ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የፍቅር ሕይወት በመጨረሻው ቀን ከጌታ ጋር ለመገናኘት ያዘጋጀናል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ በሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በጥምት 29/2013 ዓ.ም ያደረጉት  የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ከማቴዎስ ወንጌል 25፡1-13 ተወስዶ በተነበበውና “በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማይ መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ልጃገረዶችን ትመስላለች። ከእነርሱም አምስቱ ልጃገረዶች ዝንጉዎች፣ አምስቱ ደግሞ አስተዋዮች ነበሩ” በሚለው የዐሥሩ ልጃገረዶች ምሳሌ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አስተንትኖ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “የፍቅር ሕይወት በመጨረሻ ቀን ከጌታ ጋር ለመገናኘት ያዘጋጀናል” ማለታቸው ተገልጿል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የተወዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

የሁሉም ቅዱሳን በዓል እና ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ወገኖቻችንን የምናስብበት የሙታን ቀን መታሰቢያ በዓል ምክንያት የጀመርነውን የዘላለም ሕይወት ነፀብራቅ በመቀጠል የዚህ እሑድ የወንጌል ምንባብ (ማቴ 25 1-13) ላይ ማሰላሰል እንጀምራለን። ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያት መንግሥት ምልክት የሆነውን ለሠርግ ግብዣ የተጋበዙትን የአሥሩን ደናግል ምሳሌ ይናገራል።

በኢየሱስ ዘመን ሰርግ በሌሊት መከበሩ የተለመደ ነበር፣ ስለሆነም ይህ ስነ-ስረዓት የሚከናወነው በጨለማ ማብራት የሚችሉ መብራቶችን በመያዝ ነበር። አንዳንድ የሙሽራው አጃቢ የነበሩ ሴቶች ሞኞች ነበሩ፣ ምክንያቱም መብራት ይዘው መጠባበቂያ ዘይት አልያዙም ነበር። ነገር ግን ብልጦቹ የመጠባበቂያ ዘይት ከመብራቶቻቸው ጋር አብረው ይዘው ተጉዘው ነበር። ሙሽራው ዘግይቷል ፣ ዘግይቶ ነበር የመጣው፣ እናም ሁሉም አንቀላፍተው ነበር። እኩለ ሌሊት ላይ ‘ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!’ የሚል ጥሪ በተሰማ ጊዜ  ሞኞቹ በዚያን ጊዜ ለመብራቶቻቸው ዘይት እንደሌላቸው ይገነዘባሉ፣ ጥበበኞችን ልጃገረዶች ጥቂት ዘይት እንዲሰጧቸው ይጠይቃሉ፣ ጥበበኞቹ ልጃገረዶችም ግን ለእኛ እና ለእናንተ ለሁላችን የሚበቃ ዘይት ስለሌለ ሂዳቹ ግዙ በማለት ይመልሱላቸዋል።  በእዚያን ወቅት ሞኞቹ ልጃገረዶች ዘይት ለመግዛት በሄዱበት ወቅት ሙሽራው መጣ። ጥበበኞቹ ልጃገረዶች ከእርሱ ከሙሽራው ጋር ወደ ግብዣው አዳራሽ ሲገቡ በሩ ተዘጋ። ሌሎቹ በጣም ዘግይተው ስለመጡ በሩ በመዘጋቱ የተነሳ ወደ ኋላ ለመመለስ ተገደዱ።

በዚህ ምሳሌ ኢየሱስ ለዳግም ለምጽአቱ ዝግጁ መሆን እንዳለብን ሊነግረን እንደ ፈለገ ግልጽ ነው። ለዳግም ምጽአቱ ብቻ ሳይሆን ለትልቅ እና ለትንሽም የዕለት ተዕለት ገጠመኞች የእምነት መብራት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ለዚያ ግንኙነት የሚሆን የበጎ አድራጎት እና መልካም ስራዎች እንደ ሚያስፈልጉ ለመግለጽ ፈልጎ የተጠቀመው ምሳሌ ነው። ሐዋርያው ​​ጳውሎስ እንደተናገረው በእውነት ከኢየሱስ ጋር አንድ የሚያደርገን እምነት “በፍቅር የሚገለጽ እምነት” ነው (ገላ 5፡6) በማለት አሳስቦናል። በጥበበኞቹ ልጃገረዶች ባሕርይ የተመሰለው እሱ ነው። ጥበበኛ እና አስተዋይ መሆን ማለት ከእግዚአብሄር ፀጋ ጋር ለመመሳሰል እስከ መጨረሻው ሰዓት መጠበቅ ማለት አይደለም ፣ ነገር ግን ከአሁኑ በመጀመር በንቃት እና በብርታት ወዲያሁኑ ማድረግ መጀመር ማለት ነው። “እኔ… አዎ ፣ በቅርቡ እለወጣለሁ”…ማለት ተገቢ አይደለም።  “ዛሬውኑ ተለወጥ! ዛሬ ሕይወትዎን ይለውጡ! ” “አዎ ፣ አዎ ፣ ነገ እለወጣለሁ አትበሉ፣ ዛሬውኑ ተለወጡ። ነገር እለወጣለሁ የምንል ከሆነ ነገ ተመሳሳይ ነገር ይባላል ፣ እናም በጭራሽ ልውጥ ልናመጣ አንችልም። ዛሬ ተለወጡ! ከጌታ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ለመገናኘት ዝግጁ ከሆንን ፣ አሁን ከእሱ ጋር መተባበር እና በፍቅሩ የተነሳሱ መልካም ተግባሮችን ማከናወን አለብን።

እኛ ይህ አንድ ቀን እንደሚከሰት እናውቃለን ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ፣ የሕይወታችንን ዓላማ ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ትክክለኛ ቀጠሮ እንረሳለን፣ ስለሆነም የመጠበቅ ስሜትን በማጣት የአሁኑን ፍፁም ለማድረግ እንመኛለን። አንድ ሰው አሁናዊ የሆኑ ክስተቶችን ፍፁም ሲያደርግ እሱ ወይም እሷ የአሁኑን ብቻ ይመለከታሉ ፣ በጣም ጥሩ እና በጣም አስፈላጊ የሆነውን የመጠበቅ ስሜት በማጣት እንዲሁም ከአሁናዊ ሁኔታዎች ጋር የሚቃረኑ ተግባሮችን እንፈጽማለን። ይህ አስተሳሰብ - አንድ ሰው የመጠባበቅ ስሜት ሲያጣ ስለ መጪው ዓለም ማንኛውንም ነገር ለመመልከት ይታክታል፣ እኛ ሰዎች ከእዚህ ሕይወት ወደ ሌላ ሕይወት እንደምንሻገር በመዘንጋት በዚሁ መልኩ እንኖራለን፣ የፈለግነውን ነገር ሁሉ ለማከናውን እንፈልጋለን። እናም ስለዚህ ሰዎች የሚጨነቁት ስለ መውረስ ፣ ስለ መጓዝ ፣ እራሳቸውን ስለማቋቋም ብቻ እና የበለጠ እና ብዙ ነገር ስለማግኘት ብቻ ይሆናል ማለት ነው። እኛ ለእኛ በጣም በሚስቡን እና ለእኛ መልካም በሚመስለን ፣ በምንወደው ፣ በፍላጎታችን ሕይወታችን እንዲመራ ከፈቀድን ህይወታችን ከንቱ ይሆናል ወይም መካን ይሆናል፣ መብራታችን እንዳይጠፋ የሚረዳን ተጠባባቂ ዘይት አላከማቸንም ማለት ነው፣ እናም ጌታ ከመምጣቱ በፊት መብራታችን ይጠፋል ማለት ነው። እኛ ዛሬ መኖር አለብን ፣ ነገር ግን ወደ ነገ የሚወስደን ዛሬን መኖር ይኖርባንል፣ ወደዚያ መምጣት የሚያስችለን፣ ወደ ፊት መንቀሳቀስ የሚያስችለን በተስፋ የተሞላ የአሁኑን ጊዜ መኖር አለብን። በሌላ በኩል ነቅተን የምንጠብቅና መልካም በማድረግ ከእግዚአብሄር ፀጋ ጋር የምንመሳሰል ከሆነ የሙሽራውን መምጣት በደስታ መጠበቅ እንችላለን። ጌታ በምንተኛበት ጊዜ እንኳን መምጣት ይችላል። ይህ አያስጨንቀንም ፣ ምክንያቱም በየእለቱ በመልካም ስራዎቻችን የተከማቸ የዘይት ክምችት አለን ፣ ጌታን በጠባበቅ የተሞላ በተስፋ የታጀበ ሕይወት ስለኖርን ነው፣ በተቻለ ፍጥነት እንዲመጣ እና እርሱ ከእርሱ ራሱ ጋር እኛን ሊወስድ እንደ ሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን።

እንደ እርሷ ንቁ የሆነ እምነት እንድንኖር ይረዳን ዘንድ የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት እንማጸናለን፣ ከሞት ባሻገር ተሻግረን ወደ ታላቁ የሕይወት ብርሃን በዓል የምንደርስበት የሚያበራ መብራት  ሁነን እንኖር ዘንድ እርሷ በአማላጅነቷ ሁላችንንም ትርዳን።

08 November 2020, 11:56