በሰሜን አሜሪካ የሚካሄዱ የሰላም፣ የእኩልነት እና የጸረ-ዘረኝነት ትግሎች በሰሜን አሜሪካ የሚካሄዱ የሰላም፣ የእኩልነት እና የጸረ-ዘረኝነት ትግሎች 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ “ዘረኝነት ከመወገድ ይልቅ መደበቅን የሚመርጥ ወረርሽን ነው” ማለታቸው ተገለጸ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ የዘር መድልዎ የሚወገድበት ዓለም አቀፍ ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የቲዊተር ማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክታቸው፣ “የዘረኝነት መገለጫዎች በሰው ልብ ውስጥ ውርደትን በማሳደግ ላይ ናቸው” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በመልዕክታቸው “ዘረኝነት ሊወገድ ሲገባው በቀላሉ በመስፋፋት በድብቅ እያጠቃን ነው፤ መገለጫዎቹም ከጊዜ ወደ ጊዜ አድገው በሰው ልብ ውስጥ ውርደትን በመጨመር የህብረተሰብን የዕድገት ዋስትና በማሳጣት ላይ ይገኛል” በማለት የዘር መድልዎ የሚወገድበት ዓለም አቀፍ ቀንን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕት ተናግረዋል።

መጋቢት 12

ዘረኝነት የሚወገድበት ዓለም አቀፍ ቀን መጋቢት 12 እንዲሆን የተወሰነው እ. አ. አ መጋቢት 21/1960 ዓ. ም. ሲሆን ይህም በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ በመክፈት ሰባ ዘጠኝ ሰዎችን ገድለው አንድ መቶ ሰማንያ ሰዎችን ያቆሰሉበት ዕለት ለማስታወስ ተብሎ ነው። ዕለቱ በሰው ሕይወት ላይ አሰቃቂ እልቂት የተፈጸመበት በመሆኑ የሻርፕቪል ድራማ በመባል ይታወቃል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መጋቢት 12ን የዘር መድልዎ የሚወገድበት ዓለም አቀፍ ቀን እንዲሆን የወሰነው እ. አ. አ በ1966 ዓ. ም. ባካሄደው ጠቅላላ ስብሰባ ሲሆን፣ በውቅቱ ባስተላለፈው ውሳኔ ማንኛውንም ዓይነት የዘር መድልዎን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ሊደረግ ይግባል በማለት ማሳሰቡ ይታወሳል።

በአሜሪካ ግዛቶች የተካሄዱ ሰልፎች

ዕለቱን ለማስታወስ ብለው በሰሜን አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ግዞቶች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አደባባዮች እና ጎዳናዎች መውጣታቸው ተነርግሯል። በተለይም በቅርቡ በ21 ዓመት ዕድሜ ነጭ ዜጋ የተገደሉ ስምንት ሰዎች፣ ከእነዚህም መካከል የእስያ ዝርያ ያላቸው ስድስት ሴቶችን በማስታወስ በአትላንታ እና ጆርጂያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መካሄዳቸው ታውቋል። ሰልፈኞቹ ይዘው ከወጡት መፈከሮች መካከል “የእስያ ጥላቻ ይቁም” ፣ “ዘረኝነት ተላላፊ ወረርሽኝ ነው” የሚሉ ታይተዋል። አዲስ የተመረጡት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በአትላንታ በሚገኝ፣ ኤሚሪ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ “ከጥላቻ እና ከዘረኝነት ጋር የሚደረጉ ትግሎችን ጨምሮ አንዳንድ መሠረታዊ እሴቶች እና እምነቶች የአሜሪካን ሕዝብ የበለጠ ሊያቀራርቡ ይገባ ነበር” ብለው “ዘረኝነት ሕዝባችንን ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሲጎዳው የኖረው መርዝ ነው” ብለዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት በማከልም በሰዎች ውስጥ የሚፈጠሩ የጥላቻ እና የዓመፅ ስሜቶች ብዙውን ጊዜ ግልጽ ባልሆነ መንገድ በሰዎች ልብ ውስጥ ተደብቀው ይኖራሉ ብለዋል።

22 March 2021, 09:19