ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ የሕይወት ደረጃ ወደ ለውጥ ይጠራናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ ጥር 16/2013 ዓ.ም በቫቲካን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ያደረጉት አስተንትኖ መሰረቱን ያደረገው “ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፣ ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ መረብ ወደ ባሕር ሲጥሉ አያቸው። ኢየሱስም፣ “ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት” (ማርቆስ 1፡14-20) በሚለው የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መመረጥ በሚያመልክተው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ልባችንን ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ባልንጀሮቻችን ፍቅር ለመቀየር እያንዳንዱ አፍታ ትክክለኛ ጊዜ መሆኑን ክርስቲያኖችን እንዲያስታውሱ ቅዱስነታቸው የጋበዙ ሲሆን “እግዚአብሔር በእያንዳንዱ የሕይወት ደረጃ ወደ ለውጥ ይጠራናል” ማለታቸው ተገልጿል። 

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዚህ እሑድ ቅዱስ ወንጌል ምንባብ (ማርቆስ 1፡14-20)  ለመናገር ያህል ከመጥመቁ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ “ዱላ ቅብብሎሹ መተላለፉን” ያሳየናል። መጥመቁ ዮሐንስ የእርሱ መንገድ ጠቋሚ ነበር፣ ምድሪቱን እና መንገዱን ለእርሱ አዘጋጅቷል -አሁን ኢየሱስ ተልእኮውን መጀመር እና አሁን የመዳንን ቃል ማወጅ ጀምሯል። የእሱ ስብከት በእነዚህ ቃላት ተጠቃልሏል “ጊዜው ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች። ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ ”(ዮሐንስ 1፡15) ይለናል። ጊዜን እና መለወጥ በሁለት አስፈላጊ ጭብጦች ላይ እንድናሰላስል የሚጋብዝ መልእክት ነው።

በዚህ የወንጌላዊው ማርቆስ ጽሑፍ ውስጥ ፣ ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ሰራው የድነት ታሪክ ቆይታ ተደርጎ ገንዛቤ መወሰድ አለበት፣ ስለዚህ “የተፈጸመው” ጊዜ ይህ አስደናቂ እርምጃ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርስበትና ሙሉ በሙሉ የሚገነዘበው ነው -እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከበትና መንግሥቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ “ቅርብ” የሆነበት ታሪካዊ ወቅት ነው። ሆኖም  መዳን ወዲያው በፈጣን ሁኔታ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም፤ መዳን የፍቅር ስጦታ ነው እናም እንደዚህ በነፃ የተሰጠ እና በነፃ የተሰጠ ምላሽን ይጠይቃል-መለወጥን ይጠይቃል። ስለሆነም አስተሳሰብን መለወጥ እና ሕይወትን መለወጥ ማለት ነው፣ ከእንግዲህ የዓለም ምሳሌዎችን መከተል ማለት አይደለም ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር መንገድ እንድንከተል ነው ያሳየን። እሱ ወሳኝ የአካሄድ እና የአመለካከት ለውጥ ነው። በእውነቱ ፣ ኃጢአት በሌሎች ላይ እና በእግዚአብሔር ላይ ራስን የማረጋገጥ ዝንባሌን ወደ ዓለም አምጥቷል ፣ እናም ለዚህ ዓላማ ማታለል እና ዓመፅን ከመጠቀም ወደኋላ አይልም።

ይህ ሁሉ እግዚአብሔር እና የእግዚአብሄር ጸጋ እንደሚያስፈልገን እራሳችንን እንድናውቅ በሚጋብዘው የኢየሱስን መልእክት ይቃወማል። ስለ ምድራዊ ዕቃዎች ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖር ማድረግ፣ ለሌሎችን መቀበል እና ትሁት መሆን፣ ከሌሎች ጋር ስንገናኝ እና በአገልግሎት ውስጥ እራሳችንን ለማወቅ እና ለመፈፀም ስንጥር ደህንንተ እናገኛለን። ለእያንዳንዳችን ቤዛን ለመቀበል የምንችልበት ጊዜ አጭር ነው፣ በዚህ ዓለም ውስጥ የሕይወታችን ቆይታ ነው። የእግዚአብሔር ማለቂያ የሌለው ፍቅር ስጦታ ነው ፣ ነገር ግን ለእሱ ያለንን ፍቅር የምናረጋግጥበት ጊዜም እንዲሁ ነው። በዚህ ምክንያት በእያንዳንዱ ቅጽበት ፣ እያንዳንዱ የሕልውናችን ጊዜ እግዚአብሔርን እና ጎረቤትን የምንወድበት እና በዚህም ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የምንገባበት ውድ ጊዜ ነው።

የሕይወታችን ታሪክ ሁለት ምት አለው አንድ ፣ ሊለካ የሚችል ፣ ከሰዓታት ፣ ከቀናት ፣ ከዓመታት የተሠራ ፣ ሌላኛው በእድገታችን ሂደት ወቅቶች ውስጥ የተዋቀረው ሲሆን -ልደት ፣ ልጅነት ፣ ጉርምስና ፣ ብስለት ፣ እርጅና ፣ ሞት ይመለከታል። እያንዳንዱ ወቅት ፣ እያንዳንዱ ምዕራፍ የራሱ የሆነ ዋጋ አለው ፣ እናም ከጌታ ጋር የመገናኘት ልዩ ጊዜ ሊሆን ይችላል። እምነት የእነዚህን ጊዜያት መንፈሳዊ ጠቀሜታ እንድናገኝ ይረዳናል-እያንዳንዳቸው አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ምላሽ የምንሰጥበትን የተወሰነ የጌታ ጥሪ ይገልጻሉ። በወንጌሉ ውስጥ ስምዖን ፣ እንድርያስ ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ምን እንደሰጡ እንመለከታለን - የጎለመሱ ወንዶች ነበሩ። በሥራቸው ዓሣ አጥማጆች የነበሩ ሲሆን የቤተሰባዊ ሕይወት ነበራቸው .... ሆኖም ፣ ኢየሱስ ሲያልፍ እና ሲጠራቸው ፣ “ወዲያው መረባቸውን ትተው ተከተሉት” (ማርቆስ 1፡18)።

ጌታ የሚያልፍበት እና እርሱን እንድንከተል የሚጠራን እንደ መዳን ጊዜ በእያንዳንዱ ደቂቃ እንድንኖር፣ እናም ከዓለም አስተሳሰብ ወደ ፍቅር እና አገልግሎት እንድንለወጥ ትረዳን ዘንድ የድንግል ማርያምን አማላጅነ ልንማጸን ይገባል።

24 January 2021, 16:16

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >