የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የይግባኝ ሰሚ ችሎት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገኛኑበት ወቅት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የይግባኝ ሰሚ ችሎት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገኛኑበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ችሎት አባላት የቤተሰብን መልካም እሴቶች እንዲያስቀጥሉ ጠየቁ!

ሮታ ሮማ በመደበኛነት የሮማ ሮታ ሐዋርያዊ ችሎት በመባል የሚታወቀው (በላቲን ቋንቋ: Tribunal Apostolicum Rotae Romanae) የቅድስት መንበር የሕግ ችሎቶችን የተመለከተ እና ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያዊ ችሎቶችን የሚያዳምጥ  የቅድስት መንበር ፍርድ ቤት ሲሆን የላቲን ስርዓተ አምልኮ እና የምስራቃዊያንን አብያተ ክርስቲያናት በተመለከተ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የይግባኝ ሰሚ ችሎት መሆኑ ይታወቃል። በተጨማሪም ይህ ችሎት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚሰጡት የፍርድ ሂደቶች ጋር በተያያዘ በቅድስት መንበር የተቋቋመ ከፍተኛ የቤተ-ክህነት ፍርድ ቤት ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህ ሮታ ሮማ በመባል የሚታወቀው የቅድስት መንበር ከፍተኛ የቤተ-ክህነት ፍርድ ቤት እ.አ.አ የ2021 ዓ.ም የሥራ አመት በጥር 20/2013 ዓ.ም  በይፋ በመጀመረበት ወቅት በቫቲካን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን የሮታ ሮማ ሐዋርያዊ ችሎት አባላት በቤተሰብ ውስጥ የሚገኙትን የተቀናጁ እሴቶችን እንዲከባከቡ ቅዱስነታቸው መጠየቃቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በጋብቻ ሥነ የምግባር ጉድለት ላይ በሚሰጡት ውሳኔ በቤተሰብ በተለይም በሕፃናት መካከል ያለውን መልካም ነገር እንዲያስቡ አሳስቧቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አርብ ዕለት የሮታ ሮማ ልዩ ፍርድ ቤት ባለሥልጣናት እ.አ.አ የ2021 ዓ.ም የሥራ አመት በይፋ በተከፈተበት ወቅት ቅዱስነታቸው ተገኝተው ንግግር ማደረጋቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ባለፈው ዓመት ለፍርድ ቤቱ ባለሥልጣናት ያስተላለፉትን መልእክት በድጋሚ በማስታወስ የክርስቲያን ጋብቻ ጭብጥ ማንሳታቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም የቤተሰብ መልካምነት ፣ በተለይም የልጆች መልካምነት በትዳር ውስጥ ከሚንጸባረቁ እርባናቢስ ሁኔታዎች ባሻገርም መታሰብ እንዳለበት አሳስበዋል።

የጋብቻ መሰረዝ ጉዳዮችን ይግባኝ የሚመለከተው ልዩ ፍርድ ቤቱ የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። እንዲሁም ከቀኖን ሕግ ጋር በተያያዙ ሌሎች የፍትህ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ይሠራል።

ቤተሰቡ: - በእግዚአብሔር ተመስሏል

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የፍ / ቤቱ ውሳኔዎች ጥሩ ክፍል የእምነት እጦትን እና በወንድና በሴት መካከል ካለው አንድነት በተጨማሪ የልጆችን መወለድና ማደግን የሚያካትት የትብብር ህብረት መሰረታዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ መሆኑን ቅዱስ አባታችን ገልጸዋል።

የሮታ ሮማ የሕግ ሥነ-ስርዓት ከጳጳሳዊ አስተምህሮዎች ጋር በሚስማማ መልኩ በትዳር ውስጥ የሚገኙትን ተቀዳሚ እሴቶች (የቤተሰቡ መልካም ነገር) ከትዳር ስረዛ አኳያ ሲታይ ከፍተኛ የሆነ መልካም ነገሮች በጋብቻ ውስጥ እንደ ሚገኝ ያብራሩት ቅዱስነታቸው የቤተሰቡ ሥነ-መለኮታዊ አምሳል በእግዚአብሔር እንደተመሰከረ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

“በእውነቱ” አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ “ጋብቻ ሁል ጊዜም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ የተባበረው ቃል ኪዳን የተባረከ ፍሬ ነው፤ በከንቱ አዋጅ በቶሎ ሊጠፋ አይችልም፣ ምክንያቱም አንድ ሰው ቢያንስ ለተፈጠረው ዘር የመለኮታዊ እቅድ ፍሬ ስለሆነ ቤተሰብ ሲፈርስ እንደ ጥሩ ነገር ተደረጎ ሊቆጠር አይችልም” ብለዋል።

የተሰረዙ ጋብቻዎች ውስጥ የሚገኙትን ልጆች እንክብካቤ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል በሕጋዊ መንገድ የተሰረዙ እና እንዲከስሙ በተደረጉ ጋብቻዎች ውስጥ የተፈጠሩ ሕፃናት ችግር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደ ሚገባቸው የገለጹ ሲሆን በተለይም በጋብቻ ውስጥ ከባለትዳሮቹ አንዱ ወገን የኑሮ መግለጫን ለመቀበል ፈቃደኛ በማይሆንበት ወቅት በእንደ እዚህ ዓይነት ትዳር ውስጥ ለተፈጠሩ ሕጻናት ጥንቃቄ ማደረግ እንደ ሚገባ አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.ኤ.አ. በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ለካቶሊክ የቤተሰብ ማኅበራት ፌዴሬሽን ያደረጉትን ንግግር በማስታወስ ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት መሆኑን በመግለፅ ሰዎች ለቋሚ እድገታቸው አስፈላጊ የሆነውን መልካም ነገር እንዲያገኙ ለማድረግ እጅግ በጣም ተገቢው መዋቅር ሆኖ እንደሚቀጥልም አሳስበዋል። ስለሰው ልጆች ሁለንተናዊ የሆነ መልካም ነገር ስንናገር ፣ ልጆች ባሉበት በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ይህ እንዴት ልንወጣ እንደሚችል እራሳችንን መጠየቅ አስፈላጊ ነው” በማለት አጥብቀው ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አንድ ትዳር መሰረዙ ከታወጀ በኋላ አንዳንድ ጊዜ ውስብስብ የሆነውን ምስጢራዊ አንድነት ምንነት የጠቆሙ ሲሆን ይህ ደግሞ ለትዳር ጓደኞቹ የሰላም ምንጭ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

ቅዱስነታቸው አክለውም “አንድ ሰው ለምሳሌም እናታቸው በአባታቸው የተተወች እና ብዙውን ጊዜ ሌላ የጋብቻ ትስስር ለመመሥረት ፈቃደኛ ያልሆነች እናት፣ እሁድ እለት ቅዱስ ቁርባን ስትቀበል ይህንን ጉዳይ ለልጆቻቸው ማስረዳት የሚቻለው እንዴት ነው? በማለት ጥያቄ ማንሳታቸው ተገልጿል።

ይህንን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያኒቱ በላቲን ቋንቋ አሞሪስ ላዬቲሲአ (የፍቅር ሐሴት) በተሰኘው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ውስጥ ጠቃሚ የሆነ ሐዋርያዊ መሣሪያ እንዳላት ጠቁመዋል ፣ ይህም ማንም ሰው በተለይም ልጆች ብቻቸውን መተው ወይም በወላጆች መካከል የጥላቻ መሣሪያ ተደርጎ መታየት እንደሌለባቸው ግልፅ ማሳያዎችን ይሰጣል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እ.አ.አ መጋቢት 19/2021 ዓ.ም “የፍቅር ሐሴት የቤተሰብ ዓመት” እንደ ሚጀምር ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን የሮታ ሮማ ሥራ ከቤተሰብ ጋር ለሚደረገው ለዚህ የቤተክርስቲያን ጉዞ ጠቃሚ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተስፋ እንደ ሚያደረጉ አክለው ገልጸዋል።

ለልዩ ፍርድ ቤቱ የተሰጠ ማሳሰቢያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለሮታ ሮማ ባለሥልጣናት ባደረጉት ንግግር አክለው እንደ ገለጹት የሰዎች አጠቃላይ በጎነት ውሳኔ ላይ በሚወስዱት አስከፊ ውጤቶች ፊት ንቁ ሆነን እንዳንቆጠር የሚጠይቅ በመሆኑ ይህንን የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ጭንቀት ከመመስከር እንዳይቆጠቡ አሳስበዋል።

ቤተክርስቲያኗ እናት መሆኗን በንግግራቸው ያስገነዘቡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እናም እንደ የፍርድ እንቅስቃሴ አስፈላጊ በሆነ አስፈላጊ ስፍራ ውስጥ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ያላቸው እራሳቸውን ለዚህ አስቸጋሪ ግን የሚቻል የእረኝነት ስራ አድማስ እንዲከፍቱ ጥሪ ቀርቧል - ለህፃናት እንዲያስቡ፣ የቤተሰብ መበተንን እዲቃወሙ፣ የፍቺ ወይም የአዲስ የሲቪል ጥምረት ያሉ ሁኔታዎች ውስጥ ተጎጂ የሚሆኑት ሕጻናት እንደ ሆኑ ቅዱስነታቸው አክለው ገለጸዋል። ይህ እናንተ የምትመሩት ሐዋርያዊ ችሎትም ሆነ ሌሎች የቤተክርስቲያኗ ፍ / ቤቶች “ተደራሽ ሊሆኑ የሚችሉ፣ ለዘብተኛ እና ሙሉ በሙሉ ነፃ” እንዲሆኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጠይቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም የሮታ ሮማ የጋብቻ ሥነ ምግባር ጉድለት እና የጋብቻ አንድነት ውሳኔዎች ውስጥ ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ የሆኑ ስሜቶችን መጠቀም እንደ ሚገባቸው የገለጹ ሲሆን የአንድ ቤተክርስቲያን ዳኛ ፍርዶች የሚነካው “ሁለቱን ጥንዶች ብቻ ሳይሆን በልጆችም ሕይወት ላይ ያተኮሩ ብርሃኖች እና ጥላዎችን ያቀፈውን ትውስታን ችላ ማለት አይገባችሁም” በማለት መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳችሁ መጸለይ እንድትቀጥሉ አደራ አላለሁኝ ብለዋል። ባለሥልጣኖቹ “የልጆችን መልካምነት ፣ ሰላም ወይም በተቃራኒው በመለያየት ፊት የደስታ እጦታቸውን” ማስታወስ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አክለውም “እያንዳንዱን ትኩረት እና እንክብካቤ ለቤተሰብ እና ለክርስቲያናዊ ጋብቻ ከመስጠት ልንታክት አይገባንም ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ከማጠናቀቃቸው እና ለፍርድ ቤቱ ሥራ ያላቸውን አድናቆት ከመግለጻቸው በፊት የሮታ ሮማ የበላይ ጠባቂ የሆኑት አቡነ ፒዮ ቪንቶ በቅርቡ የሰማኒያ ዓመት ልደታቸውን ሲያከብሩ የሥራ ኃላፊነታቸውን እንደ ሚለቁ ያስታወቁት ቅዱስነታቸው ለብዙ አመታት ለእዚህ ፍርድቤት ላበረከቱት አስተዋጾ ልዩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

29 January 2021, 19:17