ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዓለም የሚለወጠው በኃይል እና በጉልበት ሳይሆን በቅድስና ወይም ብፁዕና ነው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከየካቲት 26-29/2013 ዓ.ም 33ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማደረግ ወደ ኢራቅ በየካቲት 26/2013 ዓ.ም ጉዞ መጀመራቸው ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በኢራቅ እያደረጉ በሚገኙት ሁለተኛ ቀን ጉብኝት በመቀጠል ቅዳሜ ጥዋት በሮም የሰዓት አቆጣጠር 07:45 ናጃፍ በመባል ወደ ምትታወቀው ከተማ መጓዛቸው የተገለጸ ሲሆን በሮም የሰዓት አቆጣጠር 09:00 ላይ ካታላቁ  አያቶላህ ሰይድ አሊ አል-ሁሰኒ አል-ሲስታኒ ጋር በናጃፍ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 11፡10 ከተለያዩ የአይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሰችው እና የአባታችን የአብርሃም አገር በመባል ወደ ምትታወቀው በከለዳውያን ምድር ወደ ምትገኘው ዑር (ኦሪት ዘፍጥረት 11፡31) በመሄድ በእዚያው ቅዱስነታቸው ንግግር ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ለሦስቱ ሐይማኖቶች ተወካዮች ማለትም ለእስልምና፣ ለአይሁድ እና ለክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት መልዕክት እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ከከዋክብት በታች በኢራቅ ውስጥ የሰላም ጎዳናን እንዲከተሉ ማሳሰባቸው ይታወሳል። በእዚያም ቅዱስነታቸው ንግግር ካደረጉ በኋላ “የአብርሃም ልጆች ጸሎት” ተብሎ የሚታወቀው ጸሎት ደግመዋል።

ለቅዱስነታቸው ለቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም የወጣው የጉዞ መርሃ ግብር እንደ ሚያስረዳው በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 13፡20 ባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተመልሰዋል።

አመሻሹ ላይ በሮም የሰዓት አቆጣጠር 16:00 ቅዱስ አባታችን በባግዳድ ውስጥ በ “ቅዱስ ዮሴፍ” የከለዳውያን ካቴድራል ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ ሲሆን በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ዓለም ሊቀየር የሚችለው በቅድስና ወይም በብጽዕና ነው እንጂ በኃይል አይደለም ማለታቸው ተገልጿል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጥበብ ፣ ስለ ምስክርነት እና ስለ ተስፋዎች ይናገራል።

በእዚህች ምድር ውስጥ ጥበብ ከጥንት ጀምሮ እየጎለበተ የመጣ ነገር ነው። በእርግጥም የጥበብ ፍለጋ ሁል ጊዜ ወንዶችንና ሴቶችን ይስባል። ብዙውን ጊዜ ብዙ አቅም ያላቸው የበለጠ ዕውቀትን ማግኘት እና የበለጠ ዕድሎችን ሊያገኙ ይችላሉ ፣ አናሳዎቹ ግን ወደ ጎን ይገለላሉ። እንዲህ ያለው እኩል ያለመሆን ልኬት በእኛ ዘመን የጨመረ የመጣ እና ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው። የጥበብ መጽሐፍ ይህንን አመለካከት በመቀልበስ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን ያመለክታል። እሱ እንደሚነግረን “ዝቅተኛው በምህረቱ ይቅር ሊባል ይችላል ፣ ኃያላን ግን በከፍተኛ ሁኔታ ይፈተናሉ” (መጽሐፈ ጥበብ 6: 6) ይለናል። በዓለም እይታ አናሳዎቹ ይገለላሉ፣ ብዙ ነገር ያላቸው ደግሞ ልዩ መብት አላቸው። ለእግዚአብሔር እንዲህ አይደለም - የበለጠ ኃይለኞች ከባድ ምርመራ ይደረግባቸዋል ፣ አናሳዎቹ ግን በእግዚአብሔር የተመረጡ ናቸው።

በአካል ጥበበኛ የሆነው ኢየሱስ በወንጌሉ ውስጥ ይህን ተገላቢጦሽ በሆነ ሁኔታ ያጠናቅቃል ፣ እናም እሱ በመጀመሪያ በተራራ ላይ ባደርገው ስብከቱ ስለብጽዕና ይናገራል። የተገላቢጦሹ ሁኔታ ጠቅላላ ሁኔታዎችን ያሳያል፣ የሚያዝኑ ፣ ስደት የሚደርስባቸው ሁሉም ብፁዕን ይባላሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይቻላል? ለዓለም የተባረኩ የሚባሉ ሰዎች ሀብታሞች ፣ ኃያላን እና ዝነኛ የሆኑ ሰዎች ናቸው! ሀብት እና ሀብት የማግኛ መንገዶችን የሚያውቁ ሰዎች ናቸው የተባረኩ የሚባሉት በዓለም እይታ! ለእግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም፣ ከእንግዲህ ወዲህ ለእግዚአብሔር ሀብታም የሚባሉ ሰዎች በመንፈስ ድሆች የሆኑ ሰዎች እንጂ ታላቅ የሆኑ ሰዎች ግን አይደሉም። ፈቃዳቸውን በሌሎች ላይ መጫን የሚችሉ አይደሉም ፣ ነገር ግን ለሁሉም ገር የሆኑ ሰዎች ናቸው።ከእንግዲህ ወዲህ ለእግዚአብሔር አብታም የሚባሉ ሰዎች በሕዝቡ ዘንድ እውቅና የተሰጣቸው ሰዎች ሳይሆኑ ነገር ግን ለወንድሞቻቸው እና ለእህቶቻቸው ምሕረትን የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው። በዚህ ጊዜ ፣ ​​እኛ እንጠይቅ ይሆናል-ኢየሱስ እንደሚጠይቀኝ ብኖር ምን አተርፋለሁ? ሌሎች በእኔ ላይ እንዲነግሱ የማድረግ አደጋ አይፈጥርም ወይ? የኢየሱስ ግብዣ ጠቃሚ ነው ወይስ የመጥፊያ ምክንያት ነው? ይህ ግብዣ ዋጋ ቢስ አይደለም ነገር ግን ጥበበኛ ነው።

የኢየሱስ ግብዣ ጥበበኛ ነው፣ ምክንያቱም የብፁዕን ልብ የሆነው ፍቅር በዓለም ዓይኖች ውስጥ ደካማ ቢመስልም በእውነቱ ሁልጊዜ ያሸንፋል። በመስቀሉ ላይ ፣ ከኃጢአት የበለጠ ጠንካራ ሆኖ ተገኝቷል ፣ በመቃብር ውስጥ ፣ ሞትን ድል ነስቷል። ይኸው ፍቅር ሰማዕታትን በፈተናዎቻቸው ውስጥ ድል አድራጊ ያደርጋቸዋል - እና ካለፈው ጊዜ በበለጠ እንኳን ባለፈው ምዕተ ዓመት ስንት ሰማዕታት ተገኝተዋል! ስለእዚህ በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት ጭፍን ጥላቻ እና ውርደት ፣ በደል እና ስደት ለደረሰባቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ፍቅር የጥንካሬያቸው ምንጭ ነበር። ሆኖም የዓለም ኃይል ፣ ክብር እና ከንቱነት ሲያልፍ ፍቅር ጽንቶ ይኖራል። ሐዋርያው ​​ጳውሎስ እንደነገረን “ፍቅር ከቶ አይወድቅም” (1 ቆሮ 13፡8) ይለናል። በብፁዕና የተቀረፀ ሕይወት መኖር ማለት የሚያልፉ ነገሮችን ዘላለማዊ ማድረግ ፣ መንግሥተ ሰማይን ወደ ምድር ማምጣት ማለት ነው።

ነገር ግን ወደ ብጽዕና የሚወስዱንን መንገድ እንዴት መለማመድ እንችላለን? ከአቅማችን በላይ የሆኑ ልዩ ልዩ ነገሮችን እንድናደርግ አይጠይቁንም። በየቀኑ ምስክርነት እንድንሰጥ ብቻ ነው የሚጠይቁን። ብፁዕን በየዋህነት የሚኖሩ ፣ የትም ባሉበት ምህረትን የሚያሳዩ ፣ በሚኖሩበት ሁሉ ከልባቸው ንፁህ የሆኑ ናቸው። ለመባረክ ፣ አልፎ አልፎ ጀግኖች መሆን አያስፈልገንም ፣ ነገር ግን ከቀን ወደ ቀን ምስክሮች መሆንን ይጠይቃል። ምስክርነት መስጠት ማለት የኢየሱስን ጥበብ መምሰል ማለት ነው። ዓለም የሚለወጠው በዚህ ነው-በኃይል እና በጉልበት  ሳይሆን በቅድስና ወይም ብፁዕና ነው። ኢየሱስ ያደረገው እንዲሁ ሲሆን ከመጀመሪያ አንስቶ የተናገረውን ነገር እስከ መጨረሻው ድረስ ኖሮ መስክሯል። ሁሉም ነገር የተመካው የኢየሱስን ፍቅር በመመስከር ላይ ነው ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በዛሬው ሁለተኛ ንባብ ውስጥ በሚያስደንቅ ሁኔታ የገለጸውን ያን ተመሳሳይ ድርጊት ነው። እስቲ እሱ እንዴት እንደሚያቀርብ እንመልከት።

በመጀመሪያ ሐዋርያው ጳውሎስ “ፍቅር ታጋሽ ነው” ብሏል (ቁ. 4)። ይህንን ቅፅል አልጠበቅንም ነበር። ፍቅር ከጥሩነት ፣ ከለጋስነትና ከመልካም ሥራዎች ጋር ተመሳሳይ ይመስላል ፣ ሆኖም ሐዋርያው ጳውሎስ ፍቅር ከሁሉም በላይ ታጋሽ ነው ብሏል። መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ እና በዋነኝነት ስለ እግዚአብሔር ትዕግሥት ይናገራል። በታሪክ ዘመናት ውስጥ ሁሉ ወንዶችና ሴቶች በአንድ ዓይነት ኃጢአቶች ውስጥ በመውደቃቸው ከእግዚአብሔር ጋር ለገቡት ቃል ኪዳን የማይታመኑ መሆናቸውን አሳይተዋል። ሆኖም ጌታ በእኛ ሥራ ከመሰላቸት እና እኛን ጥሎን ከመሄድ ይልቅ ሁል ጊዜ በታማኝነት ጸንቶ ይቅር የሚለን አምላክ ሲሆን እንደ ገና በአዲስ መልክ እንድንጀምር እድሉን ይሰጠናል። በእያንዳንዱ ጊዜ እንደገና ለመጀመር ይህ ትዕግስት የመጀመሪያው የፍቅር ምልክት ነው ፣ ምክንያቱም ፍቅር አይበሳጭም ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እንደገና ይጀምራል። ፍቅር አይደክምም ወይም ተስፋ አይቆርጥም ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ወደ ፊት እንድንሄድ ይጋብዘናል። ተስፋ አይቆርጥም ፣ ነገር ግን አዲስ ፈጠራን በውስጣችን በማኖር አዲስ ሰዎች እንድንሆን እድሉን ይሰጠናል። ፍቅር ከክፉ መንፈስ ጋር ተጋፍጧል ፣ ተስፋ አይቆርጥም ወይም እጅ አይሰጥም። የሚያፈቅሩ ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ስህተት ውስጥ ቆልፈው አይኖሩም፣ ነገር ግን በመስቀል አሸናፊነት ጥበብን በማሰብ ለክፉ ነገሮች በጥሩ ምላሽ ይሰጣሉ። የእግዚአብሔር ምስክሮች እንደዚህ ናቸው- ገብጋባ ወይም ገዳይ አይደሉም ፣ በሚከሰቱ ክስተቶች ፣ ስሜቶች ወይም ፈጣን ክስተቶች ውስጥ ምህረትን ያሳያሉ። ይልቁንም እነሱ ሁል ጊዜ ተስፋ ያደርጋሉ ፣ ምክንያቱም “ፍቅር ሁል ጊዜ ይታገሣል፤ ሁል ጊዜ ያምናል፤ ሁል ጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁል ጊዜ ጸንቶ ይቆማል” (1ቆሮ 13፡ 7) ባለው ፍቅር ውስጥ የተመሠረተ ነው።

