ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ደስታ የክርስቲያኖች መገለጫ ነው አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ለማከብር ዝግጅት የሚደረግበት የስብከተ ጋና ወቅት በኅዳር 20/2013 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ስብከተ ገና ኢየሱስ በዓለም ታሪክ ውስጥ በመግባት የዓለምን የቀን አቆጣጠር ወደ ዓመተ ምሕረት እንደቀየረው ሁሉ የእኛንም ሕይወት በምሕረቱ ሊሞላት እና ልቀይራት እንደ ሚመጣ እና በእርሱ በኩል ሁሌም ዝግጁ መሆኑ የሚሰበክበት ወቅትና፣ እኛም ለእዚህ ጌታ ለምያደርግልን መንፈሳዊ ለውጥ የማምጣት ጥሪ በቃላት እና በተግባር በተደገፈ መልኩ ምላሽ የምንሰጥበት ወቅት ነው የስብከተ ገና ወቅት።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእዚህም መሰረት የእዚህ የስብከተ ገና 3ኛ ሣምንት በታኅሳስ 04/2013 ዓ.ም በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ ዕለት እንደ ሚያደርጉት በእለቱ ከዮሐንስ ወንጌል 1:6-8፣ 19-28 ላይ ተወስዶ በተነበበውና “ከእኔ በኋላ የሚመጣው፣ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ እርሱ ነው” በማለት መጥምቁ ዮሐንስ ራሱ ክርስቶስ እንዳልሆነ እንደተናገረ በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ደስታ የክርስቲያኖች መገለጫ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 04/2013 ዓ.ም 3ኛው የስብከተ ገና ሳምንት በተጀመረበት ወቅት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ለደስታ መጋበዝ የስብከተ ገና ወቅት ባሕርይ ነው -ያጋጠመን ተስፋ አስደሳች ነው ፣ በተወሰነ ደረጃ የምንወደውን ሰው ጉብኝት የመጠበቅ ያህል ነው፣ ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ ያላየነው አንድ ውድ የሆነ ጓደኛ እንደ መጠበቅ ያህል ነው። እናም ይህ የደስታ መጠን በተለይም ዛሬ ሦስተኛውን የስብከተ ገና እሁድ በምናከብርበት በአሁኑ ወቅት በተደረገው ስርዓተ አምልኮ ላይ በተነበበው ምንባብ ላይ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ማሳሰቢያ ተጀምሮ ነበር፣ እንዲህም ይላል “ሁል ጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ” (የመግቢያ ጸሎት ፊል 4፡4 ፣ 5) ምክንያቱ ምንድነው? “ጌታ ቅርብ ነው” (ፊል 4፡ 5)። ጌታ ለእኛ ቅርብ በሆነ መጠን የበለጠ ደስታ ይሰማናል፣ በጣም ሩቅ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ሀዘን ይሰማናል።

ዛሬ ከዮሐንስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበው ምንባብ ላይ ከእመቤታችን እና ከቅዱስ ዮሴፍ በስተቀር - የመሲሑን የመጠበቅ ተስፋ እና እሱ ሲመጣ የማየትን ደስታ የመጀመሪያ እና ሙሉ በሙሉ የተገነዘበውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባህሪ ያቀርባል- ይህም ማለት ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ያወራል ማለት ነው (ዮሐ 1: 6-8፣ 19-28)።

ወንጌላዊው ክብር በተሞላው መልኩ እንዲህ በማለት ያስተዋውቀዋል “ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ። ሰዎች ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ” (ዮሐንስ 1፡6-7)። መጥምቁ በቃሉ እና ሕይወቱን በስጦታ መልክ በማቅረብ የኢየሱስ የመጀመሪያ ምስክር ነበር። ሁሉም ወንጌላዊያን በነቢያት ቃል የገባው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ክርስቶስን በማመልከት ተልእኮውን እንደፈፀመ በማሳየት ይስማማሉ። መጥመቁ ዮሐንስ በዘመኑ መሪ ነበር። ዝናው ከይሁዳ ሁሉ አልፎ ወደ ገሊላ ተሰራጭቷል። እርሱ ግን ወደራሱ ትኩረት ለመሳብ በማሰብ ለቅጽበት እንኳን ፈተና ውስጥ አልገባም፣ እርሱ ሁል ጊዜ ወደ ሚመጣው ወደ እርሱ ያዘነብላል፣ እርሱ እንዲህ ይል ነበር-“ ከእኔ በኋላ የሚመጣው፣ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ እርሱ ነው” (ዮሐንስ 1፡27) ፡፡

ይህ የመጀመሪያው የክርስቲያናዊ ደስታ ሁኔታ ነው -ራስን ሳይሆን ኢየሱስን ማዕከል ማደረግ አስፈላጊ ነው። ይህ ራስን ማግለል ማለት አይደለም፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ውጤታማ ማዕከል ስለሆነ፣ ወደዚህ ዓለም ለሚመጡት ወንድና ሴት ሕይወት ሁሉ ትርጉም የሚሰጠው እርሱ እርሱ ብርሃን ነው። ይህ ተመሳሳይ የፍቅር ተለዋዋጭነት ነው ፣ ይህም እራሴን ላለማጣት ግን እራሴን እንደገና ለማግኘት ፣ ከራሴ እንድወጣ የሚያደርገኝ ፣ እራሴን ስሰጥ ፣ የሌሎችን በጎ ነገር እሻለሁ ማለት ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ መምጣት ለመመሥከር ረጅም ጉዞ አደረገ። የደስታ ጉዞ በፓርክ ውስጥ በእግር መጓዝ ማለት አይደለም። እሱ ሁሉንም ነገር ትቶ ፣ በወጣትነቱ ፣ እግዚአብሔርን በማስቀደም ፣ ቃሉን በሙሉ ልቡና በሙሉ ኃይሉ ለማዳመጥ እግዚአብሔርን ያስቀደማል። የመንፈስ ቅዱስን ነፋስ ለመከተል የበለጠ ነፃ ለመሆን ከብዙ ነገሮች ሁሉ ራሱን ለመቆጠብ ወደ በረሃ ሄደ። በርግጥ አንዳንድ የእሱ የባህርይ መገለጫዎች ልዩ ናቸው፣ ሁሉንም ለመመምከር ሊጠቅም አይችሉ ይሆናል። ነገር ግን የእርሱ ምስክር የሕይወቱን ትርጉም ለመፈለግ እና እውነተኛ ደስታን ለማግኘት ለሚፈልግ ሁሉ ምሳሌያዊ ነው። በተለይም አጥማቂው ዮሐንስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ክርስቶስን ለሌሎች ለማወጅ ለተጠሩ ሰዎች ምሳሌ ነው - ይህን ማድረግ የሚችሉት ራሳቸውን እና ዓለማዊነትን በማግለል ብቻ ሰዎችን ወደራሳቸው በመሳብ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ በማቅናት ጭምር ነው።

አሁን የአግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብርሄል ጸሎት በምንጸልይበት ወቅት ይህ ሁሉ በድንግል ማርያም ውስጥ ሙሉ በሙሉ መተግበሩን እናያለን፣ እርሷ የእግዚአብሔርን የማዳን ቃል በዝምታ ትጠባበቃላች። እሷም ተቀበለችው፣ እሷም አዳመጠች፣ ፀነሰች። በእሷ ውስጥ እግዚአብሔር ቅርብ ሆነ። ለዚህም ነው ቤተክርስቲያን ማሪያምን “የደስታችን መንስኤ” በማለት የምትጠራው።

13 December 2020, 13:49

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >