ስደተኛ የቀን ሥራ ፈላጊዎች በሕንድ የባቡር ጣቢያ ስደተኛ የቀን ሥራ ፈላጊዎች በሕንድ የባቡር ጣቢያ  

ቫቲካን ለስደተኞች የምታደርገው አዎንታዊ አስተዋጾ ይፋ ሆነ

በቫቲካን ስር የሚተዳደረው እና የስደተኞችን ጉዳይ የሚመለከተው ተቋም ይፋ ባደርገው መረጃ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስደተኞች እያደርገች የሚትገኘውን እንክብካቤ አዎንታዊ አስተዋጾ በሪፖርቱ ያፋ ያደረገ ሲሆን በተለይም ደግም በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከሰተ በሚገኘው በኮሮና ቫይረስ በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ስደተኞች ላይ ወረርሽኙ ከፍተኛ የሆነ አደጋ እንዳያስከትል ቤተክርስቲያኗ የበኩሉዋን አስተዋጾ በማደረግ ላይ እንደ ምትገኝ ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ተፈናቃዮች እና የሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ የሆኑ ሰዎች በሕብረተሰባችን ውስጥ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን ሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን በተለያዩ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በዚህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይበልጡኑ ተጋላጭነታቸው እየጨመረ መምጣቱን ተቋሙ ይፋ ያደረገ ሲሆን  ደህንነታቸውን እና ጤናቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ለበርካታ የፍትህ መጓደሎች እና መድልዎች እጅግ ተግላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

ለዚህም ነው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን እና ማህበረሰቦችን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ሰጥታ የምትከታተለው በማለት ሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን የተለያዩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግብረ ሰናይ ተቋማት ይህንን ችግር ለመቀረፍ በትጋት እየሰሩ እንደ ሚገኙ ተገልጿል። 

የካቶሊክ ርዳታ መስጫ ተቋም (CRS)፣ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ የስደተኞች ኮሚሽን (ICMC)  እና ካሪታስ የእርዳታ መስጫ ተቋም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ስደተኞች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደ ሚገኙ ተገልጿል። በዮርዳኖስ የሚገኙ ስደተኞች ሁኔታ እጅግ በጣም አስጊ እና አስፈሪ በመሆኑ የተነሳ ቀይ መስመር ሳያልፍ በፊት ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደ ሆነ ሪፖርቱ ያፋ ያደረገ ሲሆን በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ውስጥ የሚገኙት የካሪታስ ድርጅቶች ምግብ ፣ የቤት እቃዎችን እና አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን እያቀረቡ እንደ ሚገኙ ተገልጿል። በተለይም በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ እና በአካባቢው በሚገኙ አገራት በግጭት ምክንያት በተፈጠረው የሰብአዊ ቀውስ ሳቢያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አገራቸውን ለቀው ለስደት መዳረጋቸው ተገልጿል።

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው አመታዊ ሪፖርት “የታገዱ ህይወቶች” በሚል አርዕስት ስደተኞችን በተመለከተ ባወጣው ዘገባ እንደ ገለጸው በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የስደተኞችን እለታዊ እንቅስቃሴ እና የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያግድ ወይም የሚያዘገይ፣ እንዲሁም በዕለት ተዕለት ኑሮ ምክንያት  እየተናወጡ ስለሚገኙ ሰዎች እየደረሰባቸው ስላለው አለመረጋጋት በተመለከተ የሚናገር ዘገባ እንደ ሆነም ተገልጿል። እ.አ.አ በ 2019 ዓ.ም በማዕከሉ 20 ሺህ ስደተኞች ከተቋሙ ጋር ግንኙነት ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ጨምሮ በሮሜ ከተማ ውስጥ ብቻ 11 ሺ ስደተኞች እንደ ነበሩ ተቋሙ በዘገባው አስፍሯል። እናም ይህ በቅርቡ ይፋ የሆነው መረጃ እንደሚገልጸው አስቸኳይ የሆነ እርምጃ ካልተወሰደ  በስተቀር “ስደተኞችን በተመለከተ ያለው ፖለቲካ፣ የሚጣሉ ገደቦች፣ ድንበር መዝጋት . . . ወዘተ የመሳሰሉ ጉዳዮች ከአሁኑ አግላይ ያልሆኑ ፍትሃዊ ውሳኔዎች ካልተወሰዱ በስተቀር መገለል እና መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎችን እንደ ሚያባብሱ፣ ይህም መላውን ማህበረሰብ ይበልጥ ተጋላጭ እንደ ሚያደርገው” ሪፖርቱ በስፋት ይገልጻል።

በወንድማማች ፍቅር ስደተኞችን መቀበል

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ዳይሬክተር ለሆኑት ለአባ ካሚሎ ሪፓማኖቲ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት መልእክት በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሰውን “ይህ ጽህፈት ቤት በተለይም በዚህ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ መብት ለማስከበር በዚህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እያደረገው የሚገኘውን በትጋት ያታገዘ ተግባር” በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ያደነቁ እና ያመሰገኑ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጥገኝነት የማግኘት መብት እንዲያገኙ ተቋም በማስቻሉ አመስግነው ጦርነትን፣ ረሃብን፣ ከባድ የሆነ ሰባዊ ቀዎስን በመሸሽ ወደ ተለያዩ አገራት የሚሰደዱትን ስደተኞች ተቀብሎ ማስተናገዱን እንዲቀጥል ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገልጸዋል። በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ “ስደተኞችን” በተመለከተ ከሰጠው ትርጓሜ ጋር ከሞላ ጎደለ እንደ ሚስማሙ የገለጹ ሲሆን በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ሰራተኞች ለስደተኞች ትኩረት በመስጠት በወንድማማችነት ፍቅር እንዲቀበሏቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገዋል። ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት እኔ በመንፈስ ለሁሉም ሰው ቅርብ ነኝ እናም በጸሎት እና በፍቅር ከእናንተ ጋር መሆኔን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ብለዋል። በሰዎች መካከል ሰላም፣ ፍትህ እና ቅንነት በሌለበት ዓለም ውስጥ እምነት እና ተስፋ እንዲኖር ማድረግ  ተገቢ ነው በዋል። ፡፡

12 June 2020, 18:06