እራሳችንን መጠየቅ እንችላለን -ትክክል ላልሆኑ ሁኔታዎች ምን ዓይነት ምላሽ እንሰጣለን? በችግር ጊዜ ውስጥ ሁል ጊዜ ሁለት ፈተናዎች አሉ። የመጀመሪያው መሸሽ ነው፣ ጀርባችንን ማዞር ፣ ከሁሉም ለመራቅ እየሞከርን ነው። ሁለተኛው በንዴት ምላሽ መስጠት ነው ፣ ኃይል ማሳየት። በጌቴሴማኒ የደቀመዛሙርት ሁኔታ እንደዚህ ነበር፣ ብዙዎቹ ግራ ተጋብተው ነበር፣ ብዙዎች ደግሞ ሸሹ ጴጥሮስም ሰይፉን አነሳ። ሆኖም መሸሽም ሆነ ጎራዴ ምንም ዓዲስ ነገር አልፈጠረም ነበር። ኢየሱስ ግን ታሪክን ቀይሯል። እንዴት? በትህትና፣ በፍቅር ኃይል እና በትዕግሥት ምስክርነት በመስጠት። እኛ እንድናደርግ የተጠራነው ይህንን ነው፣ እግዚአብሔርም የገባውን ቃል ይፈጽማል።

ቃል ኪዳን። በቅድስና ወይም በብጽዕና ውስጥ የተካተተው የኢየሱስ ጥበብ ምስክሮች እንድንሆን ጥሪ የሚያቀርብልን ሲሆን ይህም በመለኮታዊ ተስፋዎች ውስጥ ቃል የተገባለንን ሽልማት ያሸልመናል። እያንዳንዱ ጥበብ ወዲያውኑ በተስፋ ይታጀባልና፣ ተግባራዊ የሚያደርጋቸው ሁሉ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ ፣ ይጽናናሉ ፣ ይጠግባሉ ፣ እግዚአብሔርን ያዩታል (ማቴዎስ 5: 3-12)። የእግዚአብሔር ተስፋዎች ተወዳዳሪ የሌለውን ደስታ ያረጋግጣሉ እናም በጭራሽ አያሳዝኑንም ወይም አያሳፍሩንም። ነገር ግን እንዴት ይፈፀማሉ ብለን ልንጠይቅ እንችል ይሆናል? በእኛ ድክመቶች ውስጥ ይፈጸማሉ። እስከ መጨረሻው በውስጣቸው በድህነት መንገድ የሚጓዙትን እግዚአብሔር ይባረካቸዋል።

መንገዱ ይህ ነው፣ ሌላ መንገድ የለም። ወደ አባታችን አብርሃም እንመልከት። እግዚአብሔር ታላቅ ዘር እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር ፣ እሱና ሣራ ግን በወቅቱ በጣም በእድሜ የገፉ ሰዎች እና ምንም ልጅ ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ። ሆኖም እግዚአብሔር በትእግስት እና በታማኝነታቸው በዕድሜያቸው ድንቅ ተአምራት አድርጎ ወንድ ልጅ ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም ሙሴን እንመልከት -እግዚአብሔር ሰዎችን ከባርነት ነፃ እንደሚያወጣ ቃል ገብቷል ፣ እናም ይህን ለማድረግ ሙሴን ከፈርዖን ጋር እንዲነጋገር ይጠይቀዋል። ምንም እንኳን ሙሴ ይህንን በቃል መናገር ብዙ ፋይዳ የለውም ብሎ አምኖ የነበረ ሲሆን እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን የሚፈጽመው በቃሉ ነው። በሕጉ መሠረት ልጅ መውለድ ያልተፈቀደላት፣ ነገር ግን እናት እንድትሆን  የተጠራችውን እመቤታችንን እንመልከት። እናም ወደ ጴጥሮስ እንመልከት፣ ጌታን ይክዳል፣ እርሱ ግን ወንድሞቹን ለማፅናት ኢየሱስ የጠራው እሱ ነበር። ውድ ወንድሞች እና እህቶች ፣ አንዳንድ ጊዜ አቅመቢስ እና የማንረባ እንደ ሆንን ሆኖ ይሰማናል። እኛ በጭራሽ ለዚህ ሐሳብ ወይም አመለካከት ተገዢ መሆን የለብንም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በድክመቶቻችን በኩል በትክክል ተዓምራቶችን መሥራት ይፈልጋልና።

እግዚአብሔር ያንን ማድረግ ይወዳል ፣ እናም ዛሬ ማታ ፣ ስምንት ጊዜ ፣ ​​እኛ ከእርሱ ጋር በእውነት መንፈስ የተቆራኘን እንደ ሆንን እንድንገነዘብ ለማድረግ “ብጽዕን” (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አምስት ላይ ያለውን የተራራ ላይ ስብከት ያመለክታል) የሚለውን ቃል ነግሮናል። በእርግጥ እኛ ፈተናዎች ያጋጥሙናል፣ እናም ብዙ ጊዜ እንወድቃለን ፣ ነገር ግን ያንን መዘንጋት የለብንም ፣ ከኢየሱስ ጋር እኛ ብጽዕን ነን። ዓለም ከእኛ የምትወስደው አንድ ነገር ቢኖር ጌታ የገባውን ቃል ከሚፈጽምበት ርህራሄ እና ትዕግስት ፍቅር ጋር ሲነፃፀር ምንም አይደለም። ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ምናልባት እጆቻችንን ስንመለከት ባዶ የሆኑ ይመስሉናል፣  ምናልባት የምንበሳጭ እና የህይወት እርካታ የማይሰማን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። እንደዚያ ሲሆን አትፍሩ - በተራራው ላይ የተሰበከው ስብከት ለእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ነውና። ለእናንተ ለተጎሳቆላችሁ፣ ፍትህን ለምትራቡ እና ለተጠማችሁ ፣ ለተሰደዳችሁ ሁሉ ነውና። ጌታ ስማችሁ በእርሱ ልብ ውስጥ እንደተጻፈ፣ በሰማይ መዝገብ ላይ እንደተጻፈ ቃል ገብቶላችኋል!

ዛሬ እግዚአብሔርን ከአንተ ጋር እና ስለእናንተ አመሰግነዋለሁ፣ ምክንያቱም እዚህ የጥንት ዘመን ጥበብ በተነሳበት ፣ ብዙ ምስክሮች በእኛ ዘመን ውስጥ እንኳን ሳይቀር በተነሱበት፣ ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ላይ ችላ የተባሉ ነበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ውድ የሆኑ ሰማዕታት የመነጩበት አገር ነው። ብፁዕነታቸውን በመኖር እግዚአብሔርን የሰላም ተስፋዎቹን እንዲፈጽም እየረዱ ያሉት ምስክሮች የፈለቁበት አገር ነው።

06 March 2021, 10:55