ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢራቅ የምትገኘው ቤተክርስቲያን አሁንም ቢሆን በሕይወት አለች አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከየካቲት 26-29/2013 ዓ.ም ደረስ 33ኛውን ሐዋርያዊ ግጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢራቅ ማቅናታቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው የነበራቸውን የሶስተኛውን ቀን ጉብኝት በየካቲት 28/2013 ዓ.ም የጀምሩት ወደ ኤርቢል በመጓዝ ሲሆን በእዚያው ቅዱስነታቸው መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ተገልጿል፣ ቅዱስነታቸው በኤርቢል ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት በኢራቅ የምትገኘው ቤተክርስቲያን አሁንም ቢሆን በሕይወት አለች ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ኢራቅ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ መጠናቀቂያ ላይ በኤርቢል ፍራንሶ ሀሪሪ ስታዲየም ውስጥ እሁድ የካቲት 28/2013 ዓ.ም መስዋዕተ ቅዳሴ አድርገዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢራቅ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ ማጠናቀቂያ መስዋዕተ ቅዳሴ በማድረግ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት “ዛሬ በኢራቅ ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን በሕይወት እንዳለች ፣ ክርስቶስም በእዚህ ቅዱስ እና ታማኝ ህዝቡ ውስጥ ህያው እንደሆነ እና በስራ ላይ እንዳለ አይቻለሁ” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉት ስብከት በቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ክርስቶስ” በሚለው ምንባብ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር። ኢየሱስ “ኃይልንና ጥበብን ከምንም በላይ ይቅርታ በማድረግ ምህረትን በማሳየት ገልጧል” ብለዋል።

ብዙውን ጊዜ “እኛ ኃይለኞች ወይም ጥበበኞች መሆናችንን ለሌሎች ማሳየት አለብን ብለን በማሰብ ወጥመድ ውስጥ እንወድቃለን” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን “በጦርነት እና በዓመፅ በተፈጠሩ ቁስሎች” እየተሰቃየን “በሰው ኃይል ፣ በሰው ጥበብ” ምላሽ ለመስጠት እንፈተናለን ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ “ነገር ግን እውነቱ ሁላችንም ኢየሱስ በመስቀል ላይ የገለጠውን የእግዚአብሔርን ኃይል እና ጥበብ መፈለግ ይኖርብናል” ብለዋል።

የልባችንን ቤተ መቅደስ ማጽዳት አለበት

ጌታ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ እንዴት እንዳወጣቸው ወደ ሚናገረው ወደ እለት ቅዱስ ወንጌል ሐሳባቸውን በማደረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ገለጹት “እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ከድንጋይ የተገነባውን ቤተመቅደስ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ የልባችንን ቤተመቅደስ” እንዲያጸዳ ኢየሱስን እንደላከው ተናግረዋል። ልባችን ከሚያረክሷቸው ሐሰተኞች ከሆኑ ከግብዝነት “ከኃይል፣ ስልጣን እና ገንዘብ ፈታኝ ፈተናዎች” ማጽዳት አለብን ብለዋል።

እኛ ግን በራሳችን ጥረት ልባችንን ማፅዳት አንችልም ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን ይልቁንም እሱ “እርሱ ብቻ ነው ፣ ከክፉ ሥራዎች ሊያነፃን የሚችለው፣ ክፋቶቻችንን የማሸነፍ ፣ በሽታዎቻችንን የመፈወስ እና የልባችንን ቤተመቅደስ የመገንባት ኃይል ያለው” እርሱ ብቻ ነው ብለዋል።

የክርስቶስ መንግሥት ምልክቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል “ኢየሱስ ከኃጢአታችን ሊያነፃን ብቻ ሳይሆን በራሱ ኃይልና ጥበብም ሊያድሰን ይፈልጋል” ያሉ ሲሆን ኢየሱስ “ከቤተሰብ ፣ ከእምነት እና ከማህበረሰብ ጠባብ እና ከፋፋይ አስተሳሰቦች” ነፃ ያወጣናል፣ የተቸገሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን የሚንከባከብ ሁሉን አቀፍ ቤተክርስቲያን እና ህብረተሰብ እንድነገነባ የሚረዳን እርሱ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ ​​ኢየሱስ “በቀልን በበቀል እንዳንመልስ የሚያነሳሳውን ፈተና እንድንቋቋም ያበረታናል” ያሉ ሲሆን እንዲሁም “ሰዎች እምነታቸውን ቀይረው የእኛን እምነት እንዲይዙ ማስገደድ ሳይሆን እንደ የወንጌል ደቀ መዛሙርት ፣ ወንዶችና ሴቶች የወንጌልን ሕይወት የመለወጥ ኃይል ለመመስከር” እርሱ ይልከናል ብለዋል።ከሦስት ቀናት በኋላ ቤተመቅደሱን እንደ ሚገነባው ኢየሱስ ቃል መግባቱን የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ የሚናገረው ስለራሱ አካላዊ ትንሣኤ ብቻ አይደለም “ስለ ቤተክርስቲያንም ጭምር ነው የተናገረው” ብለዋል። ጌታ “በትንሣኤ ኃይል እኛን እና ማህበረሰቦቻችንን በፍትህ መጓደል ፣ በመከፋፈል እና በጥላቻ ከወደመው ፍርስራሽ ውስጥ አውጥቶን ከፍ እንደ ሚያደርገን ተስፍ ሰጥቶናል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ ኢየሱስ “ማንኛውንም ጉዳት ለመቀባት ፣ ሁሉንም የሚያሰቃዩ ትውስታዎችን ለመፈወስ እና ለወደፊቱ ምድር በሰላምና በወንድማማችነትን መንፈስ እንድትገነባ ለማነሳሳት ይፈልጋል” ብለዋል።

የኢራቃውያን ክርስቲያኖችን እምነት ማረጋገጥ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ ሐሳባቸውብ ወደ ኢራቃውያን የክርስቲያን ማኅበረሰብ በማዞር እንደ ገለጹት “በኢራቅ ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቸርነት የክርስቶስን ምሕረት እና ይቅር ባይነት በተለይም በታላላቅ ሰዎች ላይ በማሰራጨት ይህንን አስደናቂ የመስቀልን ጥበብ ለማወጅ ከወዲሁ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች ነው፣ ለእዚህም የሚሆን ከፍተኛ ፍላጎት አላት” ብለዋል።

ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “በመካከላችሁ እንደ መንፈሳዊ ተጓዥ ሆነው እንዲመጡ፣ እንዲያመሰግናችው እና እምነትታችሁን እና ምስክርነታችሁን እንዳረጋግጥ ከሚያደርጉኝ ምክንያቶች አንዱ ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የማርያምን ሐውልት ባረኩ

የኮርኖና ቫይረስ ለመከላከል ይቻል ዘንድ በወጣው የጤና አጠባበቅ መስፈርት መሰረት እና ለእርሳቸው ከሚደረገው የደህንነት ጥበቃ እርምጃዎች ምክንያት ወደ 10 ሺህ ያህል ሰዎች በኤርቢል ፍራንሶ ሀሪሪ ስታዲየም እሁዱ የካቲት 28/2013 ዓ.ም እርሳቸው ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ በአካል ተገኝተው የተከታተሉ ሲሆን የተቀረው የማሕበርሰብ ክፍል በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች በሬዲዮ ፣ ቴሌቪዥንና ኢንተርኔት ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ግንኙነቶች አማካኝነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ተከትለዋል።

በሰዋዕተ ቅዳሴው ስነስረዓት ማብቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች የወደመውን የድንግል ማርያም ሐውልት ታድሶ በአዲስ መልክ በቀረበበት ወቅት  የባረኩ ሲሆን የሀውልቱ ጭንቅላት እና እጆች ተቆርጠው የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ጭንቅላቱ ተመልሶ እንደገና እንዲገጥም ተደርጎ ነበር።

በኤርቢል የማሪያም ሬዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር የሆኑት አባ ሳሚር ሼር እንዳስረዱት ሀውልቱ መጀመሪያ የመጣው ከክርስቲያኖች መንደር ካራምለስ ነው። ከተባረከ በኋላ ሀውልቱ ወደ ነነዌ እንደ ሚመለስ የገለጹ ሲሆን የአከባቢው ክርስቲያኖች ተስፋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅርቡ በካራሜልስ ልጆ አቅፋ ውስጥ ተመልሳ እንደ ምትገባ ነው ብለዋል።

07 March 2021, 12:39