ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቅዱስ ቁርባን ማህደረ ትውስታን ያነቃል፣ አገልጋይ እንድንሆን ያነሳሳናል አሉ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በሰኔ 07/2012 ዓ.ም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደም የሚታሰብበት ዓመታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ተገልጿል። ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ስብከት ቅዱስ ቁርባን ማህደረ ትውስታን መልሶ ያንቃል፣ አገልጋይ እንድንሆን ያነሳሳናል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ - ቫቲካን

ጌታ በሐዘን እና በመከራ ውስጥ የነበውን ሕይወታችንን ወደ ደስታ በመቀየር በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች መንከባከብ የምንችልበትን ስጦታ ትቶልን አልፏል በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ይህ የመታሰቢያ በዓል “በቤተክርስቲያንና በሕይወት ውስጥ በመጀመሪያ ሊቀመጥ የሚገባ ውድ ሀብት” ነው ብለዋል።  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም የሚታሰብበት እለት በተከበረበት ወቅት ያደረጉት ስብከት መሰረታዊ የሆኑ ሐሳቦች የተገለጹበት እና የቅዱስ ቁርባን መሰረታዊ ባሕሪያት ጠንካራ የሆኑ ጎኖች በትህትና የተገለጹበት ነው።

የአንድነት ሰንሰለቶች ያስፈልጉናል

እንደ ህዝብ የመሰብሰብ አስፈላጊነት ማስታወሱ አስፈላጊ ነው በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የተነበቡትን ምንባባት በመጥቀስ በሕይወታችን ውስጥ እግዚአብሔር ጣልቃ በመግባት እንድንገናኝ ያደርገንን መልካም ነገር በማስታወስ ተገቢ ነው ብለዋል። ይህ “ወላጅ አልባ የሆንን ሕጻናት” እንደ ሆንን ሆኖ የሚሰማንን፣ “አሉታዊ ማህደረ ትውስታ” እና “ዝግ ማህደረ ትውስታችን” የሚፈውስ ኃይል ነው፣ የእነዚህን ሦስት የሕይወት ዘርፎች ትርጉም በማብራራት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱን ስብከታቸውን ቀጥለዋል። እኛ ብቻችንን አይደለንም ቅዱስ ቁርባን “በውስጣችን ያሉትን ነገሮች ረሀብ በማጥፋት የማገልገል ፍላጎትንም ያቀጣጥላል” በመሆኑም ከቅዱስ ቁርባን ጋር ያለንን ሕብረት አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።

እሱ ምቹ በሆነው የአኗኗር ዘይቤአችን ውስጥ ግብቶ ያስነሳናል ፣ እኛ ለመመገብ አፋችንን መክፈት እንዳልብን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለመመገብ መዘርጋት የሚኖርብን የእሱ እጆች መሆናችንን ያስታውሰናል። ምግብ እና ክብር እየተራቡ የሚገኙ ሰዎችን፣ ስራ አጥ የሆኑ እና ወደ ፊት ለመጓዝ ያዳገታቸውን ሰዎች በአስቸኳይ መንከባከብ አስፈላጊ ነው። ደግሞም ኢየሱስ የሚሰጠን እንጀራ ተጨባጭ እንደ መሆኑ መጠን እኛም ለሌሎች የምናደርገው ድጋፍ ተጨባጭ መሆን ይኖርበታል። እውነተኛ ቅርበት ያስፈልጋል ፣ እውነተኛ የትብብር ሰንሰለቶች ያስፈልጋሉ። በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ኢየሱስ ራሱን ወደ እኛ ያቀርባል፣ እኛም በቅርባችን የሚገኙትን ሰዎች ብቻቸውን መተው አይኖርብንም!

ቅዱስ ቁርባን እውነት ነው

እናም ትውስታ የታሪኩ አካል ከሆነ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ ካለበት የቅዱስ ቁርባን ተመክሮ ሊኖረን ይገባል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስለሆነም ጌታ ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ትቶልን የሄደው ነገር ግን ትውስታ ፣ የፍቅሩ ጣዕም፣ “ፍቅር ያለበት” ሕይወት በመኖር እርሱን ተቀብለን ጌታን ማስታወስ ይኖርብናል ብለዋል። በእርግጥ ኢየሱስ “ይህንን ለመታሰቢያዬ አድርጉ” በማለት መናገሩን በስብከታቸው ያስታወሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “አድርጉ” የሚለው ቃል የሚጠቁመው “ቅዱስ ቁርባን ቀላል የሆነ መታሰቢያ ሳይሆን እሱ ሐቅ ነው ፣ እርሱ ለእኛ የተሰጠ የጌታ ፋሲካ ነው” እናም በመስዋዕተ ቅዳሴ “የጌታ ሞት እና ትንሳኤ ከፊት ለፊታችን ይገለጻሉ” ብለዋል።

ስለሆነም ቅዱስ ቁርባን “በግራ መጋባት መንፈስ የሚጨነቁ እና በአሳዛኝ ክስተቶች ውስጥ የሚገኙ ወላጅ አልባ ሕጻን የሚሰማው ዓይነት ስሜት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን የሚፈውስ ምስጢር ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ ቁርባን “ወላጅ አልባነታችንን ይፈውሳል” እናም የኢየሱስን ፍቅር ይሰጠናል ፣ እርሱም  ሕይወታችን ከገባችበት መቃብር ሊያወጣት ይችላል ብለዋል።

 

14 June 2020, 13:23