ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሁላችንም ከአንድ አባት የተወለድን ነን ማለታቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባሄ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእየ አመቱ  ጥር 27 ቀን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ቀን ሆኖ እንዲከበር መወሰኑን ተከትሎ ጥር 27/2013 ዓ.ም ላይ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ቀን ስብሰባ በበይነ መረብ አማካይነት ተካሂዶ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ ስብሰባ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጨምሮ የአል-አዝሃር ታላቁ ኢማም አህመድ አህመድ-ታይየብ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴረዝ እና ሌሎች ተገባዥ እንግዶች መሳተፋቸው ይታወሳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ጥር 27/2013 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መንድማማችነት ቀን ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ውስጥ የወንድማማችነትን ጭብጥ አጉልተዋል አንስተዋል። እርሳቸው በመልእክታቸው አክለው እንደ ገለጹት ወንድማማቾች እና እህተማማቾች የመሆን ምርጫ ማድረግ እንደ ሚቻል የገለጹ ሲሆን አሊያም ሁሉንም ነገር እናጣለን በማለት በአክብሮት መልእክታቸውን ለመላው ዓለም አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ቀን ሀሙስ ዕለት ጥር 27/2013 ዓ.ም ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በአቡ ዳቢ በበይነ መረብ አማካይነት ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ ታላቁ የአል-አዛር ኢማም አህመድ ታየብ፣ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አቶ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች የታደሙበት ስብሰባ እንደ ነበረም ተገልጿል።

በእለቱ በስብሰባው ላይ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ ባደረጉት ንግግር ተግዳሮቶች ቢኖሩም ወንድማማችነትን ለማስተዋወቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እህቶች እና ወንድሞች - እነዚህ ቃላት ቃላቶቻችን ሊሆኑ የገባል” ያሉ ሲሆን በወንድማማችነት መንፈስ የተሞላ ዓለም ለመፍጠር ምንም አንኳን ርካታ የሆኑ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሙን ቢሆንም ቅሉ እነዚህን ተግዳሮቶች እና አደጋዎችን ተጋፍጠን የሰብዓዊ ወንማማችነት መንፈስ በዓለም ውስጥ እንዲሰርጽ ማደረግ እንችላለን ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሁለት ዓመት በፊት የቀረበው ሰነድ እንዲረቅ ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱት  ለምስክርነታቸውና ላደረጉት ትብብር ታላቁ ኢማም አህመድ አል-ታይየብ ልዩ እውቅና የሰጡ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአቡዳቢ ኢሚሬትስ ዘውዳዊ ልዑል ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በእዚህ ለሰብዓዊ ወንማማችነት በሚደረገው ጥርት እመንት በመጣላቸው እና የሕግ ባለሙያ የሆኑት አብዱል ሰላምም ለእዚህ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ማሕበር ለእድገቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለወንድማማችነት መንፈስ ራሳችሁን በመስጠታችሁ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ ፣ ምክንያቱም ዛሬ ወንድማማችነት የሰው ልጅ አዲስ ተግዳሮት ነው፣ ወይ ወንድማማቾች ነን ፣ ወይም እርስ በእርስ እንጠፋፋለን በማለት ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገለጸዋል።

የግዴለሽነት ጊዜ አይደለም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ዛሬ ለግድየለሽነት ጊዜ የለንም” እና አሁን ያለውን ሁኔታ በርቀት ፣ በንቀት እና በቁራኛ በመመልከት “እጃችንን ታጥበን መቀመጥ አንችልም” በማለት አጥብቀው ተናግረዋል። እኛ ወንድማማቾች ወይም እህተማማቾች መሆናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል “ወይም ሁሉም ነገር ይፈርሳል” እኛ በእዚህ ምክንያት ይህንን የሰብዐዊ ወንድማማችነት መንፈስ ተጠናክሮ በዓለም ውስጥ ይቀጥል ዘንድ “የዘመናችን ፈታኝ እና የዘመናችን ተግዳሮት” የሆኑትን ነገሮች ሁሉ መጋፈጥ ይኖርብናል ብለዋል።

ወንድማማችነት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ “የተዘረጋ እጅ ማለት ነው። ወንድማማችነት መከባበር ማለት ነው። ወንድማማችነት ማለት በተከፈተ ልብ ማዳመጥ ማለት ነው። ወንድማማችነት ማለት በራስ እምነት ውስጥ ጽናት ማለት ነው” ብለዋል።

ልዩነቶች ቢኖሩም ወንድሞች እና እህቶች ነን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በባህሎች እና ወጎች መካከል ልዩነቶች ቢኖሩም እኛ “ከአንድ አባት የተወለድን” ወንድማማቾች እና እህተማማቾች መሆናችንን” በአጽንኦት ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ወንድማማችነት በድርድር ሳይሆን የተለያዩ ባህሎቻችንና ወጎችን በማክበር መገንባት አለበት ብለዋል።

“የመደመጥ ጊዜ ነው። ከልብ የመቀበል ጊዜ ነው። ወንድማማቾች የሌሉበት ዓለም የጠላት ዓለም መሆኑ በእርግጠኝነት የተረጋገጠበት ወቅት ነው” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ። በተጨማሪም “እኛ ወንድማማቾች ነን ወንድማች አይደለንም ማለት አንችልም” በማለት አጉልቶ በመግለጽ ይልቁንም ግድየለሽነት “በጣም ረቂቅ የጥላቻ” ባሕርይ በመሆኑ “እኛ ወንድማማቾች መሆን ይኖርብናል፣ አለበለዚያ ግን እርስ በእርሳችን እንደ ጠላቶች ሆነን ነው የምንፈራረጀው” በማለት አጥብቀው አሳስቧል።

“እንደ ጠላት ለመፈራረጅ ደግሞ በጦርነት ላይ መሆን አያስፈልገንም ፣ እርስ በርሳችን አለመከባበራችን በራሱ በቂ ነው” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ነገሮችን አጣመን የመመልከት እና ሌሎች እንዳልተፈጠሩ አድርገን የመመልከት ዝንባሌን የማስወገጃው ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።

እ.አ.አ የ2021 የዛይድ ሽልማት ለሰብዓዊ ወንድማማችነት

ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ የወንድማማችነት ቀን ክብረ በዓል አንድ አካል የሆነው ደግሞ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የሞሮኮ እና የፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ  ላቲፋ ቤን ዛያቲን እ.አ.አ የ 2021 ዓ.ም የዛይድ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ሽልማት እንደ ተቀበሉም ተገልጿል። ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴረዝን በተመለከተ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ላገኙት ሽልማት “እንኳን ደሳልዎት” በማለት የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ በዓለማችን ውስጥ ሰላም እና ብልጽግና የሚረጋገጠው “በወንድማማችነት ልብ ብቻ በሚከናወኑ ተግባራት አማካይነት ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትኩረታቸውን ወደ ሁለተኛዋ የ 2021 ዓ.ም ዛይድ ሽልማት ተቀባይ ወደ ሆኑት ክብርት ወይዘሮ ላቲፋ ቤን ዛያቲን በማዞር ልጃቸውን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በማጣታቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ሐዘን ወደ ፍቅር እና ወንድማማችነትን ለማጎልበት በማስተላለፍ አነቃቂ የሆኑ ምስክርነታቸውን በመስጠታቸው ይህንን ሽልማት በመቀበላቸው ቅዱስነታቸው መደሰታቸውን አክለው ገለጸዋል።

“አዎ አህታችን የእርሶ ቃላቶች አሉባልታ ወይም የተለመዱ ነገሮች አይደለም፣ ሁላችንም ወንድማማቾች ነን ከሚል እምነት የተወለዱ ናቸው አንጂ። በሥቃይዎ ፣ በቁስሎችዎ ውስጥ የተካተተ ከፍተኛ ከሆነ ውሳኔ የተወለደ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ስለ ምስክርነቶ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ” በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው “የልጆ እናት በመሆኖ አመሰግኖታለሁ፣ የብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም እርስዎን በማዳመጥ ላይ የሚገኙ እና ከእርስዎ በመማር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ እናት በመሆኖ፣ ሁላችንም ወንድማማቾች ነን፣ ካለእዚያ ግን ሁላችንም ተያይዘን እንጠፋለን፣ ሁሉንም ነገር እናጣለን” በማለት እየሰጡት ለሚገኙት ምስክርነት እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁኝ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

05 February 2021, 14:02