ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የስብከተ ገና ወቅት መንፈሳዊ ለውጥ የምናመጣበት ወቅት ሊሆን ይገባል አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ለማከብር ዝግጅት የሚደረግበት የስብከተ ጋና ወቅት በኅዳር 20/2013 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ስብከተ ገና ኢየሱስ በዓለም ታሪክ ውስጥ በመግባት የዓለምን የቀን አቆጣጠር ወደ ዓመተ ምሕረት እንደቀየረው ሁሉ የእኛንም ሕይወት በምሕረቱ ሊሞላት እና ልቀይራት እንደ ሚመጣ እና በእርሱ በኩል ሁሌም ዝግጁ መሆኑ የሚሰበክበት ወቅትና፣ እኛም ለእዚህ ጌታ ለምያደርግልን መንፈሳዊ ለውጥ የማምጣት ጥሪ በቃላት እና በተግባር በተደገፈ መልኩ ምላሽ የምንሰጥበት ወቅት ነው የስብከተ ገና ወቅት።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእዚህም መሰረት የእዚህ የስብከተ ገና 2ኛ ሣምንት በኅዳር 27/2013 ዓ.ም በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ ዕለት እንደ ሚያደርጉት በእለቱ  ከማርቆስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበውና “እነሆ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ድምፅ’።” ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ። የይሁዳ አገር በሞላ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎች በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቁ” (ማርቆስ 1፡1-8) በሚለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን የስብከተ ገና ወቅት መንፈሳዊ ለውጥ የምናመጣበት ወቅት ሊሆን ይገባል ማለታቸው ተገልጿል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 27/2013 ዓ.ም ሁለተኛው የስብከተ ገና ሳምንት በተጀመረበት ወቅት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዚህ እሁድ ቅዱስ ወንጌል ምንባብ (ማርቆስ 1፡1-8) የመጥምቁ ዮሐንስን ግለሰባዊ ማንነት እና ሥራ ያስተዋውቀናል። እሱ የስብከተ ገና ወቅት ለእኛ ከሚያቀርበው ጋር ተመሳሳይነት ያለው የእምነት የጉዞ መስመር ለእርሱ በዘመኑ ለነበሩ ሰዎች ይገልጻል - በገና ጌታን ለመቀበል ራሳችንን እንድናዘጋጅ ይመክረናል። ይህ የእምነት መንገድ ጉዞ የመቀየሪያ መንገድ ነው። ‘መለወጥ’ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ከሁሉም በፊት እና ከሁሉም በላይ አቅጣጫ እና ባሕሪይ መለወጥ ማለት ነው፣ እናም እንዲሁም የአንድን ሰው አስተሳሰብ መቀየር ማለት ነው። በሥነ ምግባር እና በመንፈሳዊ ሕይወት መለወጥ ማለት ራስን ከክፉ ወደ መልካም ፣ ከኃጢአት ወደ እግዚአብሔር ፍቅር መለወጥ ማለት ነው። እናም መጥምቁ በይሁዳ ምድረ በዳ ውስጥ “በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ” (ማርቆስ 1፡4)። ጥምቀትን መቀበል የእርሱን ስብከት አዳምጠው ንስሐ ለመግባት የወሰኑ ሰዎች የመለወጫቸው ውጫዊና የሚታይ ምልክት ነበር። ያ ጥምቀት በዮርዳኖስ ወንዝ በውኃ ውስጥ ከመጥለቅ ጋር የተከናወነ ቢሆንም ዋጋ ቢስ ሆኖ ተገኝቷል፣ እሱ አንድ ምልክት ብቻ ነበር እናም ለንስሃ እና ህይወትን ለመለወጥ ፈቃደኝነት ከሌለ ዋጋ የለውም ነበር።

መንፈሳዊ ለውጥ ለማምጣት በቅድሚያ በፈጸምነው ኃጢአቶች ማዘን፣ ከእነሱ ነፃ የመሆን ፍላጎት እና ለዘላለም ኃጢአትን ከሕይወታችን ውስጥ አስወጥተን የመኖር ዓላማን ያካተተ መሆን ይኖርበታል። ኃጢአትን ለማስቀረት ደግሞ ከኃጢአት ጋር የተዛመዱትን ነገሮች ማስወገድ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ከኃጢአት ጋር የተዛመዱና የውድቀታችን ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች - ዓለማዊ አስተሳሰብ ፣ ከመጠን በላይ የሆነ ምቾትን መመኘት፣ ለመዝናናት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ማሳደር፣ ሐብት ለማጋበስ እና ጥሩ ኑሮ ለመኖር ከፍተኛ ጉጉት መፍጠር እነዚህ ሁሉ ከኃጢአት ጋር የተዘመዱ ነገሮች ናቸው። ይህንን የሚያሳየው ምሳሌ በዛሬው እለት በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በመጥምቁ አማካይነት እንደገና ወደ እኛ መጥቶልናል ፤ ከመጠን በላይ የሆነ ምቾትን የማይመኝ ነገር ግን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ የሚመኝ ሰው መሆን ማለት ነው። ይህ የመለወጥ የመጀመሪያ ደረጃ ነው -ከኃጢአት እና ዓለማዊነት መራቅ-ከእነዚህ ነገሮች የመነጠል ጉዞን መጀመር የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ሌላኛው የመንፈሳዊ ለውጥ ማምጫ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ እግዚአብሔርን እና የእርሱን መንግሥት መፈለግ ነው። ከዓለማዊ ነገሮች መገለል እና እግዚአብሔርን እና መንግስቱን መፈለግ። ዓለማዊ የሆኑ ምቾቶችን መተው እና ዓለማዊ አስተሳሰብን ማስወገድ በራሱ ግብ አይደለም፣ ንስሐ መግባቱ ብቻ በራሱ በቂ አይደለም፣ አንድ ክርስቲያን “ሚስኪን” ሰው መሆን የለበትም። ነገሩ ሌላ ነው። ከዓለማዊ ነገሮች ራስን መነጠል በራሱ ግብ አይደለም፣ ነገር ግን ከእዚያ ባሻገር እጅግ የላቁ ነገሮችን ማለትም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማግኘት ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለመፍጠር ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነት ለማጠናከር በንቃት መስራት ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ቀላል አይደለም፣ ምክንያቱም ከኃጢአት ጋር በቅርበት የሚያስተሳስሩን ብዙ ነገሮች አሉ ፤ ቀላል አይደለም .... ፈተና ሁል ጊዜ ወደ ታች ይጎትተናል፣ ጨምድዶ ይይዘናል፣ ወደ ኃጢአት እንድንጠጋ የሚያደርገንን ትስስር ይፈጥርልናል - አለመተማመን ፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ ክፋት ፣ ጤናማ ያልሆኑ አካባቢዎችን ማዘውተር ፣ መጥፎ ምሳሌዎችን መከተል። አንዳንድ ጊዜ ለጌታ ያለን ፍላጋጎት በጣም ደካማ ነው፣ እናም እግዚአብሔር ዝም ያለ ይመስላል። የመጽናናት ተስፋዎቹ ለእኛ እንደ ሩቅ እንደ ሆኑ በዛሬው የመጀመርያም ምንባብ ላይ እንደ ተገለጸው “አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል አምላካችሁ” (ኢሳያስ 40:1) በማለት ኢሳያስ በትንቢቱ አንደ ገለጸው እግዚአብሔር ለእኛ አሳቢ እና እውነተኛ እረኛ እንዳልሆነ ሁኖ ይሰማናል፣ ወይም ይታየናል። እናም በእዚህ የተነሳ አንድ ሰው በእውነት መንፈሳዊ መለወጥ ማምጣት አይቻልም ብሎ በማሰብ ፈተና ውስጥ ይወድቃል። ይህንን የመሰለ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ምን ያህል ጊዜ ተሰምቶናል! “አይ ፣ እኔ ማድረግ አልችልም። በጭንቅ እጀምራለሁ ከዚያም ወደ ኋላ እመለሳለሁ” በማለት ማሰብ እንጀምራለን። እናም ይሄ መጥፎ የሆነ ነገር ነው። ነገር ግን ይቻላል፣ በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል። የእዚህ ዓይነት ተስፋ አስቆራጭ ሐሳብ በሚያጋጥማችሁ ወቅት በእዚህ ሐሳብ ውስጥ ገብታችሁ እየቆዘማችሁ አትኑሩ፣ ምክንያቱም ወድቀታችንን የሚያቀላጥፍ ነገር ስለሆነ ነው። አንድ ሰው ወደ ፊት መሄድ ቢፈልግም ነገር ግን እሱ ወይም እሷ ማድረግ እንደማትችል ወደ ፊት መጓዝ እንደ ማትችል ሆኖ በሚሰማው ወቅት በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በመጀመሪያ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት በራሱ ፀጋ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፣ ማንም ሰው በራሱ ኃይል ወይም በራሷ ኃይል መለወጥ አይችሉም። ጌታ ለእኛ የሚሰጠን ጸጋ ነው፣ ስለሆነም እግዚአብሔር ይህንን ጸጋ እንዲሰጠን አጥብቀን ልንጠይቀው ይገባል። ወደ እግዚአብሔር ውበት ፣ ቸርነት ፣ ርህራሄ እራሳችንን በምንከፍትበት ደረጃ እኛን እንዲቀይረን እግዚአብሔርን በትህትና መጠየቅ ይኖርብናል። ስለ እግዚአብሔር ርህራሄ አስቡ። እግዚአብሔር መጥፎ አባት ፣ ደግነት የጎደለው አባት አይደለም ፣ በፍጹም እንድህ አይደለም። የመጨረሻውን የመንጋውን አባል እንደሚፈልግ እንደ ጥሩ እረኛ እርሱ በጣም ይወደናል። ፍቅር ነው ይህ ደግሞ መለወጥ ነው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። መራመድ ትጀምራለህ ፣ እንድትሄድ የሚገፋፋው እሱ ስለሆነ ፣ እንዴት እንደሚመጣም ታያለህ። ጸልዩ፣ ተራመዱ ሁልጊዜ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ለመንቀሳቀስ ሞክሩ፣ ለውጡን ታያላችሁና።

ከነገ ወዲያ (እ.አ.አ የቀን አቆጣጠር በታሕሳስ 08/2020 ዓ.ም ማለታቸው ነው) አመታዊ በዓሏን የምናከብረው እና ያለ አዳም አጢአት የተጸነሰች እጅግ ንጽሕት የሆነቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እራሳችንን ለእግዚአብሄር ፣ ለቃሉ ፣ ለሚለውጠው እና ለሚያድነው ለእርሱ ፍቅር ራሳችንን ለእርሱ ለመክፈት ከኃጢአትና ከዓለማዊነት የበለጠ ለመለየት ትረዳን ዘንድ አማላጅነቷን መማጸን ይኖርብናል።

06 December 2020, 11:50

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >