Vatican News
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአገልግሎት ከተሰጠ ሕይወት ጋር ኢየሱስን መስክሩ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በመጋቢት 12/2013 ዓ.ም ከቫቲካን ሆነው  ያደረጉት አስተንትኖ በእለቱ ከዮሐንስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበውና “የሰው ልጅ የሚከብርበት ሰዓቱ ደርሶአል፤ እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ሕይወቱን የሚወድ ያጣታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝንም አባቴ ያከብረዋል” (ዮሐንስ 12፡20-33) ላይ በተጠቀሰውና ኢየሱስ ስለ ሞቱ አስቀድሞ መናገሩን በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በአገልግሎት ከተሰጠ ሕይወት ጋር ኢየሱስን መመስከር እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከእዚህ በታች ያለውን የማጫወቻ ቁልፍ ይጫኑ!

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዚህ የዐብይ ጾም አምስተኛው እለተ ሰንበት (የጎሮጎርሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ማለት ነው) የስርዓተ አምልኮ ስነ ስረዓት ላይ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ከቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል የተወሰደ ሲሆን በክርስቶስ ሕይወት የመጨረሻ ቀናት ውስጥ የተከሰተውን ክፍል የሚያመለክተውን ወንጌል ያውጃል ፣ ከሕማማት ወቅት ቀደም ብሎ የተከናወነ ነገር ነበር (ዮሐንስ 12፡20-33)። ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም በነበረበት ወቅት በርካታ ግሪካውያን ስላደረገው ነገር ለማወቅ ጓጉተው እሱን ለማየት መፈለጋቸውን ገለጹ። ወደ ሐዋርያው ​​ፊልጶስ ቀርበው “ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” ይሉታል (ዮሐንስ 12፡ 21)። “ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” ማለት ነው። እስቲ ይህንን እናስታውስ “ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን?”። ፊልጶስ ለእንድርያስ ነገረው ከዚያም አብረው ለመምህሩ ሪፖርት አደረጉ። በእነዚያ ግሪኮች ጥያቄ ብዙ ወንዶችና ሴቶች በየቦታው እና በየቤተክርስቲያን እና እንዲሁም እያንዳንዳችን “ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” የሚል ጥያቄን ማየት እንችላለን።

ኢየሱስ ለቀረበለት ጥያቄ ምን ምላሽ ሰጠ? እንድናስብ በሚያደርገን መንገድ ነው መልስ የሰጠው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “የሰው ልጅ የሚከበርበት ሰዓቱ ደርሶአል፤ እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች” (ዮሐንስ 12፡23-24)። እነዚህ ቃላት እነዚያ ግሪኮች ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ አይመስሉም። በእውነቱ እነዚህ ምላሾች ከእዚያ ባሻገር የሄዱ ናቸው። በእርግጥ ኢየሱስ እሱን ለማግኘት ለሚፈልጉ ወንድ እና ሴት ሁሉ ብዙ ፍሬ ለማፍራት ለመሞት የተደበቀ ዘር መሆኑን ገልጧል። ይህም እኔን ለማወቅ ከፈለጋችሁ፣ እኔን ለመረዳት ከፈለጋችሁ፣ በአፈር ውስጥ የሚሞተውን የስንዴ እህል ተመልከቱ፣ ማለትም መስቀሌን ተመልከቱ እንደ ማለት ነው።

የመስቀሉ ምልክት ወደ አእምሯችን ይመጣል ፣ ይህም ባለፉት መቶ አመታት ውስጥ የክርስቲያኖች የሙሉ ልቀት ምልክት ሆኗል። ዛሬም ቢሆን “ኢየሱስን ማየት” የሚፈልጉ ፣ ምናልባትም ክርስትና ከማይታወቅባቸው ሀገሮች እና ባህሎች የመጡ፣ በመጀመሪያ ምን ማየት ይፈልጋሉ? የሚያጋጥሟቸው በጣም የተለመዱ ምልክቶች ምንድናቸው? ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል፣ የኢየሱስን መስቀል ነው የሚመለከቱ። በቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ፣ በክርስቲያኖች ቤት ውስጥ ፣ በሰውነታችን ላይ እንኳን የእርሱን መስቀል አጥልቀን እንጓዛለን። ዋናው ነገር ምልክቱ ከወንጌል ጋር የሚስማማ መሆኑ ነው-መስቀሉ ፍቅርን ፣ አገልግሎትን ፣ ያልተቆጠበ ራስን መስጠትን ብቻ የሚገልጽ መሆን ይኖርበታል፣ በዚህ መንገድ ብቻ በእውነት እርሱ “የሕይወት ዛፍ” ፣ የተትረፈረፈ ሕይወት መሆን የሚችለው በእዚሁ መንገድ ብቻ ነው።

በዛሬው ጊዜም ብዙ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ምንም ሳይናገሩ በተዘዋዋሪ “ኢየሱስን ማየት” ፣ እሱን ለመገናኘት ፣ እሱን ለማወቅ ይፈልጋሉ። እኛ ክርስቲያኖች እና ማኅበረሰባችን መረዳት ያለብንን ትልቅ ኃላፊነት የምንገነዘበው በዚህ መንገድ ነው። እኛም በአገልግሎት በተሰጠ ሕይወት ፣ የእግዚአብሔርን ዘይቤ - ማለትም ቅርብነትን ፣ ምህረትን እና ርህራሄን በመያዝ እና በአገልግሎት በሚሰጥ ሕይወት ምስክርነት መመለስ አለብን። እሱ ማለት በአጭር ቃል ሳይሆን በተጨባጭ ፣ በቀላል እና በድፍረት በሚሰጡ ምሳሌዎች ፣ በንድፈ ሃሳባዊ ውግዘቶች ሳይሆን ፣ በፍቅር ምልክቶች አማካኝነት የፍቅር ዘሮችን መዝራት ማለት ነው። ከዛም ጌታ በተፈጠረው አለመግባባት ፣ በችግር ወይም በስደት ፣ ወይም በሕጋዊነት ወይም በሊቀ ካህናት ሥነ ምግባሮች ምክንያት አፈሩ ቢደርቅም ፍሬውን እንድናፈራ ያደርገናል። ይህ መካን አፈር ነው ። በትክክል በዚያን ጊዜ ፣ ​​በሙከራ እና በብቸኝነት ፣ ዘሩ እየሞተ እያለ ፣ ያ በጊዜው ሞቶ ፍሬ በማፍራት ሕይወት እንዲያብብ ያደርጋል። የፍቅርን ደስታ እና እውነተኛ ፍሬ ማፍራት የምንችለው በዚህ በሞት እና በህይወት ትስስር ውስጥ ነው ፣ ሁል ጊዜም ፣ እደግመዋለሁ ፣ በእግዚአብሔር ዘይቤ የተሰጠው- ቅርበት ፣ ምሕረት እና ርህራሄ አማካይነት የተሰጠን ነው።

 የክርስቶስ ፍቅር በሁሉም አመለካከታችን ውስጥ እንዲበራ እና የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤያችን የበለጠ እየሆነ እንዲሄድ ኢየሱስን እንድንከተል ፣ በአገልግሎት ጎዳና እንድንጓዝ ፣ ጠንካራ እና ደስተኛ እንድንሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

21 March 2021, 09:44

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >