ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ማርያም በወረርሽኙ ምክንያት ብቻቸውን ሆነው ለሞቱ ሰዎች ቅርብ ናት አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በመጋቢት 15/2013 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማሪያም በወረርሽኙ ምክንያት ብቻቸውን ለሞቱ ሰዎች ቅርብ ናት ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ የምናደርገው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከማሪያም ጋር ህብረት ለመፍጠር ስለሚደረገው ፀሎት ይሆናል። መልአኩ ማሪያምን ያበሰረበት ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት የዋዜማ እለት ላይ ይህ ነገር በትክክል ይከሰታል። የክርስቲያን ጸሎት ዋና መንገድ የኢየሱስ ሰብዓዊነት መሆኑን እናውቃለን። በእውነቱ  ቃል ሥጋ ባይለብስ ኖሮ ከአብ ጋር ያለውን የእርሱን ዝምድና በመንፈሱ በመስጠት ለእኛ የክርስቲያን ጸሎት ዓይነተኛ መተማመኛ ትርጉም አይኖረውም ነበር።

ክርስቶስ አማላጅ ነው፣ ወደ አብ ለመሻገር በምናደርገው ጉዞ ላይ የምንሻግረን ድልድይ ነው (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 2674 ን ይመልከቱ)። ወደ እግዚአብሔር የምናቀርባቸው እያንዳንዱ ጸሎቶች በክርስቶስ በኩል ነው የሚያልፉት፣ በክርስቶስ እና በክርስቶስ ውስጥ ነው የሚያልፉት፣ እናም ለእርሱ አማላጅነት ምስጋና ይግባውና ጸሎቶቻችን የሚሳኩት በእርሱ ምልጃው ነው። መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ምልጃ በእያንዳንዱ ጊዜ እና ቦታ ሁሉ ያራዝማል ፤ እኛ የምንድንበት ሌላ ለየት ያለ ስም የለም (የሐዋርያት ሥራ 4፡12 ይመልከቱ)፣ እኛ የምንድነው በክርስቶስ ስም ነው።

በክርስቶስ ምልጃ ምክንያት ፣ ሌሎች ማጣቀሻዎች ክርስቲያኖች ለጸሎታቸው እና ለአምላክ የሚያደርጉት አምልኮዎች ትርጉም ያገኛሉ፣ በመጀመሪያ ከእነሱ መካከል በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ድንግል ማርያም ናት።

እሷ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ልዩ ቦታን ትይዛለች ፣ ስለሆነም በጸሎታቸውም እንዲሁ፣ ምክንያቱም እርሷ የኢየሱስ እናት ነችና። የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ብዙውን ጊዜ “መንገዱን የምታሳየው” ማለትም በልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መንገዱን የምታሳየን እርሷ እንደሆነች አድርገው ይሳሏታል። የእርሷ ከእኛ ጋር መገኘቷ በክርስቲያናዊ ሥዕላዊ መግለጫ ሥፍራ ውስጥ ብዙን ጊዜ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፣ አንዳንድ ጊዜ በጣም ጎልቶ ይታያል ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ከልጅዋ ጋር እና ከእሱ ጋር በማያያዝ እርሷ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደ ምትሆን የሚገልጹ ሥዕላዊ መገለጫዎች አሉ። እጆቿ፣ አይኖቿ፣ ባህሪዏ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሕያው የሆኑ ትምህርተ ክርስቶስ ናቸው ፣ ዘወትር መደገፊያችን ማእከላችን ኢየሱስን ያመለክታሉ። ማርያም ሙሉ በሙሉ ወደ እርሱ ትመራናለች (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 2674 ን ይመልከቱ)።

ይህ ማሪያም በምድራዊ ሕይወቷ ሁሉ የተጫወተችው ሚና እና እሷ ለዘላለም የምትኖር እና በእዚህ መልኩ ተግባሯን የምታከናውን እናት-ትሑት የጌታ አገልጋይ መሆኗን ያሳያል። በወንጌሎች ውስጥ በተወሰነ ጊዜ ላይ እሷ የተደበቀች ይመስላል። ነገር ግን እንደ ቃና ዘገሊላ ባሉ በጣም አስፈላጊ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ እንደገና ትገለጣለች ፣ ለእርሷ ጣልቃ ገብነት ምስጋና ይግባውና ልጇ የመጀመሪያውን “ምልክት” የሆነውን ተዐምር ሲያከናውን (ዮሐ 2፡1-12ን ይመልከቱ) እና ከዚያ በኋላ በጉልጎታ በመስቀሉ ስር ተገኝታ ነበር።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ለተወዳጅ ደቀ መዝሙሩ በአደራ ሲሰጥጣት የማርያም እናትነት በቤተክርስቲያኑ ሁሉ ውስጥ እንዲስፋፋ አደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተወሰኑ የመካከለኛው ዘመን በነበሩ የጥበብ ሥራዎች ወይም ሥዕሎች ላይ እንደተገለጸው ሁላችንም በእሷ ጥበቃ ስር ተሰብስበናል።

እናም እርሷን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የሚገኙትን በርካታ አገላለጾችን በመጠቀም ለምሳሌ “ጸጋ የሞላሽ”፣ “ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ” የሚሉትን አገላለጾች በመጠቀም ወደ እርሷ እንጸልያለን (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 2676) በኤፌሶን ጉባሄ ላይ “ቴዎቶኮስ” “የእግዚአብሔር እናት” የሚለው ርዕስ ብዙም ሳይቆይ ወደ ጸጋ የሞላሽ ተሻግሯል። እናም ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ አባታችን ሆይ ከሚለው ጸሎት ጋር ፣ ከምስጋና በኋላ ፣ ልመናውን እንጨምራለን -ማርያም “አሁን እና በምንሞትበት ሰዓት” በርህራሄዋ እንድታማልደን ስለ እኛ ኃጢአተኞች እንድትጸልይ እንጠይቃለን። ወደ ሕይወት ዘመናችን በሚወስደው መተላለፊያችን ውስጥ እንድትሆን እኛን አሁን ፣ በተጨባጭ የሕይወት ሁኔታዎች እና በመጨረሻው ጊዜ ውስጥ ሳይቀር ከእኛ ጋር እንድትሆን እንማጸናታለን።

ማሪያም ከዚህ ዓለም ተለይተው ከሚሄዱ ሰዎች ጋር ከልጆቿ አልጋ አጠገብ ትገኛለች ። አንድ ሰው ብቻውን ከሆነ እና የተገለለ ከሆነ ሁሉም ሰው ሲተውት ከልጇ አጠገብ በመስቀል ሥር እንደ ነበረች ሁሉ ከተገለሉ እና ከተረሱ ሰዎች ጎን ሁልጊዜም ቢሆን በአጠግባቸው ትገኛለች ።

ማሪያም በእነዚህ የወረርሽኝ ቀናት ውስጥ ከእኛ ጋር ነበረች ፣ አሁን ትገኛለች፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ፣ የምድራዊ ጉዞአቸውን ብቻቸውን ያጠናቀቁ ፣ የሚወዷቸው ሰዎች ከአጠገባቸው በማይኖሩበት ወቅት፣ ወይም ሰው በሚርቀን ወቅት ሁሉ ማሪያም ሁል ጊዜ ከእናትነቷ ርህራሄ ጋር ትገኛለች።

ለእርሷ የተደረጉ ጸሎቶች በከንቱ አይቀሩም። “እነሆኝ” ያለች ፣ የመልአኩን ግብዣ በፍጥነት የተቀበለችው እናት እንዲሁ ለጸሎታችን ምላሽ ትሰጣለች ፣ በልባችን ውስጥ ተቆልፎ የሚገኘውን በልባችን ውስጥ የሚገኘውን ነገር እንኳን ለመናገር የሚያስችል ጥንካሬ የሌላቸውን ነገር ግን ከእኛ በተሻለ እግዚአብሔር የሚያውቀውን ልመናችንን ትሰማለች። ከሁሉም ጥሩ ከሚባሉ እናቶች በላይ ማርያም ከአደጋ ትጠብቀናለች፣  እኛ በራሳችን ነገሮች ላይ ብቻ ስንተኮር እና የመንገዶቻችን ስሜት ሲጠፋን ፣ እና ጤናችንን ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም አደጋ ላይ ስናስገባ እንኳን ስለእኛ ትጨነቃለች። እንዲሁም የእኛ መዳኛ ማርያም እዚያ አለች ፣ ስለ እኛ እየጸለየች ፣ ለማይጸልዩት ሰዎች እንኳን እርሷ ትጸልያለች። ምክንያቱም እርሷ እናታችን ነችና።

24 March 2021, 12:05