በቅዱስ ቶማስ አኲኖስ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ፣ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የባሕል ኢንስቲትዩት ምስረታ፣ በቅዱስ ቶማስ አኲኖስ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ፣ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የባሕል ኢንስቲትዩት ምስረታ፣ 

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለቅዱስ ቶማስ አኩዊኖስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት መልዕክት ልከዋል።

ግንቦት 10/2012 ዓ. ም. ተከብሮ የዋለውን የቀድሞ ር. ሊ. ጳ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልደት መቶኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልክት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በቅዱስ ቶማስ አኲኖስ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብሩህ እና ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩ አስታውሰው፣ በዩኒቨርሲቲው በሚገኝ የፍልስፍና ትምህርት ፋከልቲ ሥር በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስም የሚጠራ አዲስ የባሕል ኢንስቲትዩት በመመስረቱ አድናቆታቸውን ገልጸው በተጨማሪም ለመላው አካደሚክ ማኅበረሰብ እና በኢንስቲትዩቱ ምስረታ ላይ የተገኙትን በሙሉ፣ ለኢንስቲትዩቱ ምስረታ ድጋፍ ያደረጉ፣ ፉቱራ ዩቬታ እና ቅዱስ ኒኮላ ለተባሉ ሁለት የፖላንድ አገር ፋውንዴሽን ማኅበራት ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

የቫቲካን ዜና፤

ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በዘመናችን ባሕል ላይ ትኩረት በማድረግ የተለያዩ ጥናቶችን ለማካሄድ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው ፣ ይህን ለማድረግ የኢንስቲትዩቱ አስተባባሪዎች ባሕልን በስፋት በመመልከት እውቅ የፍልስፍና እና የሥነ መለኮት አዋቂዎች፣ ወንዶችን እና ሴቶችን ማስተባበር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይህ ተቋም እንዲመሠረት ቀዳሚ ተቃናይ እንደነበሩ እና ከፍተኛ ምኞት የነበራቸው መሆኑን አስታውሰዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን ሃብታም እና ባለብዙ ገፅታ ቅርስ ላወረሱት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በነጻ እና ጥልቅ በሆኑ ሃሳባቸው ፣ ለእግዚአብሔር እና ለሰው ባላቸውን ፍቅር ፣ እንዲሁም ለፍጥረት ፣ ለታሪክ እና ለጥበባት ባላቸው ፍቅር ምሳሌ ሆነው መገኘታቸውን አስታውሰዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ባካበቱት የሕይወት ልምድ፣ በተለይም የታሪክ ሂደቶችን እና የግል ስቃዮቻቸውን፣ በሌሎች ሰዎች ሕይወት እና ባሕል ጥልቅ ምርምር በማድረግ፣ እያንዳንዱ የቅዱስ ወንጌል ምስክርነት ለማቅረብ   መንፈስ ቅዱስ ያገዛቸው መሆኑን አስረድተዋል። ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ በመጀመሪያ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው “ከሁሉ  ባሕል እና ርዕዮተ ዓለማዊ ፅንሰ-ሀሳቦች፣ እንዲሁም መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር ውይይቶችን ማድረግ እንፈልጋለን” ማለታቸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ ይህን የሚያደርጉት የሰዎችን ባሕል እና ርዕዮተ ዓለማዊ ፅንሰ-ሀሳቦችን በማክበር፣ የሐዋርያትን የሚስዮናዊነት አመለካከት በመከተል ነው” ማለታቸውን አስታውሰዋል። ሚስዮናዊነት አመለካከት የሚጀምረው፣ አንድ ሰው ውስጣዊ ሃይልን በማንቀሳቀስ ያጋጠሙትን ችግሮች በአሸናፊነት ለማለፍ የተጠቀመባቸውን መንገዶችን በመረዳት፣ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበላቸውን ስጦታዎች በማክበር እና  እርሱ ወደሚይሳየው አቅጣጫ በመጓዝ መሆኑን “የሰው ልጅ አዳኝ” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ቁጥር 12 ላይ መግለጻቸውን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስታውሰዋል።

ወደ ፊት የምትጓዝ ቤተክርስቲያን አባል ከሆንን ይህን መንገድ መከተል ይኖርብናል ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አክለውም ባለን ዕውቀት ሳንገደብ ወይም ሳንወሰን ለተጠራንበት ተልዕኮ ታማኞች ሆነን መገኘት ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህ ዕቅድ ሮም ከተማ በሚገኝ ቅዱስ ቶማስ አኲኖስ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሥፍራን ማግኘቱ አስደስቶኛል ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የቅዱስ ቶማስ አኲኖስ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚመጡ አካዳሚክ ማኅበረሰብን፣ ፕሮፌሰሮችን እና ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ በመሆኑ፣ በዓለማችን የዛሬዎቹን ባሕሎች የሚያጋጥሙ ግንባር ቀደም ተግዳሮቶች መተርጎም ወይም መተንተን ይቻላል ብለዋል።

የዶሜኒካዊ ገዳማዊያን ማኅበር ባሕል ፣ በእምነት እና ይዘቱ ላይ ምክንያታዊ ሃሳብ በማቅረብ፣ በቤተክርስቲያን አስተምህሮች በማመሳከር በዩኒቨርሲቲው የተቋቋመው ኢንስቲትዩት በሚያካህዷቸው ጥናቶች ላይ ብርታትን በመጨመር፣ የመንፈስ ነጻነትን በማቀዳጀት እና ምሁራዊ ሐቀኝነት በማከል ምቹ መንገድ እንደሚከፍት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ፣ “ብርሃን በቤተክርስቲያን” ባሉት ሐዋርያዊ መልዕክታቸው፣ እንደዚሁም ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “እምነትና ምክንያታዊነት” ባሉት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን የገለጹ መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጨረሻም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ ወንድሞች እና እህቶች፣ በአዲሱ ኢንስቲቱት ምስረታ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የአስተዳደር ክፍል ለሚያበረክቱት ተግባራት መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ልከውላቸዋል።           

20 May 2020, 17:30