፍላጎት ለሌላው ፍላጎት ያለው ሆኖ ሊታይ የሚችልበት የዕለት ተዕለት አጋርነት በጣም ጥሩ ምሳሌዎችን እናያለን ፣ በተግባርም በየቀኑ እየተመለከትን እንገኛለን፣ በእዚህ ረገድ የእዚህን ዓይነት ተግባራት የሚፈጽሙ አገራትን ማበረታታት ይኖርብናል ብለዋል።

ሶስት አስፈላጊ ቃላት

ሊቀ ጳጳስ ዩርኮቪች በመቀጠልም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቃል ተነሳስተን “እኛ በጄኔቫ የቅድስት መንበር ቋሚ ልዑካን አባላት ‘ወንድማማችነት ፣ ብዝሃነት እና ሰላም ’በሚል መሪ ቃል የሚመክር በፍተኛ ደረጃ በበይነ መረብ አማካይነት የሚደረግ ውይይት እያዘጋጀን ያለነው በትክክል በዚህ ምክንያት መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል” ብለዋል።

በማከልም ሊቀ ጳጳስ ዮርኮቪክ ስለ እነዚህ ሦስቱም ቃላት አስፈላጊነት አጥብቀው ተናግረዋል።

“ወንድማማችነት” የሚለው ቃል በግልፅ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጳጳሳዊ መልእክት የተቀመጠ መሆኑን ሊቀ ጳጳስ ዮርኮቪክ የገለጹ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን “ወንድማማችነት” የሚለውን ቃል የተጠቀሙበት ምክንያት “ብዝሃነት” የሚለውን ቃል ለማመልከት እንደ ሆነ ገልጸው ምክንያቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም ቀልጣፋ ያልሆነ፣ ነገር ግን እጅግ በጣም አስፈላጊ መስሎ የሚታየውን ዓለም አቀፍ ትብብር አስፈላጊነትን ለማጉላት ሁልጊዜ አስፈላጊ ነው ፣ እና ሦስተኛው ነገር ደግሞ “ሰላም” ነው ብለዋል።

ሰላም ሊቀ ጳጳስ ዩርኮቪች ስያስታውሱ በጄኔቫ በሚደርገው ውይይት ውስጥ ሰላም ከፍተኛ በሆነ ደረጃ ውይይት የሚደረግበት እና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ያሉ ሲሆን ምክንያቱም ከተማዋ “ትጥቅ ለማስፈታት የድርድር ቦታ” ሆና በማገልገል ላይ እንደ ምትገኝ አክለው ገልጸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚሰሩ ከ 40 በላይ ቋሚ ተወካዮች እና አምባሳደሮች በጄኔቫ እንደ ሞገኙ ልብ ሊባል ይገባዋል ብለዋል።

በበየነ መረብ የሚደርገው ስብሰባ

በሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም በበይነ መረብ አማካይነት የሚከናወነው ስብሰባ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አነሳሽነት የሚደረግ መሆኑን የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ዩርኮቪች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚል አርእስት ያፋ ካደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት ጭብጥ ሐሳብ በመውሰድ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በበይነ መረብ በሚያደርጉት ንግግር በይፋ እንደ ሚከፈት ተገልጿል።

ሊቀ-ጳጳስ ዩርኮቪክ ስለ ሁለንተናዊ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ በአንቀጽ 1 ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በመጥቀስ “ሁሉም የሰው ልጆች ነፃ እና እኩል የሆነ ክብር እና መብቶችን ተጎናጽፈው ነው ተወለዱት” በማለት የገለጹ ሲሆን ምክንያታዊ ባሕሪይ እና ሕሊና የተጎናፀፉ በመሆናቸው በወንድማማችነት መንፈስ አንዳቸው ለሌላው መንቀሳቀስ አለባቸው” ብለዋል።

ይህንን ሰነድ ያነሳሳው በትክክል “ወንድማማችነት” የሚለው ቃል መሆኑን ያስረዳሉ። በወንድማማችነት ፅንሰ-ሀሳብ የመነሳሳት ሀሳብ ያለን እኛ የመጀመሪያ ተቋም መሆናችን በጣም ዕድለኛ የሆንን ይመስለኛል ብለዋል።ዝግጅታችን ተገቢ እንደ ሆነ የምንቆጥረው ለዚህ ነው፣ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መነሳሳት መካከል ጥሩ ገጠመኝ ሊፈጥር ይችላል ብለዋል።

ለውይይት መተባበር

የዝግጅቱ ሁለተኛው ክፍል የሚያተኩረው በሃይማኖቶች መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ነው። ሊቀ ጳጳስ ዩርኮቪች በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ውይይት የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን በጣም አስፈላጊ አካል መሆኑን አክለው ተናግረዋል። “በእርግጥ ሁል ጊዜ አስፈላጊ ነበር” ነገር ግን ቀደም ሲል ለመልካም ከመጠቀም ይልቅ ብዙ ጊዜ “በደል” ለመፈጸም ሐይማኖቶችን ሽፋን አድርጎ የመጠቀም አዝማሚያ ይታይ እንደ ነበረም አስታውሰዋል።

በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ባሉ የታወቁ ሰዎች እና ትውፊቶቻቸው መካከል ትብብር መፍጠር፣ በሃይማኖቶች መካከል ትብብር እና ውይይት እንዲኖር ማደረግ አስፈላጊ እንደ ሆነ ሊቀ ጳጳሱ ዮርኮቪች አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። የቅድስት መንበር ተልእኮ በትክክል ይህ ይመስለኛል ሲሉ የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ ዩርኮቪች-ይህንን በሃይማኖቶች መካከል የሚደረገውን ውይይት ለማስቀጠል የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን መልእክት በዓለም ሁሉ ላይ ለማዳረስ ታቅዶ በበይነ መረብ አማካይነት የሚደረግ ስብሰባ እንደ ሆነ ከገለጹ በኋላ ተሰናብተዋል።

15 April 2021, 10:01