ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢየሱስ ማመን ለበጎ አድራጎት ሥራ ሙሉ ትርጉም ይሰጣል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 17/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት አስተንትኖ (በማቴዎስ ወንጌል 16፡13-20)  ላይ በተጠቀሰው  ኢየሱስ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት መለሰ።ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ብፁዕ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አይደለም። አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም። የመንግሥተ ሰማይን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርኸው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የፈታኸው ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “በኢየሱስ ማመን ለበጎ አድራጎት ሥራ ሙሉ ትርጉም ይሰጣል” ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው እለተ ሰንበት ቅዱስ ወንጌል ምንባብ  (ማቴ. 16፡13 - 20 ይመልከቱ) ጴጥሮስ  በኢየሱስ ያለውን እምነት በመግለጽ የእግዚአብሔር ልጅ እና መሲህ መሆኑን ያረጋግጣል። የደቀመዛሙርቱ ምስክርነት ከእርሱ ጋር ባላቸው ግንኙነት ወሳኝ የሆነውን እርምጃ እንዲወስዱ በሚመኘው በኢየሱስ ራሱ አነሳሽነት የቀረበ ጥይቄ ነው። በእርግጥም ኢየሱስ እሱን ከሚከተሉት ጋር በተለይም በአስራ ሁለቱ ጋር የሚያደረገው ጉዞ ሙሉ በሙሉ እምነታቸው እንዲያድግ ለማደረግ ከማስተማር ጋር የተያያዘ ነው። በመጀመሪያ “ሰዎች የሰው ልጅ ማን ይሉታል?” (ማቴ 16፡13) በማለት ይጠይቁታል። እኛ ሁላችንም እንደምናደርገው ሐዋርያት ስለ ሰዎች ማውራት ይወዳሉ። ሐሜት ማውራት እንወዳለን። ስለ ሌሎች መናገር በጣም የሚያስደስት አይደለም፣ ነገር ግን ይህንን ማድረግ እንወዳለን፣ አልፎም ተርፎም በሌሎች ላይ እናሽሟጥጣለን። በዚህ ረገድ ከሐሜት ይልቅ የእምነት እይታ ቀድሞውኑ ተፈልጓል ፣ እናም እሱ  “ህዝቡ እኔ ምን ይለኛል?” በማለት ይጠይቃል። ደቀመዛምርቱም የተለያዩ አስተያየቶችን ለመስጠት በሚመስል መልኩ የመፎካከር መንፈስ በሚመስል ሁኔታ፣ ምናልባትም በጣም ብዙ ነገሮችን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አውርተው ሊሆን ይችላል መልስ ለመስጠት ይጣደፋሉ። እነሱ ራሳቸው ስለሱ ተናግረዋል። እነርሱ ከሌሎች ጋር ሐሳቡን ተጋርተዋል። በመሠረቱ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነቢይ ተደርጎ ይቆጠር ነበር።

በሁለተኛው ጥያቄ ኢየሱስ በጥልቀት ይናገራቸዋል፣ እንዲህም ይላቸውል “እናንተስ? … እኔን ማን ትላላችሁ? ” (ማቴ 16፡15) በማለት ይጠይቃቸኋል። በዚህ ወቅት እያንዳንዳችን እኛ ኢየሱስን ለመከተል የተጠራን ሰዎች በሙሉ በዝምታ በማዳመጥ ኢየሱስን ልንክተል የተጠራንበት ምክንያት ምን እንደ ሆነ በማሰብ በጥርጣሬ ከልክ በላይ የሆነ ጥርጣሬ ውስጥ እንገባለን። አሁን “ለአንተ ኢየሱስ ማን ነው?” ብዬ ብጠይቅ እንኳ ትንሽ ጥርጣሬ ሊኖር ይችላል። ስምዖን በግልጽ “ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ አንተ ነህ” በማለት በመናገር ሁሉንም ግልጽ አወጣ (ማቴ 16፡16)። ይህ መልስ የተሟላ እና በእውቀት ብርሃን የበራ ከራሱ ፍላጎት የመጣ አይደለም ፣ ምንም እንኳን ጴጥሮስ ለጋስ የነበረ ሰው ቢሆንም ቅሉ፣ በእርግጥ ጴጥሮስ ለጋስ ሰው ነበር- ነገር ግን የሰማያዊው አባት ጸጋ ልዩ ፍሬ ነው። በእርግጥ ኢየሱስ ራሱ “ይህ በስጋ እና በደም አልተገለጠልህም” - ይህ ማለት በባህል ውስጥ ካጠናኸው ነገር ተነስቶ የተገለጠልህ ነገር አይደለም ለማለት ፈልጎ ነው። ነገር ግን “በሰማያት ውስጥ ያለው በአባቴ” (ማቴ 16፡17) ነው የገለጸልህ በማለት ይናገራል። ኢየሱስን መመስከር ከአብ የሚሰጥ ጸጋ ነው። ኢየሱስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው ፣ ቤዛ ነው ፣ እኛም ፣ “አባት ሆይ ኢየሱስን የማመን ጸጋ ስጠኝ” ብለን ልንጠይቀው የሚገባን ጸጋ ነው። በተመሳሳይ መልኩም ​​ጌታ ለስምሪት ተነሳሽነት በማሳየት ስምዖን በሰጠው ፈጣን ምላሽ በመቀበል በታላቅ ድምቀት “አንተ ጴጥሮስ ነህ ፣ እኔም በዚህ ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፣ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም (ማቴ 16፡18) በማለት ይመልስለታል። በዚህ ማረጋገጫ ኢየሱስ ለእርሱ ለስምዖን “ጴጥሮስ” ብሎ የሰጠውን አዲስ ስም ትርጉሙን እንዲያውቅ ያደርገዋል ፣ አሁን ያሳየው እምነት የእግዚአብሔር ልጅ ቤተክርስቲያኑን ለመገንባት ማለትም ማሕበረሰቡን ለመመስረት የሚያስፈልገውን ዓይነት የማይናወጥ “ዐለት” መሆኑን እንዲገነዘብ ያደርገዋል። እናም ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ በጴጥሮስ እምነት መሠረት ትጓዛለች፣ ይህም ማለት ጴጥሮስ ለኢየሱስ እውቅና በሰጠው እና የቤተክርስቲያኒቱ ራስ አደረገው በሚለው እምነት ቤተክርስቲያን ትመራለች፡፡

ዛሬ ኢየሱስ ለእኛ “እናንተ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” የሚለውን ጥያቄ ለእያንዳንዳችን ይቀርብልናል።  ለእያንዳንዳችን። እናም እያንዳንዳችን ነገረ መለኮታዊ የሆነ መልስ መስጠት የለብንም ፣ መልሳችን ሊሆን የሚገባ እምነትን ባካተተ ሕይወት ነው። “ለእኔ አንተ …” እናም ከዚያ በኋላ ኢየሱስን መመስከር።  እኛ እንደ መጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት በውስጣችን የአብን ድምፅ እና በጴጥሮስ ዙሪያ ከተሰበሰበችው ቤተክርስቲያን ጋር መስማማት የሚጠይቅ መልስ መስጠት ይኖርብናል። ክርስቶስ ለእኛ ማን እንደ ሆነ የመረዳት ጉዳይ ነው፤ እርሱ የሕይወታችን ማዕከል ከሆነ ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የገባንበት ዋነኛው ግብ እርሱ ከሆነ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለን ቁርጠኝነት ምን እንደ ሆነ የመረዳት ጉዳይ ነው። ለእኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ማን ነው ፣ ለእርስዎስ ማነው…? በየቀኑ መስጠት ያለብን መልስ ነው።

ነገር ግን ማሰታውል አለብን፣ ለሕብረተሰባችን የምናደርገው ሐዋርያዊ እንክብካቤ በየቦታው ላሉት ብዙ የድህነት እና ቀውስ ዓይነቶች ክፍት መሆናቸው አስፈላጊ እና የሚያስመሰግን መሆኑን መረዳት ይኖርብናል። ልግስና ሁል ጊዜም የእምነት ጎዳና ፣ የእምነት ፍፁም ጎዳና ነው። ነገር ግን የምናከናውናቸው የበጎ ሥራ አገልግሎቶች አስፈላጊ እና ሊከናወኑ የሚገባቸው ቢሆንም ከጌታ ኢየሱስ ጋር እንዳንገናኝ እኛን ሊያግዱን ግን አይገባም።  የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ቀላል የሆነ የበጎ አድራጎት ተግባር አይደለም ነገር ግን በአንድ ወገን ሌሎችን በክርስቶስ ዓይን ይመለከታል፣ በድሆች ፊት ላይ ኢየሱስን ይመለከታል። ይህ እውነተኛው የክርስቲያን በጎ አድራጎት መንገድ ነው ፣ በማዕከሉ ውስጥ ሁልጊዜም ቢሆን ኢየሱስ አለ። በማመኗ የተነሳ ብጽዕት የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በክርስቶስ የእምነት ጎዳና ላይ መራመድ እንችል ዘንድ መሪያችን እና አርአያችን ትሁን ፣ እናም በእርሱ ላይ ያለን መታመን ለበጎ አድራጎት ተግባር እና ለህይወታችን ሙሉ ትርጉም እንደሚሰጥ እንድንገነዘብ እርሷ በአማልጅነቷ ትርዳን።

23 August 2020, 16:21