ጋዜጠኞች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የምያስተላለፉትን መልእክት ለመዘገብ በመጠባበቅ ላይ ባሉበት ወቅት ጋዜጠኞች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የምያስተላለፉትን መልእክት ለመዘገብ በመጠባበቅ ላይ ባሉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሰዎች ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ በአካል ተገናኝቶ መወያየት ያስፈልጋል አሉ!

55 ኛው የዓለም የኮምኒኬሽን ቀን በጥር 15/2013 ዓ.ም ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ለእዚህ 55ኛው ዓለም አቀፍ የኮምኒኬሽን ቀን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያስተላለፉት መልእክት መሪ አርእስት “መጥተህ እይ” የሚለው ቃል እንደ ሆነም ተገልጿል። ሰዎችን የት እና በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደ ሚገኙ በአከል  በማግኘት መግባባት ተገቢ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ላይ የጠቀሱ ሲሆን አክለውም ሁልጊዜ ተመሳሳይ የሆነ የመረጃ ስጋት እንዳይኖር በማስጠንቀቅ “ማንም መሄድ ወደ ማይፈልግበት ቦታ በመሄድ” ማበረታታት እና በሀብታሙ ዓለም ዓይኖች ብቻ የታየውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳይሆን የገሃዱን ዓለም ሁኔታ ተመልክቶ መዘገብ አስፈላጊ እንደ ሆነ በመልእክታቸው ቅዱስነታቸው አክለው አሳስቧል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለ55ኛው ዓለም አቀፍ የኮምኒኬሽን ቀን ያስተላለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።  

“መጥተህ እይ” (ዮሐ 1፡46)። ከሰዎች ጋር የት እና እንዴት እንደሆኑ በአካል በመገናኘይ ይነጋገሩ!

ውድ ወንድሞች እና እህቶች

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከነበረው የመጀመሪያ አስደሳች ገጠመኞች ጋር አብሮ የሚመጣው “መጥተህ እይ” የሚለው ግብዣ የሁሉም ትክክለኛ የሰው ልጅ የግንኙነት ዘዴም ነው። የሕይወት ታሪክን እውነተኛ በሆነ መልኩ ለመናገር “ቀድሞ ከሚታወቀው” ምቹ ግምት ወጥቶ መንቀሳቀስ ፣ ከሰዎች ጋር ለመሆን መሄድ እና ማየት ፣ አብሮ መቆየት ፣ እነርሱን ማዳመጥ፣ እውነታዎች የሚያሳዩትን ጥቆማዎች መሰብሰብ አስፈላጊ የሆነ ነገር ሲሆን፣ ይህም በአንዳንድ ገጽታዎች ውስጥ ሁልጊዜ ያስደንቀናል። ብፁዕ ማኑዌል ሎዛኖ ጋርሪዶን “በምታየው ነገር በመደነቅ ዐይንህን ክፈት ፣ እጆችህም በአዲስ ሕይወት ሰጭ በሆኑ ፈሳሾች እንዲሞሉ አድርግ፣ ሌሎችም አንተን ሲመለከቱ ልብ በሚነካ የሕይወት ተአምር እንዲነኩ አድርግ ” በማለት የእርሱ ጓደኞች ለነበሩ ጋዜጠኞች መክሯል። ስለሆነም ግልፅ እና ሐቀኛ መሆን ለሚፈልግ ማንኛውም የግንኙነት መግለጫ ለመጠቆም ያህል ለእዚህ አመት ዓለም አቀፍ የኮምኒኬሽን ቀን መልእክት ይሆን ዘንድ “መጥተህ እይ” ለሚለው ጥሪ መልስ እንድንሰጥ እፈልጋለሁ ፤ በድህረ ገጾች በተሞላው ዓለም ውስጥ በሚገኙ በጋዜጣ አርትዖት ላይ ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በተለመደው የቤተክርስቲያን ስብከት ውስጥ፣ የፖለቲካ ወይም ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ያሉትን ነገሮች እንድንመለከት እጋብዛለሁ። ከእነዚያ የመጀመሪያ ግንኙነቶች ጀምሮ በዮርዳኖስ ወንዝ እና በገሊላ ሐይቅ ላይ ከሚገኙት የመጀመሪያ ግንኙነቶች አንስቶ የክርስቲያን እምነት የሚገናኝበት “መጥተህ እይ” የሚለው ቃል ነው።

የተበላው የጫማ ሶል

እስቲ ስለ ታላቁ የመረጃ ጉዳይ እናስብ። ትኩረት የሚሰጡባቸው ድምፆች በ ‹ፎቶ ኮፒ በተባዙ ጋዜጦች› ወይም በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ ዜናዎች እና በድረ ገጾች የሚተላለፉ ዜናዎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ሲሆኑ የምርመራ እና የሪፖርት ዘገባዎች መረጃን ለመጠቀም የሚያስችለውን ቦታ እና ጥራት የማጣት አደጋን በተመለከተ ቅሬታ ሲቀርብባቸው የቆየ ሲሆን ራሳቸውን ብቻ የሚመለከቱ ፣ የነገሮችን እውነታ እና የሰዎችን ተጨባጭ ህይወት ለመጥለፍ እና ለማቃለል የሚያደርጉት ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣቱ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ በኋላ በጣም ከባድ የሆኑ ማህበራዊ ክስተቶችን ወይም ከኅብረተሰቡ መሠረት የሚለቀቁትን አዎንታዊ ኃይሎች መገንዘብ የማይችል ነው። በዜና ክፍሎች ውስጥ ፣ በኮምፒዩተሮች ፊት ለፊት ፣ በኤጀንሲ ጣቢያዎች ውስጥ፣ በማህበራዊ አውታረመረቦች ውስጥ በመሳተፍ በጭራሽ ወደ ጎዳና ሳይወጡ “የጫማዎን ሳል ሳይጨርሱ”  ሰዎችን በመገናኘት ወደ ተከማዎቻቸው በመሄድ መረጃዎችን የሚያደርሱ የሕትመት ታሪኮችን ወይም የተወሰኑ ሁኔታዎችን ፊት-ለፊት ሳይገፈጡ የተረጋገጡ ናቸው በማለት ይዘግባሉ። ለመገኛት ራሳችንን ካላዘጋጀን የምንጠመቅበት ከሚመስለው የተጨመረው እውነታ ፊት ለፊት የማስቀመጥ ችሎታ ያላቸው የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ቢኖሩም የውጭ ተመልካቾች እንሆናለን። እያንዳንዱ መሣሪያ ጠቃሚ እና ውድ የሚሆነው እኛ የማናውቃቸውን ነገሮች በአካል በመሄድ እንድንመለከት ሲገፋፉን፣ በሌላ መንገድ የማይሰራጨውን የተጣራ እውቀት ከለበሰ ፣ ካልሆነ ደግሞ ግንኙነት እንዲፈጠር የሚፈቅድ ከሆነ ብቻ ነው።

እነዚያ የዜና ዝርዝሮች በወንጌሉ ውስጥ

ለመጀመሪያ ጊዜ እሱን ለማወቅ ለሚፈልጉት ደቀ መዛሙርት ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስ “ኑና  እዩ” (ዮሐ 1፡39) ሲል መለሰላቸው ፣ ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ጋበዘ።  ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ወንጌላዊው ዮሐንስ በጣም አርጅቶ ነበር፣ በወንጌሉ በቦታው መገኘቱን እና ተሞክሮ በሕይወቱ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ የሚያሳዩ አንዳንድ “ዜና” ዝርዝሮችን ያስታውሳል-“ወደ አሥረኛው ሰዓት ገደማ ነበር” ሲል ማስታወሱ ይህም ማለትም ከሰዓት በኋላ አራት ሰዓት ገደማ ነበር ማለት ነው (ዮሐንስ 1፡ 39)። በሚቀጥለው ቀን - ዮሐንስን ትረካውን ሲቀጥል - ፊልፖስ ከመሲሑ ጋር መገናኘቱን ለናትናኤል ነገረው። ጓደኛው ተጠራጣሪ ሰው ነው “ከናዝሬት ጥሩ ነገር ሊመጣ ይችላልን?” በማለት ፊሊፖስ ሲመልሰለት በምክንያት ለማሳመን አይሞክርም  “ኑና እዩ” በማለት ይመልሳል (ዮሐንስ 1፡45-46)። ናትናኤልም ሄዶ ያያል ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሕይወቱ ተለወጠ። የክርስትና እምነት እንደዚህ ይጀምራል። እናም በዚህ መንገድ ያስተላልፋል-እንደ ቀጥተኛ እውቀት ፣ ከልምድ የተወለደው ፣ ሲነገር በመስማት እና በመስማት ብቻ ሳይሆን በማየት ጭምር ነው። ሕዝቡ ኢየሱስ በመንደራቸው ከቆመ በኋላ ለሳምራዊቷ ሴት “እኛ ከእንግዲህ በንግግርህ አይደለም የምናምነው እኛ ራሳችን ስለሰማን ነው” በማለት ለሳምራዊቷ ሴት መናገራቸው ይታወሳል (ዮሐ 4፡39-42)። እውነታውን ለማወቅ “ኑና እዩ” ቀላሉ ዘዴ ነው። እሱ የሁሉም ማስታወቂያዎች እጅግ ሐቀኛ ማረጋገጫ ነው ፣ ምክንያቱም አንድን ሰው በሚገባ ለማወቅ እርሱን መገናኘት ይኖርብናል፣ ከፊት ለፊቴ ሆኖ እንዲናገር ልፈቅድለት ይገባል፣ የእሱ ምስክርነት ሊደርሰኝ ይገባል።

ለብዙ ጋዜጠኞች ብርታት ምስጋና ይድረስ

ጋዜጠኝነትም እንዲሁ የእውነተኛ ታሪክ ትረካ ከመሆኑ አንጻር ማንም ሂዶ መዘገብ ወደ ማይፈልግበት ቦታ ሂዶ የመዘገብ ችሎታን ይፈልጋል - መንቀሳቀስ እና የማየት ፍላጎት ያስፈልጋል። የማወቅ ጉጉት፣ ግልጽነት ፣ ፍላጎት ያስፈልጋል። ለብዙ ባለሙያዎች ድፍረት እና ቁርጠኝነት አሁንም ምሥጋና ይግባውና - ማለትም ለጋዜጠኞች ፣ ንድፍ አውጪዎች ፣ ሄዲተሮች፣ ቀራጮች ብዙውን ጊዜ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሆነው ለሚሰሩ ሰዎች ምስጋና ማቅረብ አለብን፣ ለምሳሌ ዛሬ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለተሰደዱ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታ እንድናውቅ ካደረጉን፣ በድሆች እና በፍጥረታት ላይ የሚደርሱ ብዙ በደሎች እና ኢፍትሐዊነቶች ከተወገዙ፣ ብዙ የተረሱ ጦርነቶች የሚዘገቡ ከሆነ እነዚህን ነገሮች ለሚዘግቡ ሰዎች ምስጋና ማቅረብ ይገባል። እነዚህ ድምፆች ቢከሽፉ ለመረጃ ብቻ ሳይሆን ለመላው ህብረተሰብ እና ለዴሞክራሲ ኪሳራ ይሆናል ለሰብአዊነታችን ድህነትን ይፈጥራል።

