ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ይህ አሁን የምንገኝበት የሰኔ ወር በወር ደረጃ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ልብ የሚታሰብበት ወር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው ለዚህ ለሰኔ ወር ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ “የኢየሱስ ቅዱስ ልብ እንዲነካን እንፍቀድለት” በሚለ መሪ ቃል ጸሎት የሚደረግበት ወር እንዲሆን በመልእክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዚህ በሰኔ ወር “በኮሮና ቫይረስ ማክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ለገቡ ሰዎች በርሕራኄ እና በምሕረት የተሞላው የኢየሱስ ልብ በችግር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ በኢየሱስ ልብ ውስጥ የህይወት መንገዶችን ማግኘት ይችሉ ዘንድ እንጸልይ” ማለታቸው ተገልጿል።

በመላው ዓለም በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ለገቡ ሰዎች በዚህ በሰኔ ወር ጸሎት በማድረግ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ እንዲነካን በመፍቀድ ጸሎት ማደረግ እንደ ሚገብ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም በወረርሽኙ የተነሳ መከራ የደርሰባቸው ሰዎች  የሕይወትን መንገድ ያገኙ ዘንድ ምዕመኑ እንዲጸልዩ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል። ሥቃይ፣ መከራ እና ችግር በሚኖርበት ስፍራ ሁሉ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ በዚያ ይገኛል፣ ማንም ሰው ብቻውን አይደለም የኢየሱስ ልብ ከሁላችንም ጎን ይገኛል ብለዋል።

ብዙ ሰዎች በዚህ ወረርሽኝ የተነሳ ከባድ ችግር ውስጥ የገኛሉ።  የሰዎችን ሕይወት ወደ ሚቀይር እና ወደ ርህራሄ መንገድ ወደ ሚመራን ወደ ክርስቶስ ቅዱስ ልብ የሚያመጣውን ርህራሄ የተሞላበት ጎዳና በመከተል እነሱን ልንረዳቸው እንችላለን። የሚሰቃዩ ሰዎች ሕይወታቸውን በኢየሱስ ልብ እንዲነካ በማድረግ የህይወት ጎዳናዎችን እንዲያገኙ እንጸልይ።

ለኢየሱስ ቅዱስ ልብ የሚደረግ አምልኮ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለዚህ ለሰኔ ወር ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ለኢየሱስ ቅዱስ ልብ እንዲነካን ጸሎት ማድረግ ይኖርብናል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያተኮረ መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ለዚህ ለኢየሱስ ቅዱስ ልብ የሚደረግ ስርዓተ አምልኮ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሚደረግ ስርዓተ አምልኮ እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን የኢየሱስ ቅድስ ልብ ለቅድስት ማርያም ማርጌሪታ ከተገለጸ በኋላ ለኢየሱስ ቅዱስ ልብ አክብሮት በመስጠት የሚደረግ ጸሎት እንደ ሆነ ገልጸዋል።

07 June 2020, 12:03