በፕላኔቷ ላይ ያሉ በርካታ እውነታዎች ፣ በዚህ በወረርሽኝ ጊዜ ውስጥ እንኳን ፣ የመገናኛውን ዓለም “መጥታችሁ እዩ” በማለ እየጋበዙ ነው። የተከሰተውን ወረርሽኝ እንደገና ያለመናገር አደጋ አለ ፣ ስለሆነም እያንዳንዱ ቀውስ በሀብታሙ ዓለም ዓይኖች ብቻ የመመልከት ስጋት አለ፣ “ድርብ ሂሳብ” የመያዝ አደጋ አለ። ስለ ክትባቶች ጉዳይ እንመልከት፣ በጣም የተቸገሩ ሰዎችን የማግለል ስጋት አለ፣  እንዲሁም በአጠቃላይ የሕክምና እንክብካቤን እናስብ። በእስያ ፣ በላቲን አሜሪካ እና በአፍሪካ በጣም ድሃ በሆኑ መንደሮች ውስጥ ስላለው ከወረርሽኙ ለማገገም ያላቸውን ፍላጎት ማን ይነግረናል? ስለሆነም በዓለም አቀፍ ደረጃ የፀረ-ኮቪድ ክትባቶች ስርጭትን ቅደም ተከተል የሚያመለክቱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶች አሉ። ድሆች ሁልጊዜም የመጨረሻው ደረጃ የሚሰጣቸው ሲሆን ነገር ግን በመርህ ደረጃ ሁሉም የጤና እንክብካቤ መብት እንዳላቸው በመርህ ደረጃ የተረጋገጠ ነው፣ እውነታው ግን ከእዚህ እሴት የተለየ ነው። ነገር ግን እጅግ በጣም ዕድለኛ በሆነው ዓለም ውስጥ እንኳን በፍጥነት ወደ ድህነት የገቡ ቤተሰቦች ማህበራዊ ድራማ በአብዛኛው ተደብቆ ቆይቷል -እነሱ እራሳቸውን አሸንፈው በእርዳታ መስጫ ተቋማት እና ማዕከላት ፊት ለፊት ወረፋ ይዘው የምግብ እርዳታ ለመቀበል የሚጠባበቁትን ሰዎች ሁኔታ የሚዘግቡ ብዙ ዜናዎች አይታዩም።

በድረ ገጾች ላይ ያሉ ዕድሎች እና ወጥመዶች

አውታረ መረቡ ፣ ስፍር ቁጥር በሌላቸው ማህበራዊ መግለጫዎቹ ፣ ታሪኮችን ለመተረክ እና ለሌሎች የማጋራት አቅምን ማዳበር ይችላል - ብዙ ተጨማሪ ዓይኖች ለዓለም ክፍት ናቸው ፣ ቀጣይነት ያለው የምስሎች ፍሰት እና የምስክርነቶች ይገኙበታል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ እና ወቅታዊ መረጃን እድል ይሰጠናል ፣ አንዳንድ ጊዜ በጣም ጠቃሚ ነው - የመጀመሪያዎቹን ዜናዎች እና ሌላው ቀርቶ ለሕዝቡ የመጀመሪያ የአገልግሎት ግንኙነቶች እንኳን በቀጥታ ድረ ገጽ ለሚጠቀሙ ሰዎች የሚያደርሰውን አንዳንድ ድንገተኛ ሁኔታዎችን እናስብ። እሱ አስፈሪ መሳሪያ ነው ፣ ይህም ሁላችንም እንደ ተጠቃሚዎች እና እንደ ዜና አቅራቢዎች እንድንሆን ያደርገናል። ምናልባትም ሁላችንም በባህላዊ ሚዲያዎች ችላ ተብለው ለሚታዩ ክስተቶች ምስክሮች ልንሆን እንችላለን ፣ የሲቪል አስተዋፅዖችን እናበረክታለን ፣ ብዙ ታሪኮችን እና አዎንታዊ ገጽታዎችን እንኳን እናወጣለን። ለአውታረ መረቡ ምስጋና ይድረሰውና ያየነውን ፣ በዓይናችን ፊት የሚሆነውን የመናገር ፣ ምስክሮችን የማካፈል እድል አለን።

ነገር ግን ያለማረጋገጫ በሚሰጡ ዘገባዎች አማካይነት ማህበራዊ ግንኙነት አደጋዎች ውስጥ መግባቱን አሁን ለሁሉም ሰው ግልፅ ሆነዋል። ዜናዎችን እና ምስሎችን እንኳን በሺዎች ምክንያቶች ፣ አልፎ አልፎም ራሳችንን ለማድነቅ ብቻ በማሰብ ጭምር ዜናዎችን እና ምስሎችን እንኳን በቀላሉ እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከረጅም ጊዜ በፊት ተምረናል። ይህ ወሳኝ ግንዛቤ የምንጠቀምበትን መሳርያ ሰይጣናዊ በሆነ መልኩ እንዳንጠቀምበት ይረዳናል፣ ነገር ግን በሚሰራጭበት ጊዜም ሆነ ይዘቱ በሚቀበልበት ጊዜ የመረዳት ችሎታን እና የበለጠ የበሰለ የኃላፊነት ስሜት እንዲኖረን ይገፋፋል። እኛ ለምናደርጋቸው ግንኙነቶች ፣ ለምንሰጣቸው መረጃዎች ፣ የሐሰት ዜናዎችን በአንድ ላይ የምንቆጣጠር እና የምናጋልጥ ሰዎች እንሆናለን። ሁላችንም የእውነት ምስክሮች እንድንሆን ሂደን እንድንመለከት እና ያየነውን ለሌሎች እንድናጋራ ተጠርተናል።

በዓይን ማየትን የሚተካ ምንም ነገር የለም

በግንኙነት ውስጥ በአካል ማየትን ሙሉ በሙሉ ሊተካ የሚችል ምንም ነገር አይኖርም። አንዳንድ ነገሮችን መማር የሚቻለው እነሱን በመለማመድ ብቻ ነው። በእውነቱ አንድ ሰው በቃላት ብቻ አይነጋገርም ፣ ነገር ግን በዓይኖች ፣ በድምፅ ቃና ፣ በምልክቶች ጭምር ነው የሚናገረው። ኢየሱስን ለተገናኙ ሰዎች ጠንካራ መስህብ የነበረው እርሱ የሚያደርጋቸው ስብከቶች ብቻ ላይ የተመረኮዘ ሳይሆን፣ ነገር ግን የተናገረው ነገር ውጤታማነት ከዓይኖቹ ፣ ከአመለካከቱ እና ከዝምታዎቹ እንኳን የማይነጠል ነበር። ደቀ መዛሙርቱ የእርሱን ቃላት ከማዳመጥም አልፎ እርሱ ሲናገር ተመልክተውታል። በእውነቱ በእሱ ውስጥ - አካል ያለው ቃል - ቃሉ ፊት ሆነ ፣ የማይታየው እግዚአብሔር ራሱ ዮሐንስ እንደጻፈው እንዲታይ ፣ እንዲነካ እና እንዲዳሰስ ፈቀደ (1 ዮሐ 1፡1-3)። ቃሉ ውጤታማ የሚሆነው እርስዎ “ካዩ” ብቻ ነው ፣ በአንድ ተሞክሮ ውስጥ ፣ በውይይት ውስጥ እርስዎን ካሳተፈ ብቻ። በዚህ ምክንያት “መጥታችሁ እዩ” የሚለው ቃል እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

በዘመናችንም ቢሆን ፣ በሁሉም የሕዝባዊ ሕይወት ፣ በንግድ እንዲሁም በፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ምን ያህል ባዶ ንግግሮች እንደሚበዙ እናስብ። ማለቂያ የሌለው ንግግር ይደረጋል ነገር ግን ምንም መልእክት አያስተላልፍም።  የእሱ ምክንያቶች በሁለት የጥራጥሬ ገለባ ውስጥ ያሉ ሁለት የስንጌ ፍሬዎችን ይመስላሉ። እነሱ የሚሉትን ነገር ለመረዳት ቀኑን ሙሉ መድከም የምኖርብን ሲሆን ፈልገን ስናገኛቸው ግን ለፍለጋ ያወጣናን ያህል ዋጋ አይኖራቸውም። የእንግሊዛዊው የተውኔት ጸሐፊ ወቀሳ የተሞሉ ቃላቶች ለእኛም ክርስቲያን ለሆንን የኮምኒኬሽን ሰዎች ትክክለኛ ናቸው። የወንጌል ምሥራች ከሰው ወደ ሰው ፣ ከልብ-ወደ ልብ በሚደረጉ ግንኙነቶች አማካኝነት በመላው ዓለም ተሰራጭቷል። “መጥታችሁ እዩ” የሚለውን ተመሳሳይ ግብዣ የተቀበሉ ወንዶች እና ሴቶች  ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከቱ ሰዎች እይታ ፣ ቃል እና የእጅ እንቅስቃሴ በተከናወነው የሰው ልጅ “በተጨማሪ” ተገረሙ። ሁሉም መሳሪያዎች አስፈላጊ ናቸው ፣ እናም ፓኦሎ ዲ ታርሶ የተባለ ታላቅ የኮምኒኬሽን ባለሙያ  ቃል በእርግጥ ኢሜል እና በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉትን መልዕክቶችን ይጠቀም ነበር፣ ነገር ግን በዘመኑ የነበሩትን ሰዎች እርሱ ሲሰብክ የሰሙት እና አብረው ጊዜ ለማሳለፍ ፣ በስብሰባ ወቅት ወይም በግለሰባዊ ውይይት ውስጥ እሱን ለማየት ዕድለኛ የነበሩትን የእሱ እምነት ፣ ተስፋ እና የፍቅር ሥራ ያደንቁ ነበር። በእግዚአብሔር ጸጋ ተሸካሚ የሆነው የመዳን ታሪክ ስብከት ምን ያህል እውነተኛ እና ፍሬያማ እንደነበረ እርሱ በሚኖርባቸው  ቦታዎች መጥተው በተግባር ሲያዩት አረጋግጠዋል። እናም ይህ የእግዚአብሔር ተባባሪ ሰራተኛ በአካል ሊገናኝ በማይችልበት ቦታ እንኳን ፣ በክርስቶስ ውስጥ የኖረው የአኗኗር ዘይቤ በላኳቸው ደቀ መዛሙርት መስክሯል (1 ቆሮ 4፡17)።

ቅዱስ አውጎስጢኖስ “በእጃችን ያሉት መጻሕፍት በእጃችን ያሉ እውነታዎች ናቸው” ይል የነበረ ሲሆን ቅዱስ አጎስጢኖስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት ትንቢቶች መከሰታቸውን በእውነት እንድንመሰክር ይመክራል። ስለዚህ ቅዱስ ወንጌል ከኢየሱስ ጋር በመገናኘታቸው ህይወታቸው የተለወጡ ሰዎችን ግልፅ ምስክርነት በተቀበልን ቁጥር ዛሬ እንደገና ይከሰታል። ከሁለት ሺህ ዓመታት ለሚበልጡ ጊዜያት የተገናኙ ሰንሰለቶች የክርስቲያንን ጀብዱ አስገራሚ ነገር አስተላልፈዋል። ስለዚህ የሚጠብቀን ፈታኝ ሁኔታ ሰዎችን ባሉበት ቦታ እና ባሉበት ሁኔታ ከእነርሱ ጋር እንዴት መገናኘት እንዳለብን እና የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ ነው።

ጌታ ሆይ ፣ ከራሳችን መጥተን እውነትን ፍለጋ መሄድ እንድንችል አስተምረን።

ጭፍን ጥላቻን እንዳናዳብር፣ በችኮላ ድምዳሜ ላይ እንዳንደርስ፣ እንድንሄድ እና እንድንመለከት አስተምረን።

ለመረዳት ጊዜ እንድንወስድ፣ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ትኩረት ለመስጠት ፣ከመጠን በላይ በሆኑ ነገሮች እንዳንዘናጋ፣ ከእውነታው አሳሳች ገጽታን ለመለየት እንችል ዘንድ ማንም ወደ ማይፈልግበት እንድንሄድ አስተምረን።

በዓለም ውስጥ አንተ ለምትገኝባቸው ቦታዎች ዕውቅና ለመስጠት እና ያየነውን በሐቀኝነት ለመናገር ጸጋውን ስጠን።

ሮም ፣ ከቅዱስ ዮሐንስ ላቴራን ባዚሊካ እ.ኤ.አ. ጥር 23/2021 የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዲ ላሳል አመታዊ በዓል መታሰቢያ ዋዜማ ላይ የተላለፈ መልእክት።

23 January 2021, 13